ዘመድኩን በቀለ – ጌጥዬ ያለው
* …. ጠበቃ ሔኖክ አክሊሉ ታዳሚው ጥሎ ከወጣ በኋላ በቀጠለው ችሎት የተናገረው፦
*…. በእስክንድር ነጋ ላይ የተፈጸመው ድብደባ የፈጠራ ክሱ እንደማያዋጣ ሲታወቅ የተሄደበት የፈሪዎች መንገድ ነው። ከልብ እስክንድርማ ጀግና ነው። በፈጠራ ክሱ ጦርነት ውስጥ እንገባለን ያሉትን የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዠ አብይ አህመድ አንድ ወታደር ሳያዝ በፍትህ አደባባይ ራቁታቸውን አስቀራቸው። ጭምብላቸውን በአደባባይ ደጋግሞ ገፈፈው። ውርደታቸው ከጀመረ ቆይቷል። የቀረው ውድቀታቸው ብቻ ነው ዛሬ የበለጠ ግልጽልጽ አድርገውታል።እንደቀሩት አምባገነኖች የግልገል ጁንታውም ዕጣ ተመሳሳይ ነው። ስለ ሰብዓዊ መብት ስለ ፍትሕ እንጨነቃለን የምትሉ ባለህሊኖች በእስክንድር ላይ በቅሊንጦ እስር ቤት የተፈጸመውን ድብደባ እንድታወግዙ። ቀሪው የጊዜ ጉዳይ ብቻ ነው። አዲስ ምዕራፍ አዲስ ጭፍጨፋ አዲስ ድብደባ ። መካሪ የሌለው ንጉስ አሉ።
…በቂሊንጦ ወኅኒ ቤት ታስሮ በሕግ ጥላ ስር የሚገኘው ታወቂው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች እና ጋዜጠኛ እንዲሁም የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፕሬዘዳንት አቶ እስክንድር ነጋ በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ዛሬ ሌሊት ተደብድቦ ማደሩ ተነግሯል።
…ትናንት ዐቃቤ ሕግ ምስክሬ ብሎ ያቀረበው መስካሪን በመስቀለኛ ጥያቄ ካዝረከረኩት በኋላ በሁኔታው የተበሳጨው ዐቃቤሕግ ከችሎት መልስ ምሽቱን ሲዝትና ጥርሱን ሲያፋጭ እንደነበረም ተሰምቷል። በዐቢይ አሕመድ ቀጥተኛ ትዕዛዝ በፍትሕ ሚኒስቴሩ በዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ አማካኝነት የተሾመው ዐቃቤ ሕግ ኦቦ ዮስያድ አበጀ ዓመት ሙሉ ለምስክርነት ያዘጋጃቸውን የሀሰት ምስክሮች ፈጣሪ በአንድ ጊዜ ሲበታትናቸው በቀጥታ ወደ ኃይል ጥቃት በመሻገር እስክንድርን በመግደል ፍትሕን ለመቅበር በማሰብ በማረሚያ ቤት በተደራጁ ወንጀለኞች እስክንድር እንዲደበደብ ተደርጓል።
…ዛሬ በዐቃቤ ሕግ ኦቦ ዮስያድ አበጀ የተመለመለችውና የልደታ ክፍለ ከተማ የወረዳ 5 የሴቶችና ህጻናት ኃላፊዋ አዴ መንበረ በቀለ ሁለተኛዋ የዐቃቤ ሕግ ምስክር ሆና የምትሰማበት ዕለት ነበር። በፍርድ ቤቱ የአዲስ አበባ ህዝብ ግጥም ብሎ ሞልቶ ተገኝቶም ነበረ። ዳኞችም፣ ዐቃቤ ሕጉም፣ ተኝተዋል። ከታሳሪዎቹ መካከል 3ቱ ሲገኙ እስክንድር ነጋ ግን በሥፍራው አለነበረም። ምስክርነት የሚሰማው ደግሞ በእሱ ላይ ነበር። ፍርድ ቤቱ ሥራውን ሊጀምር ሲል አቶ ስንታየሁ ቸኮል አስተያየት አለኝ በማለት ፍርድ ቤቱን ጠየቀ። ፍርድቤቱም ፈቀደለት።
… ክቡር ፍርድ ቤት። ችግር ተፈጥሯል። አቶ አስክንድር ነጋ በወኅኒ ቤት አደጋ ስላደረሱበት ወደ ፍርድ ቤት መምጣት አልቻለም። እኔም የመጣሁት ፕሬዝዳንቴ ስለሆነ ለፍርድ ቤቱ እንዳስረዳ ስለ ላከኝ እንጂ አልመጣም ነበር ብሎ እስረዳ፣ ሴቶቹም ህዝቡም ሁሉ አለቀሱ።
• ዳኞቹም ጠየቁ፦ ምንአልባት ከቻሉ ቀጠሮውን ለነገ እናድርገው?
• አቶ ስንታየሁ መለሰ፦ አይ ከሳምንት በፊት የሚድን አይመስለኝም።
…የችሎቱ ታዳሚ እያለቀሰ መውጣት ሲጀምር ዳኛዋም ዳኛ ሳይፈቅድ ችሎት ረግጦ መውጣት ክልክል ስለሆነ ህዝቡን ቆይ ተረጋጉ፣ እኛ እንፈቅድላችኋለን በማለት ለህዝቡ ችሎቱን ለቀቆ እንዲወጣ በመፍቀድ ህዝቡ ችሎቱን ረግጦ ወጥቷል። ችሎቱ ተቋርጧል ነው የተባለው። በሁኔታው ዐቃቤ ሕጉና ምስክሯ ግን ይሳሰቁ እንደነበር ነው የፍርድቤት ምንጮቼ አክለው የገለጹት።
…ቆይቶ ከችሎቱ ወጥቶ የእስክንድርን ጤንነት ለማረጋገጥ ወደ ቂሊንጦ ለመሄድ መንገድ የጀመረውን ህዝብ የአዲስ አበባን ዩኒፎርም የለበሱ የኦሮሚያ ፖሊሶች መንገድ ላይ አስቁመው እየደበደቡ በመኪና ጭነው እንደወሰዷቸውም ታውቋል።
… አሁን ዐቢይ አሕመድ በግልጽ ተሸንፏል። ዐቢይ አሕመድ ከሽፏል። ዐቢይ አሕመድ ነፍሶበታል። ዐቢይ አሕመድ እጅእጅ ብሏል። ዐብይ አሕመድ ጎርንቷል። ዐብይ አሕመድ ውቃቢው ርቆታል። ዐቢይ አሕመድ የውድቀት ቁልቁለቱን ተያይዞታል። ዐቢይ አሕመድ በእስክንድር ነጋ ቆሌው ተገፏል። ዐቢይ አሕመድ በእስክንድር ነጋ የበግ ለምዱም ተገፏል። የወርቅ ቅቡ ዐብይ አሕመድ በአንጥረኛው እስክንድር ነጋ ለቅቋል። ዐቢይ አሕመድ ዝጓል። ስብከቱም፣ ፉገራውም አልቆበታል። እህል ውኃውም እንደዚሁ አብቅቷል። “ሳናጣራ አናስርም። አስረን አናጣራም” ውኃ በልቶታል። ገመናው ተገልጧል።
…እስክንድር እንደ ጠበል ያለ ነው። አምባገነኖችን መስቀል እንዳየ፣ ጠበልም እንዳረፈበት አጋንንት እንደሚያስለፈልፍ ካህን መሳይ ነው። እርቃናቸውን አቁሞ የውስጥ ደዌያቸውን የሚያሳይ የኤክስሬይ ማሽንም ነው እስክንድር። የፈለገ ሱፍ ብትለብስ የውስጥ ደዌህን የሚገልጥ ፍቱን ሃኪምም ነው እስክንድር። መለስ ዜናዊን፣ ኃይለማርያም ደሳለኝን፣ አሁን ደግሞ ዐቢይ አሕመድን ርቃናቸውን ያስቀረ፣ ሳይታገል የሚጥል ቦክሰኛ፣ በብእር ብቻ የሚያብረከርካቸው ጦረኛ፣ ብረት ነው እስክንድር። በሕግ፣ በመንግሥት፣ በፍትሕ የሚያምን፣ በመረጡት የትግል ስልት ገብቶ የሚደፍቃቸው። ባዶ እጁን ሰራዊት አሰልፈው የማይችሉት ኃያል ነው እስክንድር። ድል ለዲሞክራሲ፣ ኃይል የእግዚአብሔር ነው እያለ መብረቅ እንደመታው ዛፍ የሚያኮማትራቸው ነው እስክንድር።
… እስክንድር እንዲታሰር ስትወተውት የነበርከው የእስክንድር ጓደኛ ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና እንኳን ደስ ያለህ። ኢዜማዎችም እንኳን ደስ አላችሁ። ባለማዕተቡ እስክንድር ነጋ ግን ያሸንፋል። የምታመልኩት ዐቢይ አሕመድም ተሸንፏል።
ስለ እስክንድር ነጋ ጉዳት እና የችሎቱ ታዳሚዎች መታሰር !!
… ዋና ሳጅን መስፍን ይልማ የተባሉ የቂሊንጦ ወኅኒ ቤት የፈረቃ ኃላፊ በዛሬው ችሎት ፍርድ ቤት ቀርበው አቶ እስክንድር ነጋ እስር ቤት ውስጥ መደብደባቸውንና ጉልበታቸው ላይ መቁሰላቸውንም ለዳኞቹ መናገራቸው ተነግሯል። የደብዳቢዎቹን ማንነትና የደረሰባቸውን የጉዳቱን ዝርዝር ሁኔታ ግን ከመግለጽ መቆጠባቸውም ተሰምቷል።
… ከችሎት ወጥተው ወደየቤታቸውና ገሚሶቹም ወደ ማረሚያ ቤት ሄደው የአቶ እስክንድር ነጋን ጤንነት ለማየት ጉዞ የጀመሩ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የአዲስ አበባን ፖሊስ መለዮና የደንብ ልብስ በለበሱ የኦሮሚያ ፖሊሶች ታፍሰው፣ ተደብድበው መኪና ላይ ተጭነው መወሰዳቸውም ተነግሯል።
… እንደገና ወደ ፖሊስ ጣቢያ የተወሰዱትን ለመጠየቅ የሄዱ ቤተሰብ፣ ጓደኞችን ፖሊስ መጠየቅ አትችሉም ብሎ ደብድቦ ያባረራቸው ሲሆን ከደበደባቸው መሃልም ወስዶ ማሰሩም ተነግሯል።
ጠበቃ ሔኖክ አክሊሉ ታዳሚው ጥሎ ከወጣ በኋላ በቀጠለው ችሎት የተናገረው፦
አቶ እስክንድር ከተያዙበት ሰኔ 24 ጀምሮ አብሬያቸው አለሁ። ገና ሲያዙ ተደብድበዋል። ቃሊቲ ተደብድበዋል። በተደጋጋሚ ነው እየተደበደቡ ያሉት። ሌላም እስክንድር ላይ የሚፈፀም ስንታየሁ ላይ የማይፈፀም፤ ስንታየሁ ላይ የሚፈፀም እስክንድር ላይ የማይፈፀም አለ። ዛሬ እስክንድር ላይ ስለተፈፀመው ድብደባ ችሎቱ መነጋገር ያለበት እስክንድር በተሰየበት ነው። “ስንታየሁም እስክንድር ባለበት ነው ዝርዝሩን የምንናገረው” ብሏል። ፍርድ ቤቱ ይሄን ሃሳብ ይቀበልና ለሰኞ ተለዋጭ ቀጠሮ ይሰጠን። እኛ ጠበቆችም ቂሊንጦ ሄደን እናግኘው። “
…አባቴ … መውደቂያህ ሲደርስ በሆነው ባልሆነው ከህዝብ ጋር ወስዶ ያላትምህሃል። በታሪክ ህዝብን በኃይል እና በጉልበት ጥቂት ጊዜ የሚያንበረክክ እንጂ የሚያሸንፍ መንግሥት አልነበረም። ወደፊትም አይኖርም። የሚያሸንፍ ህዝብ እንጂ የሚሸነፍ ህዝብ የለም።
… ኃይል የእግዚአብሔር ነው !!