>

የት እንሂድ? ለማንስ አቤት እንበል? (ሰለሞን አላምኔ)

የት እንሂድ? ለማንስ አቤት እንበል?

ሰለሞን አላምኔ
*…. የጋዜጠኛ ጌጥዬ ያለው መፈታት ጉዳይ 
የከፍተኛው ፍርድ ቤቱን ችሎት በመዳፈር  ክስ ለ4 ወር ተፍርዶበት በይግባኝ ለ1 ወር ቅጣቱ ተቃሎለት በቃሊቲ እስር ቤት የፍርድ ሂደቱን ከጨረሰ ቀናቶች ቢቆጠሩም እስከዛሬው እለት ድረስ ሊፈታ አልቻለም።
ይህንን ጉዳይ ለማጣራት ባደረግነው ሙከራ በተለይም በጠበቃ ሰለሞን እና በጠበቃ ቤተማርያም አማካኝነት ጉዳዩን ለመከታተል ተሞክሮ፤ በይግባኝ የተወሰነው ማለትም ቅጣቱ ለ4 ወር የነበረው ለ1 ወር የተላለፈው የቅጣት ወረቀት ለቃሊቲ አለመግባቱን እና የተፃፈውም ደብዳቤ ለቃሊቲ መሆን ሲገባው ለቂሊንጦ በስህተት ስለተፃፉ ነው የሚል መልስ ነበር የተሰጠን።
ይሁን እንጅ ጠበቆቻችን የይግባኝ ችሎት ወረቀቱን ረቡእ እለት አስጨርሰውታል። ፍርድ ቤቱም ደብዳቤውን ለሀሙስ ጠዋት እንደሚልኩት ገልፀውልን ነበር።
የት እንሂድ? ለማንስ አቤት እንበል?
አርብ ማለዳ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ይፈታ ብሎ ቢያዝዝም ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ጋዜጠኛ ጌጥዬ ያለውን የተፈረደበትን እስር ቢጨርስም አልፈታም ብሏል። የህግ የበላይነት የማይታወቅባት ሀገሬ ፤ አዛዡ እና ታዛዡ የማይለዩባት ሀገሬ ፤ አሸባሪ ሳይሆን የሀሳብ ሰው በእስር የሚማቅቅባት ሀገሬ #ኢትዮጲያ
የማይፈታበት ምክንያቱን ብጠይቅም የተከሰሰበት በእነ እስክንድር ነጋ ጉዳይ ስለሆነ ዛሬ አንፈታውም፤ ከማክሰኞ በኋሏ አጣርቼ ሌላ ክስ ካለ እንዲቀጥል ካልሆነ ግን ማክሰኞ ነው የምፈታው የሚል መልስ ነው የተመለሰለኝ። መጠየቅ ያለብኝ አካል ይኖር ይሆን ብየ ብጠይቅም ከቃሊቲ እንድወጣ ተነገርኞል።
ሀገሬ የት ነሽ? ፍትሕስ ወዴት ነሽ? በደል እና ግፉስ አይበቃም ወይ? ያስዝናል??? ነገር ግን ትግሉ ይቀጥላል!!  ( ማን ያውቃል ማታ ላይ ሊፈቱት ይችላሉ እኛ ትተነው ከሄድን በኋላ ) ድል ለዲሞክራሲ
Filed in: Amharic