ኢትዮ360 እና የመከላከያ መቀሌን መልቀቅ ….?!?
ምክንያታዊ የሀሳብ ፖለቲካ ገፅ
መከላከያ ሰራዊቱ ለምን ትግራይን ለቆ ወጣ??
ከሚለው በላይ ለምን የአማራ እና የአፋር ክልሎች እንዲወረሩ በዝምታ ስፍራዎችን እየለቀቀ ሁኔታዎችን አመቻቸ?
የሚሉት ጥያቄ ብዙዎችን ግራ ያጋባ ነገር ግን የኢትዮ 360 ፕሮግራም አቅራቢዎቹ ኤርሚያስ እና ሀብታሙ ደጋግመው ምክንያቱን ሲገልፁት የነበረው ጉዳይ እዚህ ጋር ሊነሳ የሚገባው ተገቢ አጀንዳ ነው።
በተለይ የትላንቱን የዶ/ር አብይ ደብዳቤ ላነበበ ሰው ለመከለከያ የተሰጠው ትእዛዝ እና የተፈፀመው ስልታዊ በሚል የተገለፀው እንቅስቃሴ ከፍተኛ አለም አቀፍ ጫና ውስጥ ገብቶ የነበረውን እና በዲፕሎማሲ ክስረት አለም ፊቱን ያዞረበትን መንግስት ጫናውን ለመቀነስ በዋናነት የወንጀል እኩሌታ በመፍጠር ጫናው ወደ ህወሓት መራሹ ሀይል እንዲዞር ለማድረግ በትግራይ ተፈፀመ የተባሉትን ተግባራት በሙሉ በአማራ እና በአፋር ክልሎች የገባው የትግራይ ሀይል እንዲፈፅም እና በተፈፀመው ድርጊት ህወሀትን ለአለም በመክሰስ ዲፕሎማሲያዊ ጫናውን የማርገብ ብሎም አለማቀፉ ማህበረሰብ ህወሀትን በአሸባሪነት እንዲፈርጀው በሚል የራሰበ ሙከራ እንደነበር ግልፅ የሚያደርግ ነው።
በተለይ ይሄ ስልት ከመተግበሩ በፊት ከመነሻው የኢትዮ 360 ተንታኞች የእንቅስቃሴውን አላማና ግብ ሲጠቅሱ እና ሲያብራሩ የነበረ ሲሆን በወቁ ሰሚ ከማግኘት ይልቅ እንደተለመደው በብልፅግና እና የግንቦት7 ካድሬዎች ወቀሳና ውርጅብኝ ነው ያስተናገዱት።
ከዚህ ስልታዊ አላማው በተጨማሪ መከላከያው በትግራይ የገጠመው ፈተና እና ተግዳሮት ጋር ተዳምሮ በመከላከያ የእዝ ሰንሰለት ውስጥ የነበረው ችግር እና እና የሀይል መበታተን ሌላው ትግራይን ለቆ ለመውጣቱ ሊጠቀስ የሚገባው ጉዳይ ነው።
በጣም የሚያሳዝነው ግን ይህንን የወንጀል አቻነት ወይም እኩሌታ ለመፍጠር በተለይ የአማራ እና የአፋር ህዝብ እንዲከፍሉ የተፈረደባቸው መስዋእትነት ክብደትን ላስተዋል እኚህ ሰዎች ለስልጣናቸው ምን ድረስ ሊሄዱ እንደሚችሉ በግልፅ የሚያሳይ ነው በተለይ አለም አቀፉ ማህበረሰብ ሁሉን እቅፍ ድርድር በሚል በቀጥታ ስልጣናቸው ላይ ሲመጣባቸው ህዝቡን የማያስከፍሉት ዋጋ አለመኖሩን የሚያሳይ ነው።
ከህወሀት ከቀደመው የትግል ታሪኩ አውሬነት እና ክፋት ጋር ተዳምሮ የመንግስት ለስልጣኑ ያለው ፍቅር በአማራ ክልል ያስከፈለውን ዋጋ ለተመለከተ በአጠቃላይ እንደሀገር በነዚህ ሰዎች አመራርነት ገና እጅግ የከበደው ፈተና አለመጀመሩን ማሰብ ይቻላል።
በኢህአዴግ አስተሳሰብ በመለስ ዜናዊ ዶክትሬን ተጠምቆ ያደገው የኢህአዴግ ፍርነው። ቡድን ለሁለት ተከፍሎ በስልጣን ጥም እና በእልህ መጋባት ህዝቡን ከማጫረስ በላይ ገና ኢትዮጵያን የማያስከፍላት ዋጋ የለም!
ሁለቱም ሀይሎች ውስጥ ያሉት ሰዎች ኢህአዴጋዊ የካድሬ አስተሳሰብ የስሬታቸው የውቅራቸው ምሰሶ ነው።
የብልፅግና እና የግንቦት ሰባት አሽቃባጭ ተደጋፊ ተደናቸው። አምላኪ ደጋፊዎች ግን የባሰውን የኢትዮጵያን ህዝብ የማደንዘዝ ሚና በመወጣት ህዝቡ የሚከፍለው ዋጋ ከመሸፋፈን አልፎ ህዝቡ ሀገሩን ማዳን የሚችልበትን አማራጭ መፈተሽ እንዳይችል የመጋረድ እና የህዝቡን ተድጋ ቢስ በማድረግ ለብልፅግና ግዞት በማመቻቸት የኢትዮጵያንም የህዝቡንም ፍዳ እያበዙ ያሉ ናቸው።
በነዚህ ሀይሎች ኢትዮጵያ ትድናለች ብሎ ማሰብ………