>

በጭና ቀበሌ በግፍ ከተጨፈጨፉት ቤተሰቦች  የተሰማ እማኝነት...!!! (ዘ ሚካኤል ዮሀንስ)

በጭና ቀበሌ በግፍ ከተጨፈጨፉት ቤተሰቦች  የተሰማ እማኝነት…!!!

ዘ ሚካኤል ዮሀንስ

በጭና ቀበሌ ለተጨፈጨፉት ወገኖቻችን በጋራ በወቅን ወይብላ ማሪያም የሀዘን ስነስርዓት ሲካሄድ ከጋዜጠኞች ቡድን ጋር በመሆን ከሀዘንተኞቹ የተገኘ መረጃ:-
 
1. ወ/ሮ አበበች ጀጃው
የተገደለባት፡ባሏ አቶ ጥላሁን
የወደመ ንብረት፡13 የቤት እንስሳት፣ አንድ ቤት ሙሉ በሙሉ
የቤተሰብ ብዛት:አምስት ልጆች እራሳቸውን ያልቻሉ
የባሏን አስከሬን ለሶስት ቀን ታቅፋ የቆየች
የአገዳደል ሁኔታ፡ ከቤት አስወጥተው በሩ ላይ ከሚስቱ ፊት
2. ወ/ሮ ብድር ተስፋ
የተገደለባት፡ባሏ አቶ ዋናው ገበየሁ
የወደመ ንብረት፡ዘጠኝ የቤት እንስሳት እና የነበረ እህል የአገዳደል ሁኔታ፡ዕቃ ሲያሸክሙት ቆይተው እጁን የፊጢኝ ታስሮ የተገደለ።
3. ወ/ሮ ብርቄ ውብሸት
የተገደለባት፡ ባለቤትዋ አቶ እያሱ ደምሴ
የወደመ ንብረት፡8 የቤት እንስሳት እና የቤት ቁሳቁስ እህልን ጨምሮ
የአገዳደል ሁኔታ: ከቤት አውጥተው ከሚስቱ ፊት አስከሬን ወ/ሮ
ብርቄ ለአራት ቀን ያክል ከጎናቸው አስቀምጠው የተገኙ
የቤተሰብ ብዛት፡ስድስት( ከሁለት ዓመት እስከ አስራ ሠባት)
4. ሟች በየነ ሙሉ እና ልጅ ካሳው በየነ
የአገዳደል ሁኔታ፡ ጎረቤት እንሸሽ ቢል ‘እኔ ምን ብየ ነው የምሸሸው ንፁህ ገበሬ ነኝ’ በማለት ጭና ተሸንፈው ሲለቁ ከልጃቸው ጋር ልብሳቸውን አስወልቀው ተሰልፈው የተረሸኑ
የወደመ ንብረት፡13 የቤት እንስሳት እና የቤት ቀለሳቁስ
የቤተሰብ ብዛት፡10
5. ወ/ሮ አቻቻል ዘውዱ ቀለስለኛ ጎንደር ሆስፒታል በመታከም ላይ የሚገኙ
ባል ሟች ቄስ ፈንታየ ምህረቴ
የአገዳደል ሁኔታ፡ቄስ አንገድልም ከቤትህ ውጣ በማለት
ከቤታቸው ሲወጡ የተገደሉ
የወደመ ንብረት፡30 የንብ ቀፎ እና የቤት እንስሳት
6. ወ/ሮ የዝቤ ጫኔ
የተገደለባት፡ባለቤትዋ አቶ ንጉሴ ወንድይራድ
የአገዳደል ሁኔታ:ከቤቱ በማስወጣት የተረሸነ ሚስት ወ/ሮ የዝቤ
የባለቤታቸውን አስከሬን ከውጭ ወደ ውስጥ ጎትተው አስገብተው
አልጋ ላይ ለአምስት ቀን ቀንና ሌሊት አብረው የተገኙ
7. አቶ ዘውዱ ክሳዴ
የተገደሉበት:ሶስት ወንድሞቹ እና አንድ የወንድም ልጅ
የቤተሰብ ብዛት:ከ20 በላይ
8. ሟች ቄስ ጥፍጥ የቤተክርስቲያን ገበዝ
የአገዳደል ሁኔታ የቤተክርስቲያንን ቁልፍ አምጣ ሲሉት አልሰጥም በማለቱ።
9. ለገዜው ስሙን የዘነጋሁት ዓይነ ስውር ከቤት አስወጥተው ይገደል አይገደል
እያለለ ሲከራከሩበት ደንግጦ ገደል ገብቶ በመታከም ላይ ያለ….ከላይ
የተፈፀመው ግፍከብዙ በጥቂቱ ነው።
የሠውን ሠቆቃ መፃፍ እንዲህ ያማል?! እስከመቸ?
Filed in: Amharic