>

አሸባሪ  አለ! - ዘምሳሌ

አሸባሪ  አለ!

ዘምሳሌ


በኢትዮጵያ መሬት በስብሶ የበቀለ
የባሰ  ዘረኛ  እርጉም  መርዝ ያዘለ
ተቃዋሚ አሳሪ   ህዝብ  አሳዶ የገደለ
በጥላቻ ዳብሮ  ስርን  ያበቀለ
በስልጣን ሚባልግ  ውርስ የተቀበለ
የአምሀራውን ትውልድ ዋጋ ያስከፈለ

አሸባሪ አለ

መቼ ህዋት ብቻ የሀገሪቱ ችግር
ሰው የሚያሳርደው በወለጋ ምድር
በሸር የተሞላው ሴረኛው  አመራር
ሽሹ ውጡ እያለ  ጦር መሬት ሚገብር
ስልጣን ላይ ቁብ ያለ  ተንኮል ሚቋጥር
መቼ  ህዋት ብቻ የኢትዮጵያ ችግር

ሁልግዜ  ሚያሞኘን ሆድን እየነፋ
እርሻ ተኮር ሚለን ጦርነት ሲከፋ
የኢትዮጵያ በሽታ  በሀገር እየሰፋ
ሰንኮፉ  መርቅዞ መርዙን እየተፋ
ቃልኪዳኑን ትቶ መንግሥት  ሲንቀላፋ
በኢትዮጵያ  ምድር   ሽብር  እየከፋ

ምኑን ህዋት ብቻ ሀገር አሸባሪ
በንግስናም ያለ ህግ አውጪና ሻሪ
ዳኛው  ጦር  ፖሊሱ  ሸረኛው መሰሪ
ሌባው ጋዜጠኛ  ህዝብ  አደናጋሪ
ጨርሶ ካልፀዳ ይህ ሁላ ቦርቧሪ
ኢትዮጵያ አትድንም  ካልሆን ታሪክ ሰሪ!!!

Filed in: Amharic