>

ቅሬታ !..... ይድረስ ለኢትዮ ሪፈረንስ?! (ዘምሳሌ)

ቅሬታ ይድረስ ለኢትዮ-  ሪፈረንስ

ዘምሳሌ


ጉዳዩ ‘ምሬት የባሰ ቀን’ በሚል የተሰራ አጭር
ወቅታዊ መልዕክት የገፁን ተነባቢነት በማሰብ
ለአንባቢያን የተላከ ግጥም ነበር

ምነዋ ወዳጄ
አስቀረኸኝ ከእጄ
አንተኑ አምኜ
እንድትሆነኝ ቀኜ
ደብዳቤ ሰድጄ
መልዕክቴን በላኸው
ከገፅህ አስቀረኸው
ብሶቴን ከትቤ
ብዕሬን አርጥቤ
ብልክ ካንተ አስቤ
ለአብይ ደብዳቤ
ወንጀሉን ዘግቤ
ከምን አደረስከው
ለንባብ በገፅህ ሳትሰቅል አስቀረኸው!

ፀሀፊ አዎን አለ በነፃነት  ያለ
ፀሀፊ አዎን አለ በእስርቤት ያለ
ዳሩ አታሚው ነው የተደላደለ
ዳሩ አንባቢው ነው ብዕርን  የገደለ

የብስጭት እርሳስ ስለው አይቀርፁትም
ከወዳጁ ወረቀት ሰምጦ እንዳይሰጥም
መልካም የስራ ዘመን

ግልባጭ ለስነ ቅሬታ ልቦች ይሁን

zemessalee@gmail.com

Filed in: Amharic