>

አስቸኳይ ጋዜጣዊ መግለጫ  የሰዎች በህይወትና በሰላም የመኖር መብት ሊከበር ይገባል! (ኢሰመጉ)

አስቸኳይ ጋዜጣዊ መግለጫ 
 

የሰዎች በህይወትና በሰላም የመኖር መብት ሊከበር ይገባል! 

ጷግሜ 5 ቀን 2013 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ፡- ኢሰመጉ በትግራይ ክልልና አዋሳኝ አካባቢዎች ያለውን የጦርነት እንቅስቃሴ ተከተሎ በተለያዩ አካባቢዎች ያለው የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታ እጅግ እንደሚያሳስበው ከዚህ ቀደም ባወጣቸው ጋዜጣዊ መግለጫዎች ሲገልፅ መቆየቱ ይታወሳል።
አሁንም በአማራ ክልል በሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት ወረዳ አምባ ጊዮርጊስ ጭና ተ/ሃይማኖት ቀበሌ ነሐሴ 26 እና 27 በህወሃት ታጣቂ ቡድን ሲቪል በሆኑና ሰላማዊ ሰዎች ላይ የፈጸመውን ጥቃት ተከተሎ በደረሰው ጥፋት ከ200 በላይ ዜጎች የተገደሉ መሆኑን እና አስከሬኖችም በጅምላ ተቀብረው መገኘታቸውን ከነዚህም ውስጥ ህጻናት፣ ሴቶችና አዛውንቶች እንደሚገኙበት እንዲሁም በአካባቢው ነዋሪ ከነበሩት ሰዎች ውስጥም ከ100 በላይ የሚሆኑ ዜጎች አሁን የደረሱበት እንደማይታወቅ ለኢሰመጉ የደረሰው መረጃ ያስረዳል።
በሌላ በኩል በመተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ ውስጥ ታጣቂዎች በከፈቱት ጥቃት በትላንትናው እለት 5  የጸጥታ ኃይሎች እና 1 የቻይና ዜጋ ላይ የደረሰውን ግድያ ኢሰመጉ ያወግዛል።
ጥቃቱ ሀገራዊ፣ አህጉራዊ እንዲሁም ዓለም አቀፍ ህግጋትን በተፃረረ መልኩ ክቡር በሆነው የሰው ልጅ ህይወት ላይ እያደረሰ ያለውን እልቂት ኢሰመጉ ያወግዛል። በተጨማሪም ጥቃቱን ተከትሎ ንብረታቸው የወደመባቸው እንዲሁም ቀያቸውን በመልቀቅ ወደ ተለያዩ አካባቢዎች ተሰደው የሚገኙ ዜጎች ሁኔታም ኢሰመጉን ያሳስበዋል…
Filed in: Amharic