>

ይድረስ ለእስክንድር ነጋ...!!!   (ከአበበ በለው)

ይድረስ ለእስክንድር ነጋ…!!!

      ከአበበ በለው

የብሄር ህገ መንግስት ዜግነትን ዋጋ አሳጥቶ መብትንም በኢትዮጵያዊነት ሳይሆን በብሄር ተወስኖ ፡ ኢትዮጵያዊ ነኝ እያልን ፡ኢትዮጵያ ውስጥ የማንኖርበት መጤ የምንባልበት ክልል ተከልሎ ፡ ዜግነት ለፓስፖርት እንጅ አገር ውስጥ ከብሄር በታች ሆኖ ፡ይህን ስንታገል ከነበርነው ፡የታገልንለት አንዱም ሳይሻሻል ፡ዛሬም የነበረው ጭራሽ ብሶ በገነነበት ሰዓት ፡የትግል ጓደኞችህ ፡በዛው ህገመንግስት ባለስልጣን ሆነዋል ፡ይውደሙ ሲሏቸው ከነበሩት የኢሃዴግ ባለስልጣናት ጋር የስራ እና የስልጣን ባልደረባ ሆነዋል፡የተቀየረ ባይኖርም ከትግል ጓደኞችህ ቱባ ቱባዎቹ ተቀይረዋል። የሚገርመው የትናንቱ ኢሃዲግ  የዛሬው የብልፅግና  ባለስልጣናት ዋሽንግተን ዲሲ ለመዝናናት ሲመጡ በየሞሉ ገዳዮች እያለ ያሳድዳቸው የነበረው ግብረሃይል ዛሬ ኤርፖርት አበባ ይዞ ይጠብቃቸዋል ፡የታገልንለት ሳይቀየር ታጋዮች ደክሞቸው ተቀይረዋል ፡፡ የገረመኝ አንተ እስረኛ እነሱ ባለ ስልጣን መሆናቸው ነው፡፡እስኬው እግዚአብሄር ያስፈታህ
Filed in: Amharic