>
5:31 pm - Saturday November 12, 9307

ለአዲስ የእርድ ምዕራፍ ብልጽግናን የመረጣችሁ ዘራችሁን እያጠፋላችሁ ነው እንኳን ደስ አላችሁ...!!!! (ጌታቸው ሽፈራው)

ለአዲስ የእርድ ምዕራፍ ብልጽግናን የመረጣችሁ ዘራችሁን እያጠፋላችሁ ነው እንኳን ደስ አላችሁ…!!!!
ጌታቸው ሽፈራው

*… ብልፅግናን የመረጣችሁ ዐማሮች እንኳን ደስስ አላችሁ። በቅቤ ምላሱ በዐቢይ ፍቅር የወደቃችሁ እንኳን ደስስ ያላችሁ። ልፋታችሁ መሬት አልወደቀም። በከንቱም አልቀረም። ይኸው በአዲስ ምዕራፍ የመረጣችሁት ብልጽግና ዘራችሁን እያጠፋላችሁ ነው። በድጋሚ እንኳን ደስ ያላችሁ። ለእዝን የሚሆን ስንዴ በገፍ እየተመረተላችሁ ስለሆነ ብዙም አትስጉ። 
…እሱ ዐቢይም ሆነ እነርሱ ኦህዴድ/ኦነግ/በአዴኖች ምንም አላጠፉም። ቃላቸውን ጠብቀው ሥራቸውን በሚገባ እየሠሩ ነው። እንሰብረዋለን ያሉትን ዐማራ “በአዲስ ምዕራፍ” ወገብ ዛላውን እያነከቱ እየሰበሩት ነው። እናጠፋዋለን ያሉትንም ኦርቶዶክስነት ድራሽ አባቱን እያጠፉት ነው። እናስ እነርሱ ምን አጠፉ? መልሱ ምንም፣ ምንም አላጠፉም ነው። እነሱ ምንም ከቃላቸው ዝንፍ ያደረጉት ነገር የለም። በትክክል በዕቅዳቸው መሠረት እንገነባታለን ያሏትን ከዐማራና ከኦርቶዶክስነት የጸዳች ኦሮሞን የመሰለች ኢትዮጵያን እየገነቡም… እየፈጠሩም ነው። ስለዚህ ወቀሳም ስድብም አይገባቸውም። በራስህ እዘን። በመረጥከው መሪ ላይ አረደን ብሎ አፍ መክፈት በእውነት ነውር ነው። ምንአለበት ቢያርድ ቢያሳርድ? የምን ምቀኝነት ነው? ቢያዝን፣ ባንዲራ ዝቅ ቢያደርግ ምንአለበት አይባልም። ነውር ነው። እንዲህ ያለ ድፍረት የድፍረት ቃል የምትናገሩ ዐማሮችም ተጠንቀቁ። አደብም ግዙ። በመረጣችሁት መሪ ላይ እጃችሁን አታንሡ። አፋችሁንም አትክፈቱ።
ሁሌም ህዝብ ድረሱልኝ ይላል ብልጽግና የሚደርሰው ግን  ዜናውን ለማፈን ነው
በተፃፈም ባልተፃፈም ሕገ መንግስት፣ የዜጎችን በሕይወት የመኖር፣ የአካል ደሕንነት ማስጠበቅ ግዴታ ነው። አንድ አገር የሚፅፈው፣ የሚጥሰው ሳይሆን ቋሚ ዓለም አቀፍ ሕግ ነው። ወለጋ ላይ እየተገረሰሰ ያለው ይህ ዓለም አቀፍ ሕግ ነው! አንድ ጊዜ ብቻ አይደለም! መአት ጊዜ ነው!
የክልሉም የፌደራል መንግስትም ንፁሃን አማራዎች “ድረሱልን” ሲሉ እየደረሱ አይደለም።  መፍትሄው አማራዎች ራሳቸውን እንዲከላከሉ ማድረግ ነው። ማስታጠቅ ነው።
የኦሮሚያ ክልል መንግስት በርካታ ፓርኮች አሉ። ፓርኮቹን በበርካታ ጠባቂ ያስጠብቃል። የዱር እንስሳትን የሚያስጠብቅ መንግስት ግን፣ አማራዎች ድረሱልኝ እያሉ ሲያልቁ ጥበቃ እያደረገ አይደለም። የዱር እንሰሳት “ድረሱልን” የሚሉ ቢሆን ኖሮ የክልሉም የፌደራል መንግስትም ሮጦ ይደርሳል።  ንፁሃን አማራዎች ድረሱልን ሲሉ ግን የሚጨንቀው አልተገኘም። መፍትሔው ንፁሃን አማራዎች  ራሳቸውን እንዲከላከሉ ማስታጠቅ ነው!
ትህነግና ኦነግ በይፋ ግንባር ፈጥረዋል። ትህነግ በይፋ የከፈተብን ግንባር ላይ ከተረባረብን በኦነግ በኩል የከፈተው ግንባር ላይ ለምንድን ነው የማንረባረበው? ትህነግም ንፁሃንን ይጨፈጭፋል፣ ኦነግም ንፁሃንን ይጨፈጭፋል። በይፋ የተከፈተ ጦርነት አይደበቅም። ንፁሃን አማራዎች ታጥቀው ራሳቸውን እንዲከላከሉ ከማድረግ በተጨማሪ  ከኦሮሚያ ክልል ካልቻለ እንደ መተከሉ የሌሎች ክልሎች ልዩ ኃይሎችም መግባት አለባቸው።
ለፀረ ትህነግ ዘመቻው በአገር ደረጃ ወጣቶች እየሰለጠኑ ነው። የሁለት ሳምንትም የወርም ስልጠና እየወሰዱ ነው። ትህነግ በኦነግ በኩል ለከፈተው ዘመቻም የአካባቢው ወጣት በተለይ የሚጠቃው አማራና ነገ የሚጠቃው ሌላው ኢትዮጵያዊ መሰልጠን አለበት።
የወለጋው ጭፍጨፋ የጦርነቱ አካል ነው! በንፁሃን ላይ ጦርነት ተከፍቶ ደግሞ ዝምታ አይመረጥም። እየተፈፀመ ያለው ጭፍጨፋ ነው። ድረሱልኝ እየተባለ፣ ጭፍጨፋ እየተካሄደ እንዴት ዝም ይባላል?
የደስታ መግለጫ
ብልፅግናን የመረጣችሁ ዐማሮች እንኳን ደስስ አላችሁ። በቅቤ ምላሱ በዐቢይ ፍቅር የወደቃችሁ እንኳን ደስስ ያላችሁ። ልፋታችሁ መሬት አልወደቀም። በከንቱም አልቀረም። ይኸው በአዲስ ምዕራፍ የመረጣችሁት ብልጽግና ዘራችሁን እያጠፋላችሁ ነው። በድጋሚ እንኳን ደስ ያላችሁ። ለእዝን የሚሆን ስንዴ በገፍ እየተመረተላችሁ ስለሆነ ብዙም አትስጉ።
… እህሉ ፍሬ ያፍራ !!
… የተገደሉትን ዐማሮችን ነፍስ ይማር  !!
… ዐማራ ግን እግዚአብሔር ይድረስልህ !!
Filed in: Amharic