>

በየእለቱ የሚጎርፉት ተፈናቃዮች  በረሀብ አለጋ የሚጠበሱባት ወሎ... ?!? (ጋዜጠኛ መሀመድ)

በየእለቱ የሚጎርፉት ተፈናቃዮች  በረሀብ አለጋ የሚጠበሱባት ወሎ… ?!?

ጋዜጠኛ መሀመድ

ኮምቦልቻ ደሴ ሀይቅ ውርጌሳ ደላንታ የረገጥኳቸው ቦታዎች ሁሉ ጦርነቱን ሸሽተው በመጡ ተፈናቃዮች ተጥለቅልቀዋል።
ዛሬም ድረስ ከራያ ሀብሩ መርሳ ጎብዬ ወልደያ እና ሌሎች ቦታዎች በእግራቸው የሚጓዙ ተፈናቃዮች ስፍር ቁጥር የላቸውም
ደሴ ከተማ ውስጥ ብቻ 24 ትምህርት ቤቶች ተፈናቃዮችን ተቀብለዋል በየዘመድ ቤት የተጠጉትን እና ዘመድም ሆነ መጠለያ አጥተው በየመንገድ ዳር የወደቁትንማ ማን ቆጥሯቸው።
  ደሴ ከተማ ስትገቡ በየመንገዱ ምግብ ግዙልኝ ብለው ልብሳችሁን የሚጎትቱ ህፃናትን መለመን እንኳን አቅቷቸው አይን አይናችሁን የሚያዩ አዛውንቶችን ማየት የተለመደ ሆኗል።
ሰብአዊ እርዳታው ከብዙ በጎ ፈቃደኞች እርብርብ ቢደረግበትም ከተፈናቃዩ ቁጥር እና ፍላጎት አንፃር ጠብ የሚል ነገር የለውም። የሚቃመሷትም ከተፈናቃይ ጉሮሮ ላይ ቀምተው ለመክበር ከሚሯሯጡ ስግብግብ አመራሮች ከተረፈ ነው።
   በህዋሃት ታጣቂዎች የደረሰባቸው ግፍ እና በደል ለሰሚውም ያማል አይኗ እያየ ልጇ የተደፈረችባትን እናት አባታቸው ሲገደል ያዩ ህፃናትን  ሆዱን በሳንጃ ተተርትሮ በተአምር የተረፈ ወጣት ዘጠኝ ሆነው ደፍረዋቸው ጓደኛዋ ስትሞት እሷ በተአምር የተረፈች ሴት የባሏ እሬሳ ለጅብ ሲሰጥ ያየችን ሴት ከማየት ከመስማት በላይ ምን  ህመም አለ?
  መንግስት ስለ ወሎ ምን እያሰበ ነው? ምን እያደረገ ነው? በሌሎች ግምባሮች የተደረገው ርብርብስ ወሎ ላይ ሲደርስ ምን እጁን ያዘው? ወልደያን ጨምሮ በተደጋጋሚ ነፃ የተደረጉ የወሎ አከባቢዎች ተመልሰው በቁጥጥር ውለዋል ህዝቡ ተበትኗል መንግስት ዝም ጭጭ ሆኗል።
  የምትፈልጉት የጥፋት ማካካሻ እንደሆነ ወሎ ላይ ከፈለጋችሁት በላይ የግፍ ፅዋወን ሞልቶ ፈሷል።
 በናንተው ሴራ ጓደኞቹን  ወንድሞቹን ቀብሮ ቤት ንብረቱን ቀየውን ተነጥቆ እንዲወጣ ከተደረገ በኋላ ከፈለገ  ሄዶ አይዘምትም  በሚል መመፃደቅ የእለት ጉርሱን ነፍጋችሁ አንገቱን ያስደፋችሁት  የወሎ ወጣት ዘመቻው ወዴት እንደሚሆን ብታስቡበት ጥሩ ነው።
Filed in: Amharic