>

ተረኛዋ ግሸን ደብረ ከርቤ ትሆን እንዴ....???  (ዘመድኩን በቀለ)

ተረኛዋ ግሸን ደብረ ከርቤ ትሆን እንዴ….??? 

ዘመድኩን በቀለ

 
… እንደሚሰማውና ልቤን ድክም እያደረጉ ካሉት ምክንያቶች መካከል ይሄ በተጠና መልኩ ዐቢይና ህወሓት ተመካክረው ግሸን ለመግባት በ30 ኪሜ ርቀት ላይ ይገኛሉ ተብሏል። እስከ አሁን ባለኝ መረጃ በአምባሰል ወረዳ ውስጥ ከሚገኙ ቀበሌዎች ቀበሌ 015 እና 016 በህውሓት ኃይሎች ስር እንዲገቡ  መደረጋቸው ተገልጧል። እንዲያውም ዛሬ ወደ ቀበሌ 017 እና 018 ሊገቡ ይችላሉ ሁላ ነው የሚባለው።  
… መንግሥት ወደ አካባቢው ቁጥራቸው አነስተኛ የሆኑ ወታደሮችን ማስገባቱ የተነገረ ሲሆን ከወራሪው የሰው ኃይል ብዛት ጋር ሲነፃፀር ግን ይሄ በቂ እንዳይደለ ነው የሚነገረው። እንደተለመደው የዐቢይ አሕመድ ወታደሮች ከተማረኩ ወይንም ወደ ኋላ ካፈገፈጉ ታላቋ ግሸን ደብረ ከርቤ በወራሪው ኃይል ስር መወደቋ እንደማይቀር ተሰግቷል።
… በአምባሰል ዙርያ ባሉት ቀበሌዎች የሚኖሩ ነዋሪዎች በእጃቸው የሚገኘውን መሣሪያ በህወሓት ትእዛዝ በድኑ ብአዴን ሙልጭ አድርጎ ስለቀማና ስለገፈፋቸው ከበትር በቀር ምንም የለውም። እናም ራሱን እንኳ መከላከል አይችልም። እንግዲህ በዐቢይ አሕመድ መንግሥት ምርጥ የአመራር ችሎታ መሰረት ሰሜኑ ክፍል እየደቀቀ፣ እንኩትኩቱም እየወጣ ነው።
… ገና ጦርነቱ እንደተጀመረ በትግራይ የሚገኙ ታላላቅ ገዳማት እና አድባራት ከነ አገልጋዮቻቸው በተጠና መንገድ እንዲወድሙም እንዲወገዱም ተደርጓል። ህወሓት በዐቢይ እና በሻአቢያ እያሳበበች፣ እነ ዐቢይ በህወሓት እያሳበቡ በመሃል ተዋሕዶ ወድማለች። የትግራዩን ውድመት ከጨረሱ በኋላም እነ ዐቢይ አሕመድ አሊ ጦርነቱን በቀጥታ ወደ ዐማራ ክልል በማምጣት ዐማራን እየወቁት እያደቀቁትም ነው።
… የቅዱስ ላሊበላ ገዳምና በዙሪያው የሚገኙ የላስታ አድባራትና ገዳማት እስከአሁን በምን ሁናቴ ላይ እንዳሉ አይታወቅም። እነ ሂዊ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ዩኒቨርሲቲ ተብሎ በሚታወቀው ሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳም ለመግባት ከጫፍ ደርሰው ነው የተመለሱት። አሁን ደግሞ ይኸው ወደ ግሸን ደብረ ከርቤ እንዲገቡ መንገድ እየተመቻቸላቸው ይመስላል።
… ታቦተ ጽዮንን ፍለጋው ቀጥሏል። አክሱም፣ ደብረ ዳሞ፣ ዋልድባ፣ ቅዱስ ላሊበላ፣ አሁን ደግሞ ግሸን ደብረ ከርቤ ማርያም። ከዚያ የሚቀሩት የጣና ሀይቅ ገዳማት ናቸው። እያለ እያለ ወደ ጎጃም እና ሸዋ ይዘልቃል። ሲመስለኝ ጉዳዩ ሃይማኖታዊ ነው። ታቦቷን ቢያገኟት ጦርነቱን የሚያቆሙት ሁላ ይመስለኛል። ሁለቱም ይህን ተልእኮ ይዘው እየሠሩም ይመስለኛል።
… ከአዲስ አበባ ወደ ትግራይ የሄዱት መነኮሳትና ካህናት ህወሓት በወረራ በያዛቻቸው አካባቢዎች ሁሉ በየቤተ መቅደሱ እየገቡ በሰፊው የጽላት ዘረፋ ላይ መሰማራታቸው መገለፁም ለዚሁ አንድ ማሳያ ነው። ቅርሱን ፅላቱን እንደ ጉድ ነው አሉ የሚሰበስቡት።
… የዛሬ ዓመት ተናግሬዋለሁ። አሁንም እደግመዋለሁ። ይሄ የዐቢይ አሕመድ አሊ፣ የደመቀ መኮንን ሐሰን፣ የሙፈሪያት ካሚል፣ የአገኘሁ ተሻገር መንግሥት ዘመን እስኪያልፍ በየገዳማቱና አድባራቱ የሚገኙ ቅርሶች ልክ እንደ ታቦተ ጽዮን ለጊዜው ቢሰወሩ መልካም ነው። እደግመዋለሁ። ቅርሶች ይቀበሩ። በምስጢርም እስከጊዜው ድረስ ይቀመጡ።
Filed in: Amharic