>

ቆቦ የአማራ ህዝባዊ ሀይል ከተቆጣጠራት በኋላ እንዴት በትግራይ ወራሪ ወደቀች?  (ጎበዜ ሲሳይ)

ቆቦ የአማራ ህዝባዊ ሀይል ከተቆጣጠራት በኋላ እንዴት በትግራይ ወራሪ ወደቀች? 
ጎበዜ ሲሳይ

ራያ ቆቦ ከተማ ጳጉሜ ወር ውስጥ በአርሶ አደሩ ትጥቅ ብቻ ከሕወሓት ታጣቂዎች ነጻ ወጥታ ነበር ።ከዞብል ፤ ከጋቲራ ፤ ከዲቢ እና ከወርቄ የተሰባሰበው አርሶ አደር ወደ ቆቦ ከተማ በመትመም ከሕወሓት ታጣቂዎች ጋር መፋለማቸውን እና የሕወሓት ታጣቂዎችም ወደ አላማጣ በመሸሽ እንደገና ኃይል አሰባስበው ቆቦ ከተማን መልሰው መቆጣጠር መቻላቸውን በጦርነቱ ውስጥ የተሳተፉ አርሶ አደሮች ተናግረዋል።
ከተማዋን መልሶ ለመያዝ በነበረው ፍልሚያ የአርሶ አደሩን ጦር ከኋላ የሚያግዘው በማጣቱ ምክንያት ቆቦ ከተማን ለቆ መመለሱን ገልጸዋል።
የሕወሓት ታጣቂዎችም የአርሶ አደሩን ጦር መውጣት ተከትሎ ከተማዋ በመግባት ቤት ለቤት እየዞሩ ነዋሪዎችን እንደገደሉ በስፍራው የነበሩ የዐይን እማኞች ተናግረዋል።
ገበሬው በጎበዝ አለቃ ተደራጅቶ የሕወሓትን እንቅስቃሴ ማስተጓጎሉን የጠቆሙት እነዚህ አርሶ አደሮች ከመንግስት ደጋፍ እንድደረግላቸውም ጠይቀዋል።
ከቆቦ ከተማ በእስከ ምስራቅ በኩል የአፋር ክልል ዞን አራት (ከለዋን ፤ አውራ እና እዋ) የተባሉ ወረዳዎች ነጻ መሆናቸውን ጠቁመው በዚያው በኩል የተቀናጀ ድጋፍ ቢደረግ ቆቦ ከተማን ነጻ ማውጣት ይቻል ነበር ሲሉ ተናግረዋል።
Filed in: Amharic