>

የመጨረሻው መጀመሪያ እንዳይሆን...!!! (ቹቹ አለባቸው)

የመጨረሻው መጀመሪያ እንዳይሆን…!!!

ቹቹ አለባቸው

ሰሞኑን በወሎ ግንባር ተገኝተን የጦርነቱን ሁኔታና የተዋጊ ኃይላችንን የውጊያ ውሎ እንዲሁም የጠላትን እንቅስቃሴና ፍላጎት በሚገባ ለመገንዘብ ዕድሉን አግኝተናል። ስለወገን ጦር ተጋድሎና ሰለህዝቡ የአርበኝነት ሚና በተደጋጋሚ ስላነሳሁ እዚህ ላይ ባልደግመውም ስትራቴጂያዊ አመራር ማረጋገጥ እስከተቻለ ድረስ ‹ሁነኛ ወገን› እንዳለን ግን በድጋሚ መመስከር ይኖርብኛል።
እንደችግር ሊጠቀስ የሚገባው መሠረታዊ ጉዳይ ኃይል ማቀናጀት ላይ ክፍተቶች መታየታቸው ነው፡፡ ሁሉም በየፊናው የመንቀሳቀስ ፍላጎት መኖሩ አቅም እንዳይሰባሰብ አድርጓል፡፡ ከዚህ አንፃር ጦርነቱን ሕዝባዊ ለማድረግ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች በሚፈለገው ልክ አለማደጋቸውና በሚጠበቅብን ልክ አቅም እየገነቡ አለመሆናቸው እንደችግር ይታያል፡፡ የገጠመን ጠላት የሚከተለው የጦርነት ስልት በሁለመናው ተለዋዋጭና ተነቃናቂ (mobile warfare) እንደመሆኑ መጠን የጠላትን ባህሪ ተረድቶ ለመልሶ ማጥቃት ራስን ማዘጋጀት፤ ለዚህ ደግሞ ኃይልን ማቀናጀት ይገባል፡፡
ጠላት ዕድሜው ከ12 ዓመት ህፃን እስከ 70 ዓመት አዛውንት ሴት ወንድ ሳይለይ ለጦር ወረራው ማሰለፉን ከሟቾች በድን አካልና ከጦር ምርኮኞች የሚገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ይህ ግልጽ የሆነ ሕዝባዊ ጦርነት እንደተከፈተብን በቂ ማሳያ ነው፡፡ ሕዝባዊ ጦርነት ውስጥ እንደመገኘታችን የጦርነቱን ባህሪ ለይተን ልረዳው ይገባል፡፡
ህዝባዊ ጦርነት ሲባል እንደሕዝብ መሰለፍን የሚጠይቅ የጦር ስልት ሲሆን፤ ሁሉም አካላዊና ህሊናዊ ሁነቶች ወደ ጦር ግንባር ማለታችን ነው፡፡ ሁሉም ነገር ወደ ጦር ግንባር ስንል ሁሉም የሚችለውን ያደርጋል ማለት ነው፡፡ በዚህ ሂደት ኃይል የማቀናጀት ስራው የድል ጫፍ የማድረስ አቅሙ ከፍ ያለ ነው፡፡ ከዚህ አንፃር የመከላከያ ኃይላችን፣ ልዩ ኃይሉ፣ ሚሊሻው፣ ፋኖውና በጠቅላላ ወጣቱ በግንባር የሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች የተናበቡና የዕዝ ጥገጋቸውን የጠበቁ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ ኃይል ማቀናጀት ባልተቻለ ቁጥር በሚፈጠረው ዝብሪት ጠላት ዕድል እያገኘ ወደወሳኝና ስትራቴጂያዊ ስፍራዎችን የመቆጣጠር ዕድል ሊያገኝ ይችላልና የኃይል ቅንጅቱ ላይ ልዩ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡
መሬት ላይ ያለውን የጠላት ፍላጎት ለተመለከተ ሰው የጠላት ዋነኛ ግብ ደሴና ኮምቦልቻን ወርሮ  በመያዝ በመጀመሪያ ደረጃ የአማራን ቅስም መስበር፣ ሲቀጥል ደግሞ ከቻለ ሁሉንም  ንብረት መውስድ ያልቻለውን ደግሞ ማውደም ነው። በዚህ ሂደት አማራ በሥነ-ልቦና እንዲሰበር ከማድረጉም በተጨማሪ የኢኮኖሚ ድቀት በመፍጠር በድህነት ሃምሳ ዓመት ወደኋላ እንዲጎተት ማድረግ ነው።
ይህን የምንለው ደሴና ኮምቦልቻ ስትራቴጂካዊ አቀማመጥ ያለቸው ቦታዎች በመሆኑ ነው፡፡ ከዚህ ተነስቶ ጠላት በወረራ የያዛቸውን ቦታዎች ማስለቀቅ የሚቻለው፡፡ እነዚህ ቦታዎች ለጂቡቲ ወደብ፣ ለአዋሽ እና መካከለኛ የኢትዮጵያ ወሳኝ ስፍራዎች መሸጋገሪያ፤ በአማራ እና ፌደራል መንግስት ደረጃ አለምአቀፋዊ የምርትና ገበያ መዳረሻ መሆናቸው፣ አካባቢውን እጅግ የላቀ ወታደራዊ ትርጉም ያለው ገዥ መሬት ያደርገዋል፡፡
ሌላውና ወሳኙ ጉዳይ ይህ ቀጠና ከትህነግ ጋር ግንባር የፈጠረዉ ኦነግ-ሸኔ ያደፈጠበትና እንደገና ተጠናክሮ ለመነሳት ተለዋጭ ሁኔታዎችን በመጠባበቅ ላይ የሚገኝበት መሆኑ ነው፡፡ በአጠቃላይ የውስጥና የውጭ ጠላቶች የጥፋት ጋብቻ የወጠኑበት፤ በቀደመ የጥፋት ተልዕኳቸውም ቀላል የማይባል ጉዳት ያደረሱበት፣ ለሴራ እንቅስቃሴ ትልቅ ጉልበት የሚያገኙበት በመሆኑ በዚህ ቀጠና ልዩ ዘመቻ ያስፈልጋል፡፡
አሁን ጥያቄው ለጊዜውም ቢሆን  የአማራ ህዝብና የፌደራሉ መንግሥት ደሴና ኮምቦልቻን ከወራሪው ኃይል መታደግ ሳይችሉ ቢቀሩ የኢትዮጵያ ፖለቲካ እንደአጠቃላይ በተለይም ደግሞ የአማራ ፖለቲካ ዕጣ ፈንታ ምን ሊሆን ይችላል የሚለው ነው።
በእኔ እምነት የደሴና ኮምቦልቻ በጠላት እጅ መውደቅ እንዲሁ ቀላል የሆነ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም ሥነ-ልቦናዊ ውድመት የሚያደርስ አይሆንም። ይህ ሁኔታ በተለይም የአማራን ሁኔታ እጅግ ያወሳስበዋል። እውነት ነው ጠላት ለገጣፍ ደርሶም ቢሆን ሊሸነፍ ይችላል፤ መሸነፉ ላይም አጠራጣሪ ነገር የለውም። ነገር ግን ጠላት ደሴና ኮምቦልቻን አውድሞ፤ ደ/ብርሀንን አድቅቆ ለገጣፎ  ሲደርስ መሸነፉ፣ለኢትዮጵያ በተለይም ለአማራ ህዝብ የሚያስገኝለት ፋይዳ እምብዛም ነው፡፡ ምክንያቱም ጠላት ለገጣፎ ላይ የሚሸነፈው በተለይም የአማራ ህዝብ በብዙ ዓመታት ሊመልሰው የማይችለው ሰብዓዊና ቁሳዊ ውድመት ከደረሰበት በኋላ ስለሚሆን ነዉ።
ስለዚህ መፍትሄው የፌደራሉ መንግሥት የቆጠበው አቅም ካለ ይሄንን የተቆጠበ አቅም አሟጦ በመጠቀም ደሴና ኮምቦልቻን በመታደግ ወደሰሜን ወሎ ማተኮር አለበት፡፡ ከአሁናዊ ሁኔታዎች አኳያ ደሴና ኮምቦልቻን መታደግ ያልቻለ አገራዊ አቅም በፍፁም ሊኖር አይገባም። የፌደራሉ መንግሥት ይሄን በማድረግ ብዙ ጥቅም ያገኝበታል። ይሄንን ባለማድረግ ደሴና ኮምቦልቻ በጠላት እጅ ከወደቁ ደግሞ የፌደራሉ መንግሥት የሚያጣው ጥቅም ዘርፈ ብዙ እንደሚሆን ለመገመት አይከብድም።
በነገራችን ላይ በዜጎች ህብረት የፀናች አንዲት ሉዓላዊነት ኢትዮጵያ እንድትኖረን እንሻለን፤ አንዱ አንገት ደፍቶ፣ ሌላው ደረቱን የሚነፋባት ኢትዮጵያ ልትፀና እንደማትችል እናውቃለንና ይህ ጦርነት የሚካሄደው በኢትዮጵያ እና በሀገረ-መንግሥቱ ጠላቶች መካከል ሁኖ በተግባር ሊተረጎም ይገባል፡፡ ጠላት ለጊዜው አማራና አፋር ላይ የጦር ወረራ ጥቃት ከፈተ እንጅ በአደጋው ልክ ሳይመከት ቀርቶ አድማሱን ባሰፋ ቁጥር ለኦሮሞውም፣ ለሲዳማውም፣ ለሱማሌውም፣…የማይመለስ ፀረ-ኢትዮጵያ ኃይል ነው፡፡ እናም የፌዴራሉ መንግሥት የቆጠበው አቅም ካለ ይሄንን የተቆጠበ አቅም አሟጦ ሊጠቀም ይገባል፡፡
ይሄም ሆኖ የፌደራሉ መንግሥት ሁሉን ነገር ሊሸፍን አይችልም። በአማራ ክልል ደረጃ የክልሉ መንግሥት ሁሉንም አቅም አሟጦ በመጠቀም በልኩ በጊዜ የለንም መንፈስ መረባረብ አለበት። በተለይም ‹ሁሉም ነገር ወደጦር ግንባር› መባል አለበት። ይህ ሁኔታ የመንግሥት መስሪያ ቤቶችን እስከመዝጋት ሊደርስ ይችላል። ከዚህም በላይ ምድር ላይ ወርዶ የቅርብ አመራርን ማረጋገጥ ያስፈልጋል። በዚህ ረገድ በግንባር የሚኖረው የአመራር ስምሪት የጦርነቱን ውጤት ለመቀየር የሚያስችል እንዲሆን ታስቦ ሊተገበር ይገባል፡፡ አዲሱ ርዕሰ መስተዳድር፤ አዲሱ ካቢኒ እሳት ላይ እንደተጣዱ ግልጽ ነው፡፡ ይህም ሁኖ የጦርነት አቋም እና ሁለንተናዊ ስምሪት ላይ መገኘት የታሪክ አስገዳጅነት ሁኗልና አዳዲሶቹ አመራሮቻችን ይህን ተልዕኮ በፅናት እንዲወጡት የአደራ መልዕክት አለኝ፡፡ ደግሞም ይችላሉ!!
የአማራ ህዝብ በተለይም ወጣቱ  እንደ ህዝብ ማምረር አለበት። ምክንያቱም ከጠላት አንፃር አሰላለፉ ሁሉንም ትግሬ  የኃይል አማራጭ  ማዕከል ያደረገ የጦር ስልት ነው የሚከተለው። ዛሬ በየትኛውም ቦታ የሚገኝ አብዛኛው ትግሬ የጦርነቱ አካል ነው፡፡ አንድም በግንባር ሌላም በፕሮፖጋንዳና በፋይናንስ ሕዝባዊ ጦርነቱ ላይ እጃቸውን አስገብተዋል፡፡
በሰሞኑ የወሎ ግንባር ቆይታየ የተማረከ ቄስ አይቻለሁ፤ ይህ ቄስ ጦርነት ውስጥም ሆኖ ‹ፅጌ ፆም› ይፆማል። የትግሬ እርጉዝ ሴቶች ክላሽ ይዘው ሕዝባችን ለመውጋት ተሰልፈዋል፡፡ አርሶ አደራቸው በአንድ እጁ ክላሽ በሌላ እጁ ማጭድ ይዞ ነው ለጦር ወረራና ዘረፋ የዘመተው፡፡ እነዚህ ሰዎች ይሄንን ያክል ነው ቆርጠው ሊያጠፉን የተነሱት። ሜዲካል ዶክተሮች፣ ኢንጅነሮችና በትልልቅ ሙያ ደረጃ ላይ የደረሱ ትግሬዎች የሬጅመንት አመራር ሁነው እያዋጉ እንደሆነ ከምርኮኞች የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡ ሌላውን የትግሬ ወጣትና  ሲቪል ሰርቫንትማ ተውት፤ ከእረኛ እስከ ምሁር ሊወጉን ብቻ ሳይሆን ሊያጠፉን ተሰልፈውብናል!!
እናም እንደአማራ አማራነትን በተግባር መሬት ላይ እናሳይ!! የአማራ ጉልሀን (አክቲቪስቱን ጨምሮ) እውነተኛ ጉልሀንና ሕዝባዊ ወገንተኝነት መለያው የሆነ አክቲቪስት  እንሁን። ቢያንስ ህዝባችን በተለይም ወጣቱ ጠላትን አምረሮ እንዲጠላና እንዲታገል መሬት ወርደን እናንቃ። የሕዝባችን ሙሉ አቅምን አሟጦ መጠቀም ላይ ትኩረት እናድርግ፡፡፡ በዚህ በኩል ጅምሮች ቢኖሩም በተደቀነብን አደጋ ልክ አልሰራንም።
ለዚህ ነው ዛሬ ላይ በጠላቶቻችን መንደር አይደለም ወጣት ቀርቶ ቀሳውስትን እንኳን ማየት ብርቅ በሆነበት ወቅት፣ በኛ ክልል ግን ያውም ተወርረን ባለንበት ሁኔታ ገጠሮቻችን እና  ከተሞቻችን በወጣቶች ተሞልተው የአዘቦት ተግባራት ላይ የምናያቸው። ይሄን ሁኔታ መቀየር ካልቻልን ድላችን ሩቅ መሆኑ አይቀሬ ነው።
ለሁሉም ደሴና ኮምቦልቻን ማዳን የሁሉም አካላት ወቅታዊና ቀዳሚ አጀንዳ መሆን አለበት። ይሄንን አለማድረግ በአገሪቱ በተለይም በአማራ ፖለቲካ ውስጥ የሚፈጥረው ምስቅልቅል እጅጉን ያስፈራኛል። የመጨረሻው መጀመሪያም ይሆናል!! ትግሉ ከጠላት ጋር ብቻ ሳይሆን ከጊዜ ጋር ጭምር ሊሆን ይገባል!!
Filed in: Amharic