>

ከወዲያ ስድብ እና ከስራ የማፈንቀል ዘመቻ   ከወዲህ የድጋፍ ፊርማ የጎረፈላት ልበ ሙሉዋ ጋዜጠኛ....!!!

ከወዲያ ስድብ እና ከስራ የማፈንቀል ዘመቻ 
 ከወዲህ የድጋፍ ፊርማ የጎረፈላት ልበ ሙሉዋ ጋዜጠኛ….!!!

ኢትዮጽያዊቷ የትግራይ ተወላጅ  የCBS News ጋዜጠኛ ሄርሜላ አረጋዊ ፣ ሚዛናዊ በሆነ የሙያ ስነምግባር ፣ የዘር ፓለቲካን ወዲያ ጥላ ትህነግ ላይ ባቀረበችዉ ጠንከር ያለ የትችት ዘገባ፣ከወዲያ ስድብ እና ከስራ የማፈንቀል ዘመቻ እንዲሁም ዛቻን በየቀኑ እያስተናገደች ሲሆን  : ከወዲህ ደግሞ ይህ ነዉ የማይባል የድጋፍ ፊርማ እየተሰባሰበላት ይገኛል።
ጋዜጠኛዋ በልበ ሙሉነት በእንግሊዘኛ ቋንቋ በቪዲዮ ግልጽ አድርጋ ያስቀመጠችዉ መልእክት በዚህ መልኩ ተተርጉሟል ።
“እንደ ትግራውያን ማህበራዊ አንቂዎች አይነት አሸማቃቂና ተሳዳቢ የለም። ድንቅ የሚለኝ ነገር  ፤ እውን ውሃ የሚቋጥር እውነት አላችሁ?  እውነቴን ነው አንዳች በቂ  ምክንያት የላችሁም። የምንነዛው ውሸት የት እንደሚያደርሰን እናያለን። አሁን ባለው ሁኔታ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ሕዝብ የቅዠታችሁ ሰለባ ሆኖ በቅርቃር ውስጥ ቢገኝም እናንተ ግን በሞቀ የዲያስፖራ ወንበራችሁ ተቀምጣችሁ አሁንም ደንታችሁ አይደለም። ይባስ ብላችሁ ስራችሁ ጦርነትን ማቀጣጠል ሆኖል። እርዳታ ለጦርነት ሲውል ግድ የላችሁም፣ ሺዎችና ሚሊዮኖች  ሲሞቱና ሲረግፉም ግድ አይሰጣችሁም፣ እንዲያውም እሱኑ ታበረታታላችሁ እናም ምንም አሳማኝ ምክንያት የላችሁም።ለዚያም ነው  ቁጣችሁን ወደኔ ያዞራችሁት። አናንተ አቅላችሁን ስታችሁ ብታብዱም እኔ እንደሁ ለሚሊዮኖች ድምጽ መሆኔን እቀጥላለሁ ለከንቱ ጩኸታችሁም ደንታ የለኝም። ወደ ኋላ የሚመልሰኝም ነገር የለም። መቼስ ለእውነት ደንታ የላችሁም። ይሁንና፤
 ለምናገረው ነገር  አይከፈለኝም ።የምናገረውም ለማንም ብዬ አልናገርም የማስበውንም እንደዚያው።  ብታምኑም ባታምኑም ። ሴት የራሷ የሆነ አስተሳሰብ ሊኖራት ይችላል። አንዲት ከትግራይ የምትመዘዝ ሴት ያውም ጋዜጠኛ  የራሷ የሆነ ሃሳብ አላት። አይገርምም!? ዋው¡¡  ይኼ የእብድ አስተሳሳሰብ ነው።አውቃለሁ እንዲህ ያለ አቋም እንደ ዱብዳ ያስደነግጣል። ምክንያቱም አንድ አይነት ንግግር የማይናገር  የእናንተን ሃሳብ የማይደግፍና የተለየ ሃሳብ ያለውን ሰው ባንዳ የሚል ስም እየለጠፋችሁ የምታሸማቅቁበት መርዛማ ባህል አላችሁ። ይኼ በእውነት ሲበዛ በሽታ ነው በጣም የታመመ ባህል።”
ደጁ ከመርካቶ
Filed in: Amharic