>

ኢትዮጵያ 11ኛውን አዲስ ክልሏን አምጣ ወለደች...!!! (ዘመድኩን በቀለ)

ኢትዮጵያ 11ኛውን አዲስ ክልሏን አምጣ ወለደች…!!!

ዘመድኩን በቀለ

 

…በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ውስጥ የነበሩ አምስት ዞኖች እና አንድ ልዩ ወረዳ ውስጥ ከሚኖሩ ዜጎች መካከል 1ሚሊየን 344 ሺህ 622 ዜጎች ድምፅ ለመሥጠት ተመዝግበው 1ሚሊየን 262ሺህ 679 ዜጎች ወይም ከተመዘገቡት 93 ነጥብ 9 በመቶ ድምፃቸውን በመስጠት ከቀረቡት ሁለት አማራጮች መካከል 1ሚሊየን 221 ሺህ 92 ዜጎች “የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች በሚል የጋራ አንድ ክልል ለመመስረት እደግፋለሁ” በማለት •የኮንታ ልዩ ወረዳ፣ •የምዕራብ ኦሞ ዞን፣ •የቤንች ሸኮ ዞን፣ •የዳውሮ ዞን፣ •የከፋ ዞን እና •የሸካ ዞኖች ድምፅ በመስጠታቸው የኦቦ አባዱላ ገመዳ ጥንስስ ፍሬ አፍርቶ፣ የእነ ጀዋር መሐመድ ህልም ተሳክቶ በዘመነ ዐቢይ አሕመድ በወ/ሮ ብርቱካን ሚደቅሳ አዋላጅነት መስከረም 20/2014 ዓም በተካሂደ ህዝበ ውሳኔ ኢትዮጵያ 11ኛውን አዲስ ክልል አምጣ ለመውለድ በቅታለች። በእውነት እንኳን ደስ የለን።
…በተወዳጁና አፍቃሬ ኢትዮጵያው አሻጋሪያችን ጠሚዶኮ ዐቢይ አሕመድ ሁለት አዳዲስ ክልሎች ከተጨማሪ ሁለት አዳዲስ ባንዲራዎች ጋር የተፈጠሩልን ሲሆን በቀጣይም ሀገር ለመሆን በትግል ላይ ያለችው ትግራይና ክልል ለመሆን በጥያቄ ላይ ያሉት፣ የወለጋ፣ የከምባታ፣ የጉራጌ እና የሌሎችም ብሔር ብሔረሰቦች ትግላቸውና ጥያቄያቸው ታይቶ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 39 መሠረት ሀገርም፣ ክልልም ይሆናሉ ተብሎም ይጠበቃል። ወያኔ በ27 ዓመት ኢትዮጵያን ዘጠኝ ቦታ የሸነሸነሸች ሲሆን የወያኔ ልጅ ብልፅግና ደግሞ ገና በ3 ዓመቱ ሁለት ክልል ፈጥሮ የወላጁን ሪከርድ ለመስበር እየተጋ ይገኛል።
… ዶሮ ማነቂያ… ደጃች ዉቤ… እሪ በከንቱ… ጌጃ ሰፈር… ቄራ… ካዛንችስ… ሽሮሜዳ… የካዎችም አስቡበት።
… ኤርትራ √ … ትግራይ…?  ኦሮሚያ…? ሶማሊያ…? አንቀጽ 39…
Filed in: Amharic