>

አብይ አህመድ እስክንድር ነጋን ለምን ፈራው!? (ሰለሞን አለምነህ)

አብይ አህመድ እስክንድር ነጋን ለምን ፈራው!?

ሰለሞን አለምነህ

*… አብይ አህመድ እስክንድርን ለምን ፈራዉ ብለን ስንጠይቅ የሚከተሉትን አንኳር ነጥቦች እናገኛለን:-
በተለይ በፓለቲካ ተሳትፎዉ ትልቅ ተፅዕኖ ማሳረፍ የሚችለዉ በኢትዮጲያዊነቱ የማይደራደረዉ ብዙሀኑ ዲያስፓራ የእስክንድር ደጋፊ ስለሆነ በእስክንድር አንቀሳቃሽነት ለሀገሩና ለህዝቡ በንቃት መሳተፍ ይችላል ፤ትልቅ የፓለቲካ ሀይልም ሆኖ ይወጣል ማለት ነዉ። በሀገር ዉስጥ ያለዉ የከተማ ህዝብ በተለይም አዲስአበቤዉ በከፍተኛ ሁኔታ እስክንድርን ይደግፋል ፤ ስለሆነም በአዲስአበባና በትላልቅ ከተሞች የሚገኘዉ (እስከዛሬ ሆነ ተብሎ ፓለቲካዊ ዉክልና እንዳይኖረዉ የተደረገ ህዝብ) ይህ ሰፊ እምቅ የፓለቲካ አቅም ያለዉ ህዝብ በእስክንድር የማይነቃነቅ የአላማ ፅናትና ቁርጠኝነት ከተመራ የኢትዮጵያ የፓለቲካ ሚዛን ያለጥርጥር በእጁ መጨበጥ ይችላል ማለት ነዉ።
ከዚህ በተጨማሪም ታላቁ እስክንድር ነጋ በአለምአቀፍ ማህበረሰብ አይን ያለዉ ተቀባይነትና ክብር ከፍተኛ ነዉ። (ከ10 ያላነሱ አለምአቀፍ ሽልማቶች ያሉት ነዉ) በመሆኑም ይህ የእስክንድር ግዙፍ አለምአቀፍ ገፅታ በዙሪያዉ ካለዉ ህዝብ እምቅ ፓለቲካ አቅም ጋር ተዳምሮ ሊፈጥር የሚችለዉ ባላንስ እነ አብይ አህመድ በፀሎት እንኳን ሊደርሱበት የማይችሉት እጅግ ግዙፍ ነዉ።እስክንድር ማለት በአለም ዳርቻ ያለዉን ሰፊዉን ህዝብ በአንድ ላይ አንቀሳቅሶ እጅግ ግዙፍ የፓለቲካ ሀይል አድርጎ የሚያስነሳዉና ስልጣን እንዲጨብጥ የሚያስችለዉ Master Key የሚባል አይነት መሪ ነዉ!!!
አብይ አህመድ ይህንን ሁሉ ጠንቅቆ ስለሚያዉቅ ነበር ከእስክንድር ጋር በቀጥታ ጦርነት እንገባለን ለማለት የተገደደዉ።
ስለሆነም ሰፊዉ ህዝብ መገንዘብ ያለበት ነገር ቢኖር እስክንድር ነጋን ማስፈታት ማለት ዋጋዉ ሀገርን ከመታደግም በላይ መሆኑን ነዉ!!!
ድል_ለዲሞክራሲ
Filed in: Amharic