>

ሌላኛው የትግራይ ወራሪ ኃይል ሰነድ!  ( ከትግርኛ የተተረጎመ) - ጌታቸው ሽፈራው

ሌላኛው የትግራይ ወራሪ ኃይል ሰነድ! 

ከትግርኛ የተተረጎመ) – ጌታቸው ሽፈራው


የትግራይ ወራሪ ኃይል አባል የሆኑ ቡድኖች ሰሞኑን:_
~የትግራይ ወራሪ ሰራዊትን ትህነግ የእኔ ነው እያለ ነው ብለው ተቃውሞ አሰምተዋል!
~ትግሬዎች ባንዳ እየተባሉ ያለ ፍርድ፣ ያለ ምግብ እየታሰሩ ነው ብለው ተናግረዋል።
~ የስልጣን ሽሚያ ላይ አስተያየት ሰጥተው የትህነግ ደጋፊዎች ጮኸውባቸዋል
~ብዙ ችግሮቻቸውንና ሴራዎቻቸውን በትግርኛ ሲናገሩ ሰንብተዋል። ይሁንና ትህነግን አትንኩ ስለተባለ አሁን በሲቪክ ተቋም ስም መጥተዋል።
ከስር ያለው ፅሁፍ የትግራይ ወራሪ ኃይል ወንጀል የታመነበት ሰነድ ነው። የትግርኛ ትርጉሙ ውስጥ ለውስጥ ሲዘዋወር የነበር ነው። አማርኛ ትርጉሙ ከስር ተያይዟል። ያመናቸውን ወንጀሎች ታገኙበታላችሁ።
…………………………………
ከትግራይ ተቆርቋሪዎች የተሰጠ አስቸኳይ ማሳሰቢያ
እኛ ይህን ሀሳብ ወደ ሕዝብ እንዲደርስ የፈለግን ወገኖች ጀግናው ሰራዊታችን TDF ከምድረ ገፅ ሊያጠፉት እየሰሩ ያሉ ጠላቶችን አሸንፎ ትግራይን ከጠላት ነፃ ባደረገበት ሁኔታ ይህን ድላችንን የሚጎዱ ጥሩ ያልሆኑ አዝማሚያዎች እየታዩ በመሆኑ፣
እነዚህ አዝማሚያዎች በቶሎ ካልተፈቱ የሕዝባችን ቀንደኛ ጠላቶች እድል አግኝተው ካለፈው የባሰ መከራ እንዲያደርሱብን በር እንዳይከፍትላቸው የእርምት  እርምጃ አስፈላጊ በመሆኑ፣
ይሄንን ምክረሃሣብ ለመስጠት ተገደናል።
ይህን ሀሳብ ያነሳን ተጋሩ ከተለያዩ ማሕበረሰብ ክፍሎች የተወጣጣን ስንሆን ሀሳቡን በውጭ ሀገር ለሚኖሩ አንዳንድ ታዋቂ ተጋሩ ግለሰቦች፣ ሰራዊቱን እየመሩ ለሚገኙና ጉዳዩ ላሳሰባቸው አንዳንድ የሰራዊት አባላት እንዲሁም አንዳንድ የሲቪክ ተቋማት መሪዎች አሳይተን ሀሳባቸውንም አካትተንበታል። ይህን ሀሳብ ያቀረብን አካላት ስማችን ያልጠቀሰነው ከሀሳቡ ይልቅ ግለሰብ ፍረጃ ውስጥ እንዳይገባና ሀሳቡ ላይ ትኩረት እንዲደረግ፣ ለጠላት ጥቃት ራሳችንን ላለማጋለጥ በመፈለግ እንደሆነ ከወዲሁ እንዲታወቅ እንወዳለን።
የዚህ ሀሳብ አቅራቢዎች፣ ከሀሳቡ ቀደም ብሎ ሕዝባችንና የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ በዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ እንጠይቃለን።
1) ምከታውን በድል መወጣት የማንኛውም ትግራዊ ቀዳሚ አጀንዳ መሆን ይገባዋል።  ጠላቶቻችን ከየትም ተሰብስበው ሕዝባችን ለማጥፋት በቋመጡበት ወቅት የትኛውም ኃይል ጥቃቅን የፖለቲካ ልዩነቱ ምከታው ላይ ምንም አይነት ጫና እንዳያሳድር በማድረግ ሕዝባችን በምከታው ላይ ትኩረት እንዲያደርግ እንጠይቃለን።
2) የተመረጠው የትግራይ መንግስት ላይ ሁላችንም መስማማት ይገባናል ብለን እናስባለን። ምንም እንኳ ብዙ ክፍተቶች ቢኖሩትም ሕጋዊ ሆነን ጥያቄ ለመጠየቅ እንዲያመቸን የተመረጠው መንግስት ሕጋዊነት ላይ የምናነሳው ጥያቄ ለጠላት መጠቀሚያ እንዳይሆን ሁላችንም አንድ አይነት አቋም ሊኖረን ይገባል።
3) በቀጣዩ ትግራይ ላይ እያንዳንዱ ተጋሩ መወሰን እንዳለበት ማመን ይገባናል። አሁን የገጠመን ችግር እስካሁን ካየነው በአይነቱ የተለየና መጠነ ሰፊ እንደመሆኑ ችግራችን በአንድ ድርጅት የማይፈታ መሆኑ ታውቆ ሁሉም ተሳታፊ የሚሆንበት መንገድ ላይ መተማመን ይገባናል።
ከላይ በተጠቀሱት ዋና ዋና ጉዳዮች መሰረት አድርገን በአሁኑ ወቅት በሕዝባችን ላይ ስጋት የፈጠሩት ጉዳዮችን በመገንዘብ እርምት መደረግ እንዳለባቸው እናምናለን!
እነዚህን መነሻ በማድረግና በቅርብ ጊዚያት እየመጡ ያሉ ክፍተቶችን ሁሉም ተጋሩ ተረባርቦ በጊዜ ማክሰም ስለሚጠበቅበት የሚከተሉትን ጉዳዮች በፍጥነት እንዲታዩ እናሳስባለን፥
1) በድርጅቶች መካከል ያሉ ፉክክሮች ጤናማ ሆነው እንዲቀጥሉ እናሳስባለን። በሰራዊታችንና ሕዝባችን ድል ወደ መቀሌ ከተመለስን በኋላ ህወሃት እየፈፀማቸው ያሉ አንዳንድ ጉዳዮች ወታደራዊ አመራሮችን፣ የድርጅት አባል ሳይሆኑ ትግሉን የተቀላቀሉ ጀግኖችንና የተለያዩ ድርጅቶችን እያስከፉ የምከታ ስራችን ላይ ጥቁር ነጥብ እንደጣሉ ተመልክተናል። የህወሃት አመራሮች በሕዝባችን የተገኘውን ድል ጠቅልለው የድርጅት አድርገዋል የሚሉ ሰፊ ቅሬታዎች ከዚህም ከዛም ይሰማሉ። በተመሳሳይ በድሉ ድርሻ ያላቸውን አካላት በተገቢው መንገድ ምከታውና የትግራይ ቀጣይ ሁኔታ ላይ ያለማሳተፍ ሁኔታዎች እንደታዩ ታዝበናል። እነዚህ ጉዳዮች በአስቸካይ መስተካከል ይኖርባቸዋል ብለን እናምናለን።
2) ከድል መልስ  በተደረጉ ግምገማዎች ንፁሃን ተጋሩ ያለ አግባብ ተፈርጀው ለእስር ተዳርገዋል። ከጊዜያዊ አስተዳደሩና ከአብይ አህመድ ጋር ሰርታችኋል በሚል ያለ ማስረጃ እርምጃ የተወሰደባቸው እንዳሉም ለመረዳት ችለናል። በተለይ መቀሌና አካባቢው በንፁሃን ላይ ያለ አግባብ እርምጃዎች መወሰዳቸውን ለማጣራት ችለናል። ከትግራይ ውጭ የሚኖሩ ተጋሩዎች በግፍ ታሰሩ እያልን በምንጠይቅበት ወቅት ትግራይ ውስጥ በሕዝባችን ላይ ተመሳሳይ ወንጀል መፈፀም ሕዝባችን ምከታው ላይ እንዳያተኩር የሚያደርግ፣ ለጠላቶቻችን እድል የሚሰጥ በመሆኑ በአስቸኳይ ግመገማውና አሰራሩ እንዲከለስ እንጠይቃለን። በተለይ አንዳንድ አካባቢዎች ላይ ያለ አግባብ ባንዳ እየተባሉ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ያለ ምግብ የታሰሩ አካላት በአስቸካይ መፍትሄ እንዲሰጣቸው እንጠይቃለን። ለነፃነት በምንታገልበት በዚህ ወቅት መሰል ሕገወጥ ተግባራት  ከአላማችን የሚያደናቅፉን መሆናቸው በግልፅ መታወቅ አለበት።
3) በትግራይ ተቃዋሚዎችና ገዥው ህወሃት መካከል ያሉት ክፍተቶች በአስቸካይ እንዲታረሙ እንጠይቃለን። ተቃዋሚዎቹ በጫካ ቆይታቸው ህወሃትን በመገምገም ደካማ ነው የሚል አቋም ይዘዋል። በተመሳሳይ ህወሃት ተቃዋሚዎቹን ፅንፈኛ ናቸው እያለ በመፈረጅ ከስራና ከሚዲያ እያገለላቸው እንደሆነ ታዝበናል። ሁለቱም ውስጥ ለውስጥ የራሳቸውን ሀሳብ ለማስረዳት እየሄዱበት ያለው መንገድ አደገኛ እና የሚበትነን መሆኑ መታወቅ አለበት። ተቃዋሚዎች አሁን የተፈጠረውን የአስተዳደር ክፍተት ተጠቅሞ ህወሀትን እንደ ሰይጣን መሣል ማቆም አለባቸው። ህወሃት በበኩሉ ይህን  ድርጊት በአፈና ለማስቆም እየሄደበት ያለው መንገድ ልዩነቱን በይፋ የሚያወጣ፣ ከዚህም በተጨማሪ እስከመገዳደል ሊያደርስ እንደሚችል መታወቅ ይኖርበታል። ስለሆነም በሁሉም ወገን በሰነከ መንገድ ውይይት እንዲያደርጉ እንጠይቃለን። ህወሃት ተቃዋሚዎቹን እንዲያሳትፍ፣ ተቃዋሚዎች ሀሳባቸውን ለሕዝብ እንዳያደርሱ የሚያደርገውን ክልከላ እንዲያቆም እንጠይቃለን።
በተመሳሳይ ተቃዋሚዎች ፍረጃዎችን አቁመው ለምከታ የሚጠቅምና የሕዝብን አንድነት የማይጎዱ ሀሳቦችን እንዲሰነዝሩ እንጠይቃለን።
4) የትግራይ ኃይሎች ተስማምተው ባልሰሩበት ሁኔታ ውጤት የማያመጡና ለሚዲያ ፍጆታ ብቻ የሚደረጉ ውሎች ጥቅማቸው ቢጠና መልካም ነው እንላለን። ለምሳሌ ያህል ከትግራይ ሀይሎች ጋር በጥምረት መሰራት ሳይቻል ከኦነግና የመሳሰሉት ጋር የሚደረግ ግንኙነት ፖለቲካችን እየጎዳው ይገኛል። የኦሮሚያ ክልል መንግስትና አንዳንድ የኦሮሞ ኃይሎች ከኦነግ ጋር እየሰራን ነው ሲባል መቀስቀሻ አድርገው ኦነግ የወያኔ ተላላኪ ነው በሚል መጠነ ሰፊ መቀስቀሻ አድርገው፣ ከአህዳዊ ሀይሎች ጋር በአንድነት እንዲቆሙብን ያደረገ አጀንዳ ሰጥተናል። በተመሳሳይ የቅማንትና የአገው ኃይሎችም በሚዲያ ከሚወራው ውጭ፣ የተደረገላቸውን ድጋፍ ያህል እያገዙ እንዳልሆነ ለመረዳት ችለናል። መንገድ ከመጠቆም ውጭ ጠንካራ እንቅስቃሴ ባለማድረጋቸው ሰራዊታችን ዋጋ የከፈለበት ሁኔታ አለ። በመሆኑም ወደ ውጭ ከማየታችን በፊት ውስጣችን ማጠንከርና ሌላውን እንደሁኔታው ማስኬድ ይኖርብናል እንላለን።
5) አንዳንድ የፕሮፖጋንዳ አካሄዶች እርማት ሊደረግባቸው ይገባል። ለምሳሌ ሕዝባችን በርሃብ እየተሰቃየ ባለበት ሁኔታ የትግራይ  ሕዝብ ለሰራዊቱ ደጀን ሆኖ ስንቅ እያዘጋጀና ገንዘብ እያወጣ እያገዘ ነው የሚለው አጥፊ የሆነ አካሄድ ነው። በአንድ ጎን ሕዝባችን የሚቀምሰው የለውም እያልን በሌላ በኩል ደግሞ ለሰራዊቱ እገዛ አደረገ ማለት ከእኛ የማይጠበቅ የሚዲያ አካሄድ በመሆኑ በቶሎ መታረም ይኖርበታል። በተጨማሪም ውሸታም የሚያስብሉን አንዳንድ የሚዲያ አሰራሮች እርምት ሊወሰድባቸው ይገባል።
6) ጀግናው ሰራዊታችን በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች እንደገና ክለሳ ያስፈልጋቸዋል። በሚዲያ ብንክድም አንዳንድ ስህተቶች እየተሰሩ ስማችን እየጠፋ ይገኛል። ለምሳሌ ዓለም አቀፍ ማሕበረሰቡ ጫና እንዳያደርግ በሞዲያ ከሕዝብ ጎን ቆመን ነፃ እናወጣዋለን እያልን ተቋማትን መዝረፍና ማውደም በራሳችን ላይ እንደመተኮስ ነው። ይህ ጉዳይ ጠላት የሚለው ብቻ ሳይሆን የተረጋገጠ ነው። አንዳንድ አካባቢዎች ላይ ሰው በገደሉ የሰራዊታችን አባላት ላይም ሕጋዊ እርምት እርምጃ ቢወሰድብ ብዙ ቦታዎች ላይ የተፈፀሙ ጉዳዮች እንድንጠላ አድርገውናል። የትምክት ሚዲያው ተጠራርቶ ትግራዊ የሊጥ ሌባ እያለ የሚዘምተው በእኛም ስህተት የመጣ መሆኑ ታምኖ እርምት መደረግ አለበት። ሕዝባችን ክርስትያን ሕዝብ እንደመሆኑ ከቄሶች፣ ከቤተ ክስርትያን ወዘተ ላይ ተደረጉ የተባሉ ጉዳዮች ተመርምረው እውነት ሆነው ከተገኙ ማስተካከያ ተወስዶ ለሕዝብ ማሳየት ይጠበቅብናል። ሙስሊሞች ወዘተ በመሳሰሉ የማሕበረሰብ ክፍሎች ላይ ተፈፀሙ የሚባሉትም ጠላት ኃይል እንዲያሰባስብ የሚያግዘው ስለሆነ ጥንቃቄ መደረግ አለበት።
7) ከሰራዊት ምልመላ ጋር በተያያዘ የሚታዩ አንዳንድ ክፍተቶች በአስቸኳይ እንዲፈቱ እንጠይቃለን።  በግዳጅና ሕዝብን እርዳታ አታገኝም እያሉ ከማስፈራራት የሕልውናው ጉዳይ እንደሆነና በልጆቹ ነፃ መውጣት እንዳለበት ማስረዳት ይገባል።  የትግራይ እናቶች ልጆቻቸውን መርቀው ሲልኩ መስዋዕት ሆነው ቀጣዩዋ ትግራይ ሰላም እንድትሆን አውቀው ነው። ስለሆነም የተወሰው የሰራዊት አባላት ለወላጆቻቸው በአግባቡ መገለፅ አለባቸው። የተሰው የሰራዊት አባላት በጅምላ የተቀበሩበት፣ ወንዝ ላይ የተጣሉበት አጋጣሚ መኖሩ መረጃዎች አሉ። በክብር ማረፍ ያለባቸውን ጀግኖች በዚህ ሁኔታ ያዋረደ ካለ ተመርምሮ ለቀጣይ የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ እንጠይቀለን።
8/ ትግላችን ፍትሐዊ፣ ለነገ ዲሞክራሲ መግቢያ በር ነው።  ይሁንና በዚህ የሞት ሽረት የምከታ ወቅት አንዳንድ ከሕዝባችን ስሪት ያፈነገጡ አካሄዶች ይስተዋላሉ። ወደ መቀሌ ከተመለስን በኋላ በአንዳንድ አካባቢዎች የሴቶች መደፈር ሪፖርት ተደርጓል። የትግራይ እናቶች በጠላት ተደፈሩብን እያልን እየጮህን ጠላትን ጠራርገን ካስወጣን በኋላ የእርዳታ ድርጅቶች ይህን ወሬ ሲሰሙ ጩኸታችን ከንቱ እንደሚቀር ግልፅ ነው።  በሰራዊታችን እጅ ካሉ አካባቢዎች እያስመለስናቸው ያሉ ቁሳቁስና ገንዘብም ለተራበው ሕዝብና ለቀጣይ ትግል እርሾ እንዳይውል በካድሬዎችና ቤተሰቦቻቸው የሚጠቀሙበት አጋጣሚ እንዳለ መረጃዎች አሉ። ከጠላት ያመጣነው ንብረትና ከውጭ የሚገኝ እርዳታ ለሕዝብ መዋል ሲገባው ለካድሬና ቤተሰብ የሚውልበት ሁኔታ ከአሁኑ መቆም አለበት።
9)  ጠላቶቻችን በትግራይ ላይ ሁሉን አቀፍ ጥቃት በፈፀሙ ወቅት ዝግጅት ባለመደረጉ ብዙ ጉዳቶች ደርሰዋል። ትልቁ የውድቀታችን ምንጭ አዲስ አበባ እንገባለን የሚል አማራጭ ብቻ ተይዞ ያ ሁሉ ችግር ሲደርስ ያለ ዝግጅት መረጃዎችን አዝረክርኮ ወደ ጫካ መግባቱ ብዙ ጉዳት አድርሶብናል። በእስር ላይ ያሉትና በተለያዩ ክልሎች በትግል ላይ የነበሩ የትግራይ ጓዶች የተጠቁት ህወሃት ባንጠባጠበቅ መረጃ ነው። ሰሞኑን እንኳን በጠላት እንደ አጀንዳ የሚዘዋወረው ሰነድ በዚሁ መልክ የተገኘ ነው። የአንድን ሕዝብ ስትራቴጅያዊ አካሄድ የሚተነብይ፣ የትግል ሚስጥሮችን የያዙ ሰነዶች በጠላት እጅ ገብተው ጉዳት እያደረሱ ነው። በዚህ ጉዳይ ጥልቅ ግምገማ ተደርጎ ለቀጣይ አንደኛው የምከታ ዘርፍ መሆን ይገባዋል።
11) በዚህ ወቅት ከትግራይ ጋር የቆሙ የውጭ ወዳጆቻችን አሉ። ሆኖም የውጮቹን ማሳመን የምንችለው በራሳችን አቅም ነው። ከዚህ ውጭ ከመጠን በላይ በውጭ አካላት ማመን ጉዳት ይኖረዋል። ለምሳሌ ያህል ትግራይ ውስጥ የሚሰሩ የእርዳታ ድርጅቶች ለሕዝባችን እየጠቀሙ፣ ለድርጅቶቻችን ጋር እየተናበቡ ቢሆንም ጠላት ይህን አጥንቶ የቀረባቸው የውጭ ግለሰቦች መኖራቸውን መረጃዎች አሉ። አንዳንድ የውጭ ሀገር ግለሰቦች ከትግራይ መንግስትና የትግራይ መከላከያ ኃይል ጋር ባላቸው ቅርበት የሚያገኙትን መረጃ ለጠላት እያደረሱ መሆኑን የኤምባሲ ምንጮች ጠቁመዋል። ስለሆነም በራሳችን አቅም ተማምነን፣ አጋሮቻችንን በጥንቃቄ እንድንመለከት እንመክራለን።
12) ሁሉም ተጋሩ አንድነቱን እንዲያጠናክር እንጠይቃለን። በተለይ ከድልና ስልጣን ሽሚያ ራስን በማራቅ ትኩረቱ የጋራ ጉዳይ ላይ እንዲሆን ማሳሰብ እንወዳለን። በውጭ የምትኖሩ ወገኖቻችን ከጀግናው ሰራዊታችን ባልተለየ የውጩን ዲፕሎማሲ ይዛችሁ፣ እየተሰደባችሁ ለሕዝባችሁ ፀንታችሁ እንደቆማችሁት ሁሉ፣ ድሉ የእናንተም ነውና በድካማችሁ የተገኘውን ድል የተወሰኑ አካላት እንጠቅልል ሲሉ ዳር ባለመቆም ለቀጣይ የትግራይ እጣ የበኩላችሁን እንድታበረክቱ ጥሪ እናቀርባለን። ሚዲያዎች የውስጥ ጉዳዮቻችን ላይ ለትግራይ ሕዝብና ጥቅም ብቻ በመወገን ከማንኛውም ወገን ላይ ባለመወገን ድርሻችሁን እንድትወጡ ጥሪ እናቀርባለን።
ትግራይ ታሸንፋለች!
10/01/2014
Filed in: Amharic