>
5:13 pm - Tuesday April 19, 5577

ግኖቹ ግን ቢያንስ መሳሪያ አቅርቡልን እያሉ ይማጸናሉ ... ግና ሰሚ የለም....!!! (ጎበዜ ሲሳይ )

ጀግኖቹ ግን ቢያንስ መሳሪያ አቅርቡልን እያሉ ይማጸናሉ … ግና ሰሚ የለም….!!!
የጎበዜ ሲሳይ 

*.... መንግስት ተብዬዉ ሸሽቶ አርሶ አደሩ እራሱን በጎበዝ አለቃ አደራጅቶ ተጋድሎ ያደርጋል…!
 
  *.... የኦህዴድ መከላከያ ደግሞ ቁጭ ብሎ ጥሩን ይፍቃል!
  *.... ወደ መሃል መሳብ በሚሉት ቅንጦታዊ ስትራቴጂ ይራቀርቃሉ!
ከዞብል እስከ ቆቦ ግርጌ ገደመዩ ፣ ዲቢን እና ጎሊናን ተሻግሬ ወርቄን አየሁት። የሕወሓት ታጣቂዎች የተቆጣጠሯቸውን ቀበሌዎች ሳይቀር ገብቼ ተመለከትኩ።
የራያ ወጣት ሸፍቷል። ሽማግሌ ሳይቀር ታጥቋል። ገበሬው አዝመራ መሰብሰቡን ትቶ  ምሽግ ውስጥ ነው። በየቀኑ ውጊያ አለ።
እገሌ አምስት ክላሽን ኮቭ ማረከ ፣ እገሌ አስር ገደለ ሆኗል ወሬው። (በምርኮ እና ግዳይ በጣለ ሆኗል ፉክክሩ)
የሕወሓት ታጣቂዎች በየቀበሌው የተከፈተባቸውን ውጊያ ለመመከት ከቆቦ ወልዲያ ዋናውን መስመር ይዘው በተሽከርካሪ ኃይል ወዲያና ወዲህ ያመላልሳሉ።
በገበሬው ጦር ጥቃት ሲደርስባቸው ከተማ ውስጥ  ያለን ነዋሪ በጅምላ ይገድላሉ። (ጳጉሜ ፬ ቆቦ ከተማ የተፈጠረው ይሄው ነው) በተመሳሳይ የወርቄን ግንባር ለመዘገብ በቦታው በነበርኩበት ወቅት 34 የሕወሓት ታጣቂዎች ሲገደሉ ወዲያውኑ ወደዪ  እና አፉፍ የተባሉ ቀበሌዎችን ቤት ለቤት እየዞሩ ማቃጠላቸውን በቦታው ተገኝቼ ተመልክቻለሁ።
ከወርቄ እስከ ዞብል ከአፋፍ እስከ ጎብዬ እና ሮቢት ድረስ ገበሬው በጎበዝ አለቃ   በአጭር ጊዜ ውስጥ መደራጀቱ አስገርሞኛል።
የራያን ትግል  እየመራ ያለው  የወርቄው በካሪስ ጎቤ ሲሆን 22 ቀበሌውችን  በማስተባበር ሸሽቶ የወጣውን አርሶ አደር አደራጅቷል።በየቀበሌው የተደራጀው ገበሬው ተመሳሳይ የሆነ ጥያቄ አለው።
1ኛ መንግስት ነፃ በሆነው የአፋር ክልል በኩል ትጥቅ እንዲያቀርብላቸው።
2ኛ ቁስለኞች በአፋር ክልል በኩል ወጥተው በቶሎ  ህክምና እንዲያገኙ
3ኛ የምግብ አቅርቦት የሚሉ ናቸው።
በእርግጥም በራያ ቆቦ በእስከ ምስራቅ የአፋር ክልል በኩል ነፃ በመሆኑ መንግስት ማንኛውንም ድጋፍ ላድርግ ቢል እንቅፋት የለበትም።
Filed in: Amharic