>

እስከመቼ ይሆን?!? (ዘምሳሌ)

እስከመቼ ይሆን?!?

 

ዘምሳሌ

እስከመቼ ይሆን
እነርሱ ልጆቻቸውን ሲያቅፉ
የሌላን ቤተሰብ  ወላጆች እየደፉ
ግፋቸው ከመጠን በላይ አልፎ
ህዙቡን ሲደርጉት አውራ ንብ እንዳጣ ቀፎ

ኢትዮጵያውያዊነትን ከልሰው
ስሟን እንኳ ለመጥራት ተጠይፈው
በወንጀላቸው ቀጥለው ሌላ ፓርቲ  ሲፈበርኩ
ህዝብ የሚያጋድለውን ህገደንብ እያመፃደቁ
ያልነበረ ስም ለጥፈው ራሳቸውን ሲያፀድቁ

የፈሪ ዱላ ጨብጠው
ለሀገር  ክብር የሚተጉትን ወህኒ ከተው
ፀሎትና ምህላ ሁሉ በየቤቱ ይዞ
መሄጃ መውጫ ሲጠፋ ለነፃነት የሚደረገው ጉዞ

እስከመቼ ኢትዮጵያ
ፈጣሪ  ሀገራችንን  አትምርም
ከአለማቱ ተጠራርጎ የገባውን ሴይጣናት
አታስወግድም
እመጫት ልጇን ተነጥቃ አካሏ ሲበለት
የሰው ልጅ በገዛ ፍጥረቱ የጭካኔ መጨረሻ
ሲመሰርት

ፍረድልን ! ፍረድ ልን እያሉ ሲማፀኑ
ህገ ገምድሎች  ብሰው ገዳዮችን ሲያሰለጥኑ

ሰዎች በወገናቸው ላይ  ሲሆኑ አናብስት
ስጋ በልተው እንደቅርጫ ሲካፈሉት

ዘቅዝቀው ሲሰቅሉ ጥርስ እያፋጩ
በድን ሙታን በገጀራቸው እየፈጩ

መማር መደደብ ከሆነ በኢትዮጵያ
የበታችነት ደዌ  ማምረቻ ገበያ

የማይድን ህመም  በጭንቅላታቸው ታቅፈው
ሀገርን ለማጥፋት የውሸት ታሪክ ፈጥረው

እስከመቼ በኢትዮጵያ

የሰላማዊውን ህዝብ ኑሮ ሆነው አፍራሾች
በህዝቡ ሲቃ የሆኑ ዳንኪራ ረጋጮች
ጥቂት መስሎ አዳሪ እውር ምሁራን ሰብስበው
በየመድረኩ ስማቸው ለማወደስ ታሪክ ሽረው

የበሉበት የሚጮሁ የሀገር አሜኬላዎች
ጠያፍ ስነምግባር የጎደላቸው  ማፊያዎች
ሕዝብ አስተምሮ ለወጉ ባደረሰ
ሌላው ባልሰራው ወንጀል  ተይዞ እየተከሰሰ
ሞት እስር እንግልት ባገር ሰፍኖ
መቆም መቀመጥ  እያቃተው  ሰው ባክኖ
እንዴት ይኖራል  ኢትዮጵያዊው በገዛ ሀገሩ
ተጨቁኖ

ዜጋ በወንጀለኞች ሴራ እጅ እግሩ ተጠፍሮ
ጥቂት በሚጣልለት ቅንጣቢ አንጀቱ አርሮ
ከያኒው ደራሲው ጋዜጠኛው እየሆነ ውሸትን
ዘጋቢ
የአምባገነኑ መሪ ስርዐት ርዕት አራጋቢ
በማያዛልቅ ተረኝነት በየመድረኩ እዩኝ ባይ
በዝቶ
የሚያነባውን ወገን  የሚዳኘው አድማጭ አጥቶ
የእምነት ደጃፎች በተረኝነት ጥላ ወድቀው
ህዝብ ከፈጣሪው እንዳይታረቅ እንቅፋት ሆነው
በቂም ቁርሾ ከቤተመቅደስ አጥቢያ ተገትረው
መሀሪውን አምላክ የፈጠረውን እንዲያጠፋላቸው
ተማፅነው

ምህረት ሰላምና ተስፋ ከሀገር ርቆ
ሰው በገዛ ህሊናው ክፉ ምኞት ወድቆ

እስከመቼ  በኢትዮጵያ

እነርሱ ሲሸላለሙበት በዘመኑ ጨቋኝ
እርስ በርስ እየተጋባበዙ ሲሆኑ እማኝ

መርገም ተጣብቶአቸው እንደ አልቅት
ስልጣንን ለግል ጥቅማቸው ሲያውሉት

ተረኞች ልጆቻቸውን አቅፈው በጉያቸው
ሌላውን ኢትዮጵያዊ እየነቀሉት ከቀየው

ወጣት አዛውንት ሴት ባልቴቱ ባለበት ፈዞ
ሀገር ስትወድም እያየ የሚኖር ተክዞ

እስከመቼ ድረስ ይሆን  የህዝቡ ፍዘት
የማይተመው ለነፃነት ለመዝመት
ቆርጦ የማይነሳው  በቁጭት

እስከመቼ  ይሆን የማይቆመው የኢትዮጵያውን
እልቂት

Filed in: Amharic