>
5:13 pm - Thursday April 18, 7315

ብልፅግና ወይም ሞት ብለን   ከተደፋን ቢረግጡን ስለም ይከፋናል?!  (ጎዳና ያእቆብ)

ብልፅግና ወይም ሞት ብለን   ከተደፋን ቢረግጡን ስለም ይከፋናል?! 
ጎዳና ያእቆብ

የመንግስት አይነት (form of government) ለማወቅ ማነው የሚመራው የሚለው ላይ ከማተኮር ይልቅ ማን ይጠቀማል (ወይም ተጠቀመ) የሚለው ግልፅ የሆነ ምላሽ ይሰጣል::
እውነተኛ ተረኛነትን የምታውቀው በተረኞች የሚፈፀም ወንጀል እንኳን ተቃሎ ሲታይና የጦስ ዶሮ ሲፈለግለት ነው:: ለምሳሌ አሜሪካ ውስጥ ፈረንጅ ሰዎችን ሲገድል ክፉ ሆኖ ነው ከማለት ይልቅ የአይምሮ በሽተኛ ሆኖ ይሆን? በህፃንነቱ ከአልጋ ላይ ወድቆ ጭንቅላቱ ተጎትቶ ይሆን? የሚሉ ማስተባበያዎች የብዙኃን መገናኛ ሲፈጥርላቸው ጥቁር አንድ ሰው ሲገድል ክፉ አረመኔ ፀረ-ሰው የሚሉ ፍረጃዎች ላይ ይገባል:: ሙስሊም በተለይ ደግሞ አረብ አንድ ዛፍ ሲያቃጥል አሸባሪ ለማለት ብዙኃን መገናኛዎች ሲረባረቡ ይታያል::
በኢትዮጵያና በአሜሪካ መካከል ያለ ልዩነት ፍርድ ቤቱ የህግ ሂደቱን ከማንነት (ነጭ ጥቁር አረብ ወዘተ) አንፃር  ሳይሆን ከህግ እና ከህግ አንፃር ብቻ መሆኑ ነው::
ለእስክንድር ነጋ አስቴር ስዩም ስንታየው ቸኮል አስካለ አቶ ታዲዮስን አስሮ እያንገላታ በአሸባሪነት የተፈረጀውን የኦነግ አመራር ሽመልስ አብዲሳ ሳይፀየፍ አቅፎ ስሞ ይቅርታ ሲለው ስታይ በኢትዮጵያ ውስጥ ዛሬ ማን ነዋሪ ማን ደግሞ አኗኗሪ እንደሆነ ያሳይኸል:: ማን ተረኛ እንደሆነ ያሳይኸል::
ከህግ ተጠያቂነት በላይ መሆን አንዱ በተረኛነት የሚገኝ ጥቅማ ጥቅም ነው:: የስልጣን ክፍፍል: የኢኮኖሚ ተጠቃሚ መሆን ሌላው የተረኛነት መገለጫ ነው::
ለነገሩኮ የአብይ አህመድ ብልፅግና ሳይነግረን ያደረገው አንድ ነገር ስለሌለ እነ አብይ አህመድን መወንጀል አይቻልም:: ወደሽ ከተደፋሽ ቢረግጡሽ አይክፋሽ እንዲሉ ብልፅግና የኦሮሞ ነው ብለው በግልፅ እየነገሩን ብልፅግና ወይም ሞት ካልን ወደን ተደፍተናል::
የኦሮሚያ ብሔራዊ መዝሙር ላይ <<ከመቶ አመት በኃላ ስልጣን በእጃችን ገባ>> ሲሉን ስለ ፌደራል መንግስት እንጂ ስለ ክልላዊ መንግስት እያወሩ እንዳልሆነ ግልፅ ሆኖ ሳለ ብልፅግና ወይም ሞት ብለን ወደን ከተደፋን ቢረግጡን እንዴት ይከፋናል?!
አንድ እርግጠ የሆነ ነገር ቢሆን ቢኖር ተረኛ ስንል የኦሮሞ ካድሬዎችን እንጂ የኦሮሞ ማኅበረሰብ  ተጎጂ እንጂ ተጠቃሚ እንደማሆን ግልፅ ነው:: ልክ ትላንት በህዋሃት ተረኛነት ዘመን የትግራይ ማኅበረሰብ ተጠቃሚ እንዳልሆነ ሁሉ ማለት ነው::
ነፃ እርምጃ እየተወሰደባቸው ያሉት የኦሮሞ ልጆች ናቸው::
ስልካችሁ ጮኸ ተብለው የሚገደሉት የኦሮሞ ልጆች ናቸው::
50 ሺ የሚሆኑ በእስር የሚማቅቁ እናም የሚጮህላቸው የሌለ የኦሮሞ ልጆች ናቸው::
ጃዋር ተከበብኩ ባለ ጊዜ ከተጨፈጨፉት መካከል በአብይ አህመድ ምስክርነት 57% (ከግማሽ በላዩ) ኦሮሞች ናቸው ብሎናልና ሕዝብ እንደ ህዝብ ተጠቃሚ አለመሆን ብቻ ሳይሆን በቀጥታ ተጎጂ ነው::ሰለባ ነው::
አቶ ብርሀኑ ነጋ <<ሻሸመኔን ያነደዷት እና ሁለት መቶ የሚጠጉ ንፁኃንን ያረዱ ሰዎች ሶስት መቶ ብር እና ላይተር የተሰጣቸው ምንም የማያውቁ ወጣቶች ናቸው>> ብሎ ወንጀላቸውን ሲያስተባብል እያየን በዝምታ ወደን ከተደፋን ቢረግጡን ስለም ይከፋናል?!
ጦርነቱ በተጀመረ ሰሞን በኦሮሚያ ላይ ንፁኃንን በአማራነታቸና በኦርቶዶክስነታቸው ብቻ የሚያርዱ አረመኔዎችን << ህዋሃት ክፉና ደጉን የማያውቁ የዋህ ወጣቶችን እያስታጠቁና እና በገንዘብ እየደለሉ ያሰማራሉ>> ብሎ በኦሮሚያ አሰቃቂ እና ፀረ-ሰው የሆነ ድርጊት ይሚፈፅሙትን <<ክፉና ደጉን የማያውቁ የዋሆች>> ብሎ ከተነከሩበት ወንጀል እና በእጃቸው ካለ የንፁኃን ደም ሲያነፃቸው ዝም ብለን ወደን ተደፍተናል ቢረግጡን ስለ ምን ይከፋናል?!
ክፉ እና ደጉን የማያውቁ የዋሆች ከሚላቸው ወንጀለኞች አንዱ ይህ ሽመልስ በእቅፉ ይዞ ይቅርታ ያደረገለት ሰው ነው:: ነገ ከነገ ወዲያ ሹመት ባይሰጠው ይደንቀኛል::
አማራ መጨፍጨፍና የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያናትና ከማቃጠል አማራ ወደ ፍፁም ድህነት እና ተመፅዋችነት ማሸጋገርን የመሰለ ታላቅ ስራ ሰርቶ እንዴት አይታቀፍ? እንዴት አይሸለም? እንዴትስ አይሾም:: <<አማራ እየጠፋ ነው:: ሌሎች ክልሎች ቁልቁል እየሄዱ ነው::>> ያለው ሽመልስ አብዲሳ የአብይ አህመድን ቃል ልዋስና << እናስባለን: እናቅዳለን: እንናገራለን: በጥራት እንተገብራለን::>> ብሎ ዛሬም እንዳስታወሰን <<እንሰብራለን እንበላለን እንገዛለን>> ብሎ አስቧል: አቅዷል: ተናግሯል: በጥራትም ተግብሯልና ምን አድርጉ እንላቸዋለን?!
ሲነግሩን በዝምታ አውቀን ከተደፋን በእቅድና በጥራት ሲረግጡን ስለምን ይከፋናል? ኢትዮጵያ በድንቁርና በንፁኃን ደም በለየለት ጦርነት እየበለፀገች ነው:: ያን እንደሚያደርጉ ደግሞ አስበው አቅደው ተናግረው በጥራት እየተገበሩት ነው:: ትግራይን በሻሻ በማድረግ እንዳበለፀጓት ሁሉ አማራ ክልልንም የተናጥል ተኩስ አቁም ብለን ለቀን በመውጣትና መከላከያውን ወደ ችግኝ ተከላ በማሰማራት አማራና ትግራይን ደም እናቃባ: ሁለት ኦርቶዶክሳዊያን እርስ በርስ ይጨራረሱ ታሪካዊ ቅርሶች ይውደሙ ሰሜናዊያን ከዚህ በኃላ በኢትዮጵያ ፓለቲካ ላይ ምንም ድርሻ እንዳይኖራቸው እና አከርካሪያቸው እንዲሰበር <<የህግ ማስከበር ዘምቻ>> ተብሎ የተጀመረውን ጦርነት በሁለቱ መካከል እንዲሆን እናድርግ ብለው አስበው አቅደው አማራ ካለ ማንም እርዳታ ለትግራይ አያንስም ብለው ተናግረው በጥራት እየተገበሩት ይገኛሉ::
ቃል በተግባር ይሉሀል ይሄ ነው!
ከአሸባሪ ጋር አንደረደርም እንደመስሳቸዋለን የሚልህ ኦህዴድ መራሹ ኢህአዴግ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት  አሸባሪ ተብሎ ከተፈረጀው ብድን ጋር መደራደር ብቻ አይደለም እንዲህ እየተቃቀፈ እንደ አስቴር አወቀ ፍቅር አነሰኝ ይልልሀል!!! አስቧል:: አቅዷል:: ተናግሯል:: በጥራት ተግብሯል::
Filed in: Amharic