ይወገዝ ይወገድ!
ይወገዝ ይረገም ንፁሀን የፈጀ
ለስልጣን ጥማቱ ሀይልን ያደረጀ
ሰላማዊውን ህዝብ ነጥሎ የፈረጀ
እሰር ግደል ብሎ አዝዞ ፀብ ያወጀ
ይወገዝ ይረገም እንዳይበቅል ዳግም
የገደላቸው ነፍስ ይሁኑበት መርገም
በራሱ ይድረሰው የመከራ ህመም
እንዳይኖር በኢትዮጵያ ህይወቱ ትጨልም
ይወገዝ ይረገም እምነት የበከለ
ባህል ተቋም ሽሮ ክብራችን የጣለ
ከገዳዮች ሚያብር በኢትዮጵያ ያለ
በህዝቡ ላይ ክዳት ሲፈፅም የዋለ
ይወገዝ ይረገም ሀገር የሚጎዳ
ሀላፊነት ወስዶ የጨመረን ዕዳ
የእምነት ጥላ ለብሶ ያመጣብን ፍዳ
ጭንቅላት መርዞ ሀገርን ያስከዳ
ቅጥረኛ የሆነ የሽብር ጠበቃ
በዘር ተሸጉጦ ያለ ሆኖ ሳንካ
ፖርላማ የሚኖር በጥል ፀብ ሰበካ
ይወገዝ ይወገድ ሕዝብን የሚያስጠቃ
ዘምሳሌ