>

እየሆነ ያለው እንዲህ ነው! ዋሸሁ እንዴ....??? (ዶ/ር ዮናስ )

እየሆነ ያለው እንዲህ ነው! ዋሸሁ እንዴ….???
ዶ/ር ዮናስ አበራ

በመጀመሪያ ባለ ስልቻ ሆዳም አማሮች ከብአዴን ውስጥ ታዘጋጅና በከርስ ትይዛቸዋለህ፣ የአማራን ክልል ደህና ደህና የሚባሉትን መሪዎች ትገድላለህ፣ ህዝቡን በከርሳሞቹ ብአዴኖች በኩል ትጥቅ ታስፈታለህ፣ ክልሉ ልዩ ኃይል እንዳያሰለጥን ከልክለህ ታዳክማለህ፣
የጎንደር፣ የጎጃም፣ የወሎ፣ የሸዋ እያልክ ከፋፍለህ ባለስልጣናቱን እርስ በእርስ ታራኩታለህ፣ጦርነቱን ከትግራይ ምድር ጎትተህ ታመጣና በአማራ ሜዳ ላይ እንዲካሄድ ታደርጋለህ፣
“ቤጌምድር ጀግና ነው፣ ለራሱ አያንስም” ትልና እሱን ትጥቅ ከልክለህ በገፍ ካስታጠከው ወያኔ ጋር ይዋጣላችሁ ብለህ እያጫረስክ ዳር ቆመህ ትመለከታለህ፥ እሱ እዚያ ሲሞሻለቅ እንተ አ አ ላይ ችግኝ ስትተክል ወይም ከሙዚቀኞች ጋር አሼሼ ስትል ትውላለህ፣
ወያኔ አየል ስትል የፌዴራል ጦር ልከህ ኮርኮም ኮርኮም ታደርጋለህ፣ የአማራ ሚሊሻና መከላከያው ሲገፋ “ስልታዊ ማፈግፈግ” ብለህ ሉጓምህን ትስባለህ፣
የሁለቱ መተላለቅ ቀዝቀዝ ሲል ሬንጀር ለብሰህ ቲቪ ላይ ትወጣና “ወያኔን ውጊያ መለማመጃ አደረግነው” የሚል ዘፈን ለቅቀህ እያላገጥክ በነፍስ ወከፍ አምስት አምስት ጥይት ለአማራ ሚሊሻ ታድልና “በመቶ አመት ታይቶ የማይታወቅ አየር ኃይል ገነባን” እያልክ ዙፋንህን በጨበጣ ታስቀጥላለህ፣
ህዝብ ማጉረምረም ሲጀምር ከርሳም የማድቤት ቅልብ አጋፋሪህ የሆነውን፥ ቤተስኪያኗን ከነገባው የሸጠውን ዲያቆን አደባባይ ልከህ “የምታጓጓ ኢትዮጵያ ላመጣላችሁ በአራት ኪሎ ትናንት ምሽት ራእይ ታይቷል በልልኝ እስኪ ይሄንን መንጋ” ብለህ ትልካለህ…
ምክንያቱም አንተ እርኩሱ አብይ አህመድ ነህና!!ይሄ አይደል እየሆነ ያለው?ዋሸሁ እንዴ?
Filed in: Amharic