>

ይድረሰ ለኢትዮጵያዊያን:- ታማኝ እንዴት ይጥፋ?! (ዘምሳሌ)

ይድረሰ ለኢትዮጵያዊያን

ታማኝ እንዴት ይጥፋ?!


ታማኝ እንዴት ይጥፋ የተሻለ ዜጋ
ሚወግን ለህዝቡ ለሰላም ሚተጋ
ሀገሪቱ እንዳትፈርስ ሰው ሚያረጋጋ
ቅን ልቦና ያለው ከእውነት የተጠጋ

ታማኝ እንዴት ይጥፋ መልካም ህሊና ያለው
በህዝቡ ሚታመን ሕዝብ ሚወክለው
ስራው ሚመሰክር  ለስልጣን ማይጓጓው
ለሀገር ለወገን ታግሎ ሚያታግል ሰው

ታማኝ እንዴት ይጥፋ ዜጎች ተስፋ እያጡ
መከራና እምባ ዘወትር እያማጡ
ባለስልጣናቱ ዋሽተው ሲቀመጡ
ለጨቋኞች አድረው ፓርላማ ሲቀልጡ
ገና መቼ አልቆ የኢትዮጵያወያን ምጡ

ታማኝ  እንዴት ይጥፋ ስንት ንፁሃን አልቆ
ሀሳቡ የሚያሸንፍ ልዕልናው ልቆ
ለኢትዮጵያ የቆመ ዘረኞችን ንቆ
መፍትሔ ሚፈጥር  ህገ ደምብ  አርቅቆ
ኢትዮጵያን የሚያድን ከአጥፊዎቿ ነጥቆ

ታማኝ እንዴት ይጥፋ ዘረኛ ያልሆነ
በሀገርና  ህዝብ ፈፅሞ የታመነ
ሕዝብን የማይሰድብ  ለእውነት የጨከነ
ሀይማኖት ሚየከብር ለኢትዮጵያ የወገነ

ታማኝ እንዴት ይጥፋ የሚለን በርትቶ
እውነት ነፃ ያወጣል ሀሰትን እረቶ
ያለማወቅ ድቅድቅ ጨለማን አጥፍቶ
ወደተሻለ እድገት የሚያደርሰን ከቶ

በጎ እንዴት ይጥፋ ባለንበት ዘመን
ለሀገር የቆመ በህዝቡ ሚታመን
በሸፍጥ ያልታጀለ  ሀገርን የሚያድን
በከንቱ ፉከራ መድረክ ላይ ማይጀግን
ቆራጥ መሪ የሆነ  የሚወድ ኢትዮጵያን
ታማኝ እንዴት ይጥፋ…

ዘምሳሌ

Filed in: Amharic