>

"ካሸነፍን አገር እንሆናለን....!!!" የህወሀት አፈ ቀላጤ (ጌታቸው ረዳ)

“ካሸነፍን አገር እንሆናለን….!!!

የህወሀት አፈ ቀላጤ ጌታቸው ረዳ
“በኢትዮጵያ ላይ ጦርነት የተከፈተው በትግራይ አቅጣጫ ብቻ አይደለም። በኦሮሚያም ቤንሻንጉልም በሶማሌ ክልልም  በጋምቤላም በኩልም ነው።……ተወግተን ስናሸንፍ ትግራይ የምትባል ሀገር እንመሰርታለን።”
 
ጌታቸው ረዳ፣ በግብፅ ሚዲያ ቀርቦ የተናገረው
ሱሌይማን አብደላ

ጌታቸው ረዳ በግብፅ ሚዲያ ላይ እንግዳው ሆኖ ቀርቧል። ሚዲያው የፕሬዝዳንት ሲሲ ሚዲያ ነው። ያቋቋመው እሱ ነው። እዚህ ሚዲያ ላይ የሚሰሩ ሰዎች እንግዳ ሆነው የሚቀርቡ ሰዎች በግብፅ የደህንነት መስሪያ ቤት እውቅናና ተልዕኮ ነው። በዚህ ሚዲያ ላይ ማንኛውም የፖለቲካ ሰው ወይም የኔ ቢጤ ቀርቦ ትንታኔ አይሰጠም። ሚዲያው የፕሬዝዳንት ሲሲ ትልቁ ተወንጫፊ ሚሳኤሉና የተልዕኮ ማስፈፀሚያ መሳሪያው ነው።
ጌታቸው በዚህ ሚዲያ ላይ እንዴት ቀረበ ብሎ መጠየቅ አያስፈልግም። ከላይ እንዳልኳችሁ በዚህ ሚዲያ ላይ የሚቀርቡ ሰዎችን የሚመርጠው፤  እውቅናና ፍቃድ የሚሰጠው የግብፅ የደህንነት መስሪያቤት ነው። ጌቾን በቀላሉ ወደዛ ያስገቧትም ደህንነቶ ናቸው። ወያኔና ግብፅ ምን ያህል ፍቅር ላይ እንዳሉ ከዚህ በላይ ሌላ ማስረጃ የለም።
ጌታቸው ከጋዜጠኛው የቀረበለትን ጥያቄ በሚገባ መልሷል። ተዋግተን አዲስ አበባ ከገባን በህዝብና በክልሉ መንግስት ድምፅ መሰረት ትግራ የምትባል አገር
እንመሰርታለን ብሏል። እኛ ብቻ ሳንሆን ኦሮሞውም ጉምዙም ሶማሌውም ጋቤላውም አገር መሆን ይፈልጋል። ለዚህም አሁን ተጣምረን እየተዋጋን ነው። አሁን በኢትዮጵያ ላይ ጦርነት የተከፈተው በትግራይ አቅጣጫ ብቻ አይደለም በኦሮሚያም ቤንሻንጉልም በሶማሌ ክልልም  በጋምቤላም በኩልም ነው። እኛም ከነሱ ጋር አብረን እየሰራን ነው በቅርቡ የአብይ አሕመድን መግንሥት በውጊያው እናሸንፋለን፤ ይሄንንም ማሳካት የሚያስችሉ ስራዎች ተሰርተው እየተጠናቀቁ ነው ትንሽ ነው የቀረን ብሏል።
ጋዜጠኛው ዋና ዋና ጥያቄዎችን ያደረገው የህወሓትን የወደፊት እቅድ ምንም እንደሆነ መለየት ላይ ነበር። እሱንም አለሳልሶ ጠይቆ ከጌታቸው ረዳ በቂ መልስ አግኜቷል። ተዋግተን ካሸነፍን ህዝብና የትግራይ መንግስት ተመካክረው አገር እንሆናለን እኛም ብቻ ሳንሆን ኦሮሞ ጉምዝ ሱማሌ ጋቤላው ከኛ ጋር ተመሳሳይ ፍላገት ኖሮት አብሮን እየሰራ ነው ብሎ ለጋዜጣጠኛው ጥያቄ ተጊቢውን መልስ ሰቶታል።  በርግጥ ጌታቸው በግብፅ መንግስት ሚዲያ ላይ የቀረበው እንዲሁ አይደለም። ሰዎቹ አብረው በጋራ አገሪቱን ለማፍረስ እየሰሩ ስለሆነ ምን ያህል የጋራ አላማ ቢኖሯቸውም ነው እንዲህ በዚህ በተመረጠ ሚዲያ ላይ ቀርቦ እንግዳ የሆነው ማለትም አያስፈልግም። ህወሓት አሁን ላይ የሚያደርገው ውጊያና አንዳንድ አለማቀፍ ድርጅቶችና የተወሰኑ አገራት በኢትዮጵያ ላይ ለምን ጫና እንደሚያደርጉ ከዚህ ጀርባ ማን ምን እየሰራ እንደሆነ ይታወቃል። ጌታቸውም ዛሬ በትክክለኛው ሚዲያ ትክክለኛው ማንነቱን ይዞ ከነስሙ ለኢትዮጵያውያን አሳውቋል።
Filed in: Amharic