>

መንግስት በወለጋ የሚፈጸሙ ጭፍጨፋዎችን ለምን ማስቆም ተሳነው...??? (ያሬድ ሀይለማርያም)

መንግስት በወለጋ የሚፈጸሙ ጭፍጨፋዎችን ለምን ማስቆም ተሳነው…???
ያሬድ ሀይለማርያም

47,000 ዐማራዎች በወለጋ በአንድ አካባቢ ብቻ በከበባ እና  በእልቂት ዉስጥ ናቸዉ ይላል የኢትዮኒዉስ/Ethio News/ ሪፖርት::
መንግስት በወለጋ የሚፈጸሙ ጭፍጨፋዎችን ለምን ማስቆም ተሳነው? እሺ መንግስት በሰሜኑ ጦርነት ተወጥሮ ነው ቢባል እንኳ የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናትስ በተደጋጋሚ ኦነግ-ሽኔን በአጭር ጊዜ ማጥፋት እንችላለን ሲሉ እየተደመጠ ታዲያ ምን ያዛቸው? በክልሉ ውስጥ ስልጠና የተሰጠው በአሥር ሺዎች የሚቆጠር ልዩ ሃይል የዜጎችን ደህንነት መጠበቅ ካልቻለ ሥራው ምንድን ነው? በወለጋ ለሚጨፈጨፉት የአማራ ብሔር ተወላጆች ተጠያቂውስ ማነው? ሰሞኑን በጅምላ ከተጨፈጨፉት ሰዎች በተጨማሪ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የአማራ ተወላጆች በዚሁ አካባቢ ህይወታቸው ለአደጋ መጋለጡን ከአካባቢው የወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ማነው የሚታደጋቸው?
የፌደራል መንግስት እና #የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት ዜጎችን ከጥቃት የመታደግ ሃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል።
Filed in: Amharic