የአማራ ሕዝብ ብቸኛ አማራጭ
መስፍን አረጋ
ጠላቶች በሁለት ዓይነት ይከፈላሉ፡፡ አንደኛው ሁኔታወችን መሠረት ያደረገ ጠላት ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ማንነትን መሠረት ያደረገ ጠላት ነው፡፡
ሁኔታወችን መሠረት ያደረገ ጠላት፣ ሁኔታወቹ በቀሰቀሱት ጦርነት ድል አድርጎ ሁኔታወቹን ቢያስቀይር ጠላትነቱ ወዲያውኑ ያከትማል፡፡ በተጨማሪ ደግሞ ድል ቢያደርግም፣ የድል ተደራጊውን ስሜት ላለመጉዳት ከፍተኛ ጥንቃቄ ያደርጋል፡፡ ድል አደረኩ ብሎ በድል ተደራጊው ላይ ማድረግ የሚችለውን ሁሉ አያደርግም፡፡ ይልቁንም ደግሞ ከኔ ይቅር በማለት ለድል ተደራጊው ከሚገባው በላይ ይቸርለታል (ቸር ይሆንለታል)፡፡ ለተሸናፊው ቡድን ርህራሄንና ከበሬታን ስለሚያሳይ ጨዋ አሸናፊ (gracious winner) ይባላል፡፡
ለምሳሌ ያህል አጤ ምኒሊክ በጨዋ አሸናፊነታቸው ወደር ያልነበራቸው ታላቅ ንጉስ ነበሩ፡፡ አጤ ምኒሊክ ጨዋ አሸናፊ ባይሆኑ ኖሮ፣ ከኦሮሞ መስፋፋት በኋላ በጉዲፈቻና በሞጋሳ አማካኝነት ኦሮሞነትን እንዲላበስ የተደረገውን እልፍ አእላፍ ሕዝብ ወደ እውነተኛ ማንነቱ በግድም በውድም እንዲመለስ ከማድረግ የሚያግዳቸው ምንም ኃይል አልነበረም፡፡ ወሎን፣ ወለጋን፣ አሩሲን … በቀደምት ስማቸው ማስጠራት ይችሉ ነበር፡፡ በጥቅሉ ለመናገር አጤ ምኒሊክ ጨዋ አሸነፊ ባይሆኑ ኖሮ በዛሬይቱ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሕዳጣኑ ከቦረኔ ውጭ ኦሮሞ ነኝ የሚል ማንም ስለማይኖር፣ የኦሮሞ ቁጥር ሚሊዮን እንኳን ባልሞላ ነበር፡፡ በኦሮምኛ የተሰየመ ቦታ ደግሞ የትም አይኖርም ነበር፡፡
በሌላ በኩል ግን ማንነትን መሠረት ያደረገ ጠላት፣ ጠላትነቱ ዘላለማዊ ነው፡፡ በለስ ቀንቶት የሚጠላውን ቡድን ድል ቢያደርግ፣ በጥላቻው ላይ ንቀት ስለሚጨምርበት ጥላቻው ይበልጥና ይበልጥ መሪር ይሆናል፡፡ የድል ተደራጊውን ቅስም ለመሰባበር የማይፈጽመው እኩይ ተግባር የለም፡፡ ከጥላቸው ምሬት የተነሳ ድል ተደራጊውን እያሰቃየና እያዋረደ ቀስ በቀስ ይገድለዋል እንጅ፣ ባንድ ጥይት አይገላግለውም፡፡ እርካታ የሚሰጠው የጠላቱ መከራ እንጅ የራሱ ተድላ አይደለም፡፡ ጠላቱን እስከጨፈጨፈ፣ እስካሰቃየ፣ እስካስራበ፣ እስካስጠማ፣ እስካሳረዘ ድረስ፣ የሱ መጨፍጨፍ፣ መሰቃየት፣ መራብ፣ መጠማት፣ መታረዝ ቅር አያሰኘውም፡፡ የጠላቱ አንድ ዓይን የሚጠፋ ከሆነ፣ የሱ ሁለት ዓይኖች ድርግም ቢሉ ዴንታ የለውም፡፡
ወያኔ አማራን በማንነቱ የሚጠላ የአማራ መሠረታዊ ጠላት ነው፡፡ አማራ ገዝግዞ የጣለውን ደርግን በአማራ ድጋፍ አስወግዶ ስልጣን ሲይዝ፣ ከአማራ ጋር በመከባበር ከመተባበር ይልቅ፣ አማራን አሸነፍኩ እያለ በመታበይ ከኦነጋውያን ጋር የተሞሸረው፣ አማራን የሚጠላው በአቋሙ ሳይሆን በማንነቱ ስለሆነ ብቻ ነው፡፡ አማራን አሸነፍኩ ካለ ደግሞ ጨዋ አሸናፊነትን ተላብሶ ለጊዜውም ቢሆን ተሸናፊ የሆነውን የአማራን ስሜት ላለመጉዳት ከመጣር ይልቅ፣ ባማራ ሕዝብ ላይ ለመናገር የሚቀፉ ብልግናወችን የፈጸመው ጥላቸው የማንነትና የማንነት ብቻ ስለሆነ ነው፡፡
ባሁኑ ጦርነት ደግሞ በለስ ቀንቶት አማራን ቢያሸንፍ የአማራን ሕዘብ በሁሉም ረገዶች ቁም ስቅሉን እያሳየ ቀስ በቀስ እንደሚያጠፋው የሃያ ሰባት ዓመታት ታሪኩ በግልጽ ይመሰክርበታል፡፡ ስለዚህም፣ የአማራ ሕዝብ እንደ ሕዝብ እንዳይጠፋ ከፈለገ ያለው ብቸኛ አማራጭ ወያኔን ማጥፋት ነው፡፡
አቶ ዳንኤል ክብረት ወያኔን በሥጋ ብቻ ሳይሆን በመንፈስም ማጥፋት አለብን ሲል ምንም አልተሳሳተም፡፡ ዳንኤል ክብረትን በጥላቻ ንግግር የሚኮንኑት አሜሪቃኖች፣ ‹‹አንድ ነፍሰጡር ያረገዘችው ልጅ የወደፊቱ ሂትለር መሆኑን ብታውቅ ታስጨንግፈው አታስጨንግፈው?›› (“Kill an unborn baby hitler?”) በሚል መላምታዊ ጥያቄ በትልቁ ጋዜጣቸው በኒዮርክ ታይምስ (New York Times) ላይ ላያሌ ቀናት የጦፈ ክርክር የተከራከሩ ተመጻዳቂወች ናቸው፡፡ አሜሪቃኖችን (በተለይም ደግሞ አንቶኒ ብሊንከንን (Antony Blinken) የመሳሰሉ አይሁድ አሜሪቃኖችን) የሚያሳስባቸው ጀርመናዊት የፀነሰችው ልጅ ሂትለር ይሆን ወይ የሚለው የገና ለገና ስጋታቸው ነው፡፡ የአማራ ሕዝብ እየተፋለመ ያለው ግን ሂትለርነታቸውን በግልጽ ካስመሰከሩ የወያኔና የኦነግ መሪወችና እነሱን በጭፍን ከሚከተሉ በሚሊዮኖች ከሚቆጠሩ አውሬነትን ከተላበሱ መንጋወቻው ጋር ነው፡፡
የአማራ ሕዝብ እንደ ሕዝብ በወያኔ እንዳይጠፋ ከፈለገ ወያኔን ማጥፋት አለበት፡፡ ወያኔን ለማጥፋት ደግሞ ቁልፉ እርምጃ ኦነጋዊውን ዐብይ አሕመድን ማስወገድ ነው፡፡ የራሱ የሆነውን ኦነግን በደንብ አድራጅቶ፣ እስካፍንጫው አስታጥቆ፣ በወሳኝ ቦታወች ላይ ያሰማራው ዐብይ አሕመድ፣ አማራን አትደራጅ፣ አትታጠቅ፣ አትዝመት የሚለው፣ የአማራን ሕዝብ ባንድ በኩል በወያኔ በሌላ በኩል በሸኔ እያንገረገበ ፍጻሜውን ለማፋጠን ነው፡፡
የአማራ ሕዝብ በከፈለው ከፍተኛ መስዋዕትነት ድባቅ ተመትቶ የነበረውን ወያኔን ባጭር ጊዜ ውስጥ እንዲያንሰራራ ያደረገውን፣ ቀጥሎ ደግሞ ያማራን ሕዝብ ፍዳ እያስበላ ባጭር ጊዜ ውስጥ ደሴ በር እንዲደርስ ያመቻቸለትን ኦነጋዊውን ዐብይ አህመድን የጦር ጠቅላይ አዛዥ አድርጎ ከወያኔ ጋር ጦርነት መግጠም፣ ውጤቱ የአማራን ሽንፈትና እንደ ሕዝብ መጥፋት ማፋጠን ብቻና ብቻ ነው፡፡
ዐብይ አህመድ የጭቆናን ምንነት በቅጡ ሊረዳ በማይችልበት ለጋ እድሜው “ያማራ ጨቋኞችን” ለመታገል ጫካ ገብቶ የወያኔን ጡት እየጠባ ባማራ ጥላቻ ተመርዞና ተሰቅዞ ያደገ፣ አማራን በማጥፋት አማራዊ ናት የሚላትን ጦቢያን አፈራርሶ በሷ መቃብር ላይ የኦሮሞ አጼጌ (Oromo empire) ለመመሥረት ቆርጦ የተነሳ፣ በዚያ ላይ ደግሞ በማንነቱ ምክኒያት በሥርሰደድ (chronic) የስነልቦና በሽታ የሚሰቃይ ኦነጋዊ አውሬ ነው፡፡ የዚህ እኩይ ግለሰብ የአማራ ጥላቻ፣ ከወያኔ የአማራ ጥላቻ እጅግ ቢብስ እንጅ አያንስም፡፡ ከመምህሩ ደቀ መዝሙሩ ወይም ደግሞ ከለማበት የተጋባበት እንዲሉ፡፡
ዐብይ አሕመድ ማለት በአማራ ሕዝብ ላይ ዘግናኝ ጭፍጨፋ እስኪፈጸም ድረስ ሥራየ ብሎ እየጠበቀ፣ በነገታው አዳባባይ ወጥቶ አበባ በመትከል፣ ወይም ደግሞ በፌስቡክና በትዊተር ስለ አበባ ውበት በመደስኮር፣ ወይም ደግሞ ስለ ስንዴ ማሳ በመቀባጠር፣ የአማራን ሞት ከዝንብ ሞት እንደማይቆጥረው በግልጽ የሚያሳይ፣ የአማራን ሕዝብ ክፉኛ እያቆሰለ፣ ማቁሰሉ ብቻ ስለማያረካው በቁስሉ ላይ እንጨት የሚሰድ አረመኔ ነው፡፡ የዚህ አኩይ ግለሰብ የአማራ ጥላቻ እጅግ የመረረ ከመሆኑ የተነሳ፣ አማራ ወያኔን አሸንፎ እሱን ከሚያድነው ይልቅ፣ ወያኔ አማራን አሸንፎ እሱን ቢሰቅለው እንደሚመርጥ ሥራው ሁሉ በግልጽ ይመሰክርበታል፡፡
ስለዚህም የአማራ የህልውናው ጦርነት ዋና ትኩረት መሆን ያለበት የወያኔን ኅልውና ባረጋገጠው በዐብይ አሕመድ ላይ ነው፡፡ የህልውናው መፈክር መሆን ያለበት ደግሞ ሁሉም ነገር ወደ ወሎ ሳይሆን ወደ ሁሉም ነገር ወደ ዐራት ኪሎ ነው፡፡
Email: mesfin.arega@gmail.com