>
5:13 pm - Tuesday April 19, 1825

ኢትዮጵያን የረሳው የክልሎች መዝሙር...!!! ትዕግስት ዘሪሁን 

ኢትዮጵያን የረሳው የክልሎች መዝሙር…!!!

ትዕግስት ዘሪሁን 
በኢትዮጵያ ከደቡብ ክልል ውጪ ያሉት ሁሉም ክልሎች የራሳቸው የህዝብ መዝሙር አላቸው፡፡
በየትምህርት ቤቱም ታዳጊዎች የሚዘምሩት ይህንኑ የየክልሉን የህዝብ መዝሙር ነው፡፡
በተለይ አንዳንድ ክልሎች ሲያዘምሩት የኖሩትና አሁንም ያለው የህዝብ መዝሙር ቁርሾ፣ ቂምና በቀልን የሚያነሳሳ፣ ፀበኝነትን የሚያበረታታ ይዘት እንዳላቸው ሸገር ያነጋገራቸውና በግጥሞቹ ይዘት ላይ ትንታኔ የሰጡ ባለሙያዎች ትዝብታቸውን ተናግረዋል፡፡
ታዳጊ ሕፃናት ያሉበትን ክልል ብቻ እንደ አገር ቆጥረው ኢትዮጵያን እንዲዘነጉ የሚያደርግ ይዘት እንዳለውም ይነገራል፡፡
ወንድማማችነትና መከባበርንም የሚያመጣ ይዘት የለውም፡፡
 
የትግራይ ክልል መዝሙር   
የማንወጣው ተራራ የማንሻገረው ወንዝ የለም
ፍፁም ወደ ኋላ የለም
መስመር ነው ኃይላችን ፣ ሕዝብ ነው ኃይላችን
በጭራሽ አንሸነፍም
በፀሐይ ሃሩርና በቁር
ነፍሳችን ውሃ ይጥማት
አለት ይሁን ትራሳችን
ዋሻ ይሁን ቤታችን
ሌትም ቀንም ጉዞ
ይድከመንም ይራበንም
 ሆኖም
መስመር ነው ኃይላችን ህዝብ ነው ኃይላችን በጭራሽ አንሸነፍም
በጅቦች እንከበብ ፣ መሬት ይጥበበን
የጠላቶቻችን ጥርስ ስጋችን ውስጥ ይቀርቀር
ስጋችን ላሞራ ፣ ደማች እንደጎርፍ ይፍሰስ
አጥንታችን ይድቀቅ ዱቄት ሆኖ ይበተን
መስመር ነው ኃይላችን ፣ ሕዝብ ነው ኃይላችን
በፍፁም አንሸነፍም
የጦር መሳሪያ መርዝ ፣ ፋሺስታዊ ንዳድ
ሚሊዮን ጠላቶቻችን ፊታች ላይ ይጉረፉ
መስዋዕትነት ፣ መቁሰልና ኪሳራም እንከፍላለን
የከፋ መከራም ቢመጣ ወደን እንከፍላለን
መስመር ነው ኃይላችን ህዝብ ነው ኃይላችን
 በዚህ ሁሉ ጉዞ ግን አሸናፊዎች እኛ ነን፡፡
የኦሮሚያ ክልል መዝሙር
ኦሮሚያ ኦሮሚያ የትልቅ ታሪክ ባለቤት
የኦሮሞ እምብርት
 የገዳ ስርዓት ማዕከል
የህግና ሥርዓት ምድር
የጨፌ ኦዳ እናት
የበለፀግሽ የታደልሽ
ሁሉን አብቃይ
የመቶ አመት ግፍን
በደማችን አጠብንልሽ
መስዋእትነት ከፍለን
ሰንደቅሽን ከፍ አደረግን
ደስ ብሎናል ደስ ይበልሽ
ገዳችን ተመለሰልሽ
ሰላምና ዲሞክራሲ
ለሰው ልጆች ክብር
አስተማማኝ ልማት
ፈጣን እድገት
በሰላምና በአንድነት
ከሕዝባችን ጋራ
ትልቅ ህልምን ይዘን
ለኑሮ ምስክርነት
በአዲስ ሀይል ተነስተናል
ኦሮሚያ እደጊ በልፅጊ ፣ ስፊ ትልቅ ሁኚና ኑሪ
የአማራ ብሔራዊ ክልል መዝሙር
የታታሪ ህዝቦች የታሪክ ማህደር
የአኩሪ ባህል አምባ የድንግል ሀብት አፈር
የህዝቦችሽ ተስፋ ለሟ ክልላችን
በሰላም በፍቅር በልማት ጉዟችን
ተባብረን በሥራ እንገነባሻለን
የአማራነት ክብር ደማቅ አርማ ይዘን
ከሌሎች ህዝቦች ጋር እኩል ተከባብረን
በፍቅር በአንድነት አብረን እንዘልቃለን፡፡
Ethiopia Sheger Werewoch የህዝብ_መዝሙር #አማራ_ክልል #ትግራይ_ክልል #ኦሮሚያ_ክልል #አፋር_ክልል #ሲዳማ_ክልል
Filed in: Amharic