>

".... ፋሽስት ወያኔዎች ዛሬ ያመጡት፣ ያልነበራቸው አመልና የታየባቸው አዲስ ጠባይ አለን...??? (አቻምየለህ ታምሩ)

“…. ፋሽስት ወያኔዎች ዛሬ ያመጡት፣ ያልነበራቸው አመልና የታየባቸው አዲስ ጠባይ አለን…???
አቻምየለህ ታምሩ


“ዳንኤል ክብረት እንዲህ በአሰቃቂ መልኩ  የገለጸው የጽልመት ድርጅት በግፍ በወረራቸው አካበቢዎች ተጨማሪ ጥፋት እንዳያደርስ አባል የሆነበት አገዛዝስ ምን እየሰራ ነው?!??”
ፋሽስት ወያኔዎች ዛሬ ብቻ ሳይሆን ዳንኤል ክብረት አብሯቸው ይሰራ በነበረበትም ወቅት ሞራልና ሥነ-ምግባር የሌላቸው፤ ሥነ-ሥርዓት፣ ሚዛናዊነት፣ ቅንነትና መልካምነት ሲያልፍ የማያውቁ፤ ያላቸውን አቅምና ጉልበት ሁሉ ሳይቆጥቡ ለክፉ ተግባር ያዋሉ፤ በእምነትና በቅን ሀሳብ ተገፋፍተው ያለፏቸው ክፉ ነገሮች በመብራት ተፈልገው የማይገኙባቸው፤ በዘር ማጥፋት፣ በዘረፋ፣ በውድመትና በጅምላ ፍጅት ክብረወሰን የተቀዳጁ ዘረኞች፣ ግፈኞች፣ ጨካኞች፣ ስግብግቦችና በቃኝ ማለትን የማያውቁና ሁሉን ለእኔ የሚሉ ደካማ ፍጥረቶችና አረመኔዎች ነበሩ።
ባጭሩ ዳንኤል ክብረት አሰላለፉን አስተካክሎ ከተለያቸው በኋላ ፋሽስት ወያኔዎች ያመጡት ያልነበራቸው አመልና የታየባቸው አዲስ ጠባይ የለም። ፋሽስት ወያኔ በግፍ በወረራቸው በወሎ፣ በጎንደርና በአፋር አካባቢዎች የፈጸመውና  እየፈጸመው የሚገኘው የዘር ማጥፋት፣ ዘረፋ፣ ውድመትና የጅምላ ፍጅት ባለፉት 46 ዓመታት ሲፈጸመው የኖረው ቅጥያ ነው።
አሁን ጥያቄው መሆን ያለበት ዳንኤል ክብረት በአካል ተገኝቼ ተመልክቻለሁ ባላቸው አካባቢዎች ያየውን አይነት ጥፋት፣ ውድመትና ጅፍት በየደቂቃው እየፈጸመ ከሚፈጽምባቸው የወሎና የጎንደር አካባቢዎች የጽልመት ድርጅቱን [criminal enterprise] ጠራርጎ ለማስወጣትና ውድመትና ጅፍቱን ለማስቆም አባል የሆነበት አገዛዝ ምን እየሰራ ነው የሚለው ነው።
በኔ እምነት ዳንኤል ክብረት ከገለጸው በላይ ሊገለጽ የሚችል ክፋትና የጥፋት ክብረ ወሰን የተቀዳጁት አረመኔዎቹ ፋሽስት ወያኔዎች በግፍ በወረሯቸው አካባቢዎች በሚያደርሱት ተጨማሪ የዘር ማጥፋት፣ ዘረፋ፣ ውድመትና የጅምላ ፍጅት ተጠያቂው የጽልመቱ ድርጅት ብቻ ሳይሆን የጽልመቱ ድርጅት አባላት ፋሽስት ወያኔዎች ምን አይነት ጨካኝ ፍጡራን እንደሆኑ እያወቀና ያደረሱትን ግፍ በቴሌቭዥን መስኮት ለሕዝብ እያሳየ አንድ ቀንም ቢሆን በግፍ በወረሩት አካባቢ እንዲቆዩና የማይረካውን  የክፋትና የጥፋት ጥማታቸውን እንዲወጡ የሚፈቅድላቸው ዳንኤል ክብረት የሚያገለግለው አገዛዝ ጭምር ነው።
በመሆኑም ካሁን በኋላ ፋሽስት ወያኔዎች በግፍ በወረሯቸው የወሎና የጎንደር አካባቢዎች በሚፈጽሙት ተጨማሪ የዘር ማጥፋት፣ ዘረፋ፣ ውድመትና የጅምላ ፍጅት ተጠያቂዎቹ የድርጊቱ ፈጻሚዎቹ ፋሽስት ወያኔ ብቻ ሳይሆን ዳኔል ክብረት ከስር በተያያዘው የቪዲዮ ንግግሩ የገለጻቸው አረመኔዎች በግፍ በወረሯቸው አካባቢዎች አንድ ቀንም እንኳን ቢሆን እንዲቆዩ የሚፈቅደው ዳንኤል ክብረት አባል የሆነበት አገዛዝ ጭምር ነው።
Filed in: Amharic