>

የሰሜን ወሎ ጉዳይ: (ወንድወሰን ተክሉ)

የሰሜን ወሎ ጉዳይ

አገኘሁ ተሻገር የአማራ ልዩ ኋይል ከኮረም ለቅቆ እንዲወጣ ሶስት ግዜ አዟል-ለምን??

  ወንድወሰን ተክሉ


፨ የዐማራ ልዩ ሀይል ከኮረም እንዲወጣ አገኘሁ ተሻገር ሶስት ጊዜ ለ ዐማራ ልዩ ሀይል አዛዥ ደብዳቤ እንደፃፈ ምን ያህል ዐማራ እውነቱን አውቋል??

፨ ትእዛዝ ያልተቀበሉ የ ዐማራ ልዩ ሀይል አባላት ኮረም ተቆርጠው ቀርተው በጥላት እንዲያልቁ ተደርጎ የጥላትን ክበባ ጥሰውት ከወጡ በኋላ ትእዛዝ አልጠበቃችሁም በሚል ሰቆጣ እንዲታሰሩ እንደተደረገ ስንቱ ዐማራ እዉነቱን አውቋል??

፨ ያለምንም ጦርነት የዐማራ ልዩ ሀይል ወደ ዋጃ እንዲመለስ እንዳደረጉት ስንቶቻችንስ ነን ይህንን እውነት የምናውቅ ??

፨ የመከላከያ ሰራዊት ከ ኮረም እስከ ወልድያ አንድም ጦርነት አለማድረጉን ስንቶቻችን እናውቃለን?የህወሀት ሰራዊት እስከ መቄት ያለውን ስትቆጣጠር ያለ ምንም ጦርነት መሆኑን ስንቶቻችን አውቀናል?መከላከያ ጦርነት ያደረገዉ ወልድያ ከተማ ሲገቡ ብቻ ነውበወልድያው ጦርነት አዬር ሀይል እንዳይሳተፍ ተደርጎ በህወሀት እንዲያዝ ተደረገከ ወልድያ የሸሸው መከላከያ ያለምንም ጦርነት ከ ወልድያ ወደ ውርጌሳ ተጉዞ ውጫሌ ቁጥሮ ላይ ከባድ መሳሪያ እንዳጠመደ ስንቶቻችን እናውቃለን?

፨ ውርጌሳ የሰፈረው መከላከያ ሰራዊት ከ ሁለት ወር በላይ ያለፈው መከላከያ አቅም ስለሌለው ነው?  የ ዐማራ ልዩ ሀይልና ፋኖ ብቻቸውን በዋግና ላስታ እንዲዋጉ የተደረገው የ መከላከያ ሰራዊት እጥረት ስላለ ነው?

በውርጌሳ ግንባር የ ዐማራ ልዩ ሀይል እንዳይሳተፍ የተፈለገበት ምክንያትስ ምን አይነት ሚስጥር ስላላቸው ነው??

፨፨፨፠፠፠፠፨፨፨

አሁን የሰሜን ወሎ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለው ነገር መንግስታዊ ነው የዐማራ ህዝብ በህወሀት መፈፀሙን አይመለከት እንዲፈፀም ሁሉን ነገር ያመቻቸላቸው የ ዐማራ ክልል መንግስትና የፌደራል መንግስትናቸው።

እኛ ሳንደራጅ በሶስት ሳምንት ያለቀን ጦርነት  በቂ ስልጠና ባልወሰዱ የ ህወሀት ሰራዊት ጦርነቱ ሁለት ወር ወስዶባቸው የህወሀት ሰራዊት አንድ ዞን ተቆጣጥራ ተቀመጠች ብለን የምናስብ ህዝብ ከሆን አብደናል መታከም አለብን።

ለተፈፀመው የዘር ጭፍጨፋ የክልላችን፣ የፌደራል መንግስት አመራሮችና የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ ባለስልጣናት ዋና ተጠያቂዎች ናቸው

( ከሰሜን ወሎ ህዝብ በውስጥ ከደሩሱኝ  መልእክቶች  በጥቂቱ)

Filed in: Amharic