>

ሦስተኛው እስክንድር ላይ መስካሪ የአዲስ አበባ ፖሊስ አባል ምስክርነቱን አሰምቷል...!!! (ዘመድኩን በቀለ)

ሦስተኛው እስክንድር ላይ መስካሪ የአዲስ አበባ ፖሊስ አባል ምስክርነቱን አሰምቷል…!!!
ዘመድኩን በቀለ

ስም… ያየህ ብርሃኑ ግዛው።
ዕድሜ…  28
ብሔር…  ዐማራ
ሃይማኖት… ኦርቶዶክስ
ሥራ… አዲስ አበባ ፖሊስ
የትምህርት ደረጃ… 10+1
አድራሻ… አዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 የቤት ቁጥሩን በማያውቀው ቤት ውስጥ የሚኖር።
… ፖሊስ ያየህ ብርሃኑ… የትዉልድ ስፍራው ምዕራብ ጎጃም አዴት ወረዳ ዳባል ቀበሌ ሲሆን የ10ኛ ክፍል ውጤት አልመጣለት ባለ ጊዜ ወደ አዲስ አበባ በመሄድ በፖሊስነት ሙያ የተቀጠረ የጎጃም ዐማራ መሆኑን የፖሊስ ያየህ ወዳጅ ዘመዶቹ ለእኔ ለዘመዴ መረጃውን ከነፎቶው ጀባ ብለውኛል።
…ዐቃቤ ሕግ ፖሊስ ያየህ በርሃኑን በእነ አቶ እስክንድር ነጋ ላይ 3ተኛ ምስክር ሆኖ እንዲቀርብ ያደረገው ሲሆን… አንዳንድ የሕግ ባለሙያዎች ግን የፖሊሱ ምስክርነት ከዐቃቤ ሕግ ይልቅ ለእስክንድር የሚጠቅም ነበር በማለት ሃሳብ ይሰነዝራሉ። የሆነው ሆኖ ዐቃቤ ሕግ ከመጋረጃ ጀርባ ካልመሰከሩልኝ ብሎ ያዙኝ ልቀቁኝ ብሎ ለምስክርነት የጠራቸው በሙሉ አሁን ማንነታቸውም… የሥራ መደባቸውም… ብሔራቸውም ጭምር ታውቋል።
… ፍርድ ቤቱ የዐቃቤ ሕግን 3ኛ ምስክር ለማድመጥ ተሰይሟል – ምስክሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ ባልደረባ ናቸው…!!!
ዳኛ፦ ስምዎትን ይንገሩኝ።
ምስክር፦ ያዬ ብርሃኑ
ዳኛ፦ የአያት ስም
ምስክር፦ ግዛው
ዕድሜ፦ 28
አድራሻ፦ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6
ዳኛ፦ የቤት ቁጥር?
ምስክር፦ ተከራይ ነኝ።
ዳኛ፦ የትምህርት ደረጃ
ምስክር፦ 10+1
ዳኛ፦ ዐቃቤ ሕግ ዋና ጥያቄውን መቀጠል ይችላሉ።
የዐቃቤ ሕግ ጥያቄዎች
‼ዐቃቤ ሕግ፦ ሊመሰክሩበት የፈለጉት ጉዳይ ምንድን ነው?
… ምስክር፦ በ26፤ 05 ነው። በቦሌ በሕገ ወጥ ሊገነባ የተሞከረ ቤተክርስቲያን ነበር። እገባለሁ አትገባም በሚል አቶ እስክንድር ወጣቶችን ለብጥብጥ ሊያነሳሱ ነበር።
‼ዐቃቤ ሕግ፦ካስነሱ በኋላ ምን ተከሰተ?
…ምስክር፦ አቶ እስክንድር ከሄዱ በኋላ ብጥብጥ ሊነሳ ነበር።
‼ዐቃቤ ሕግ፦በምን ምክንያት ነው ብጥብጥ የሚነሳው?
…ምስክር፦ አስቀድሞ የሞቱ ልጆች ስለነበሩ በእርሱ ምክንያት፤ ግን ሳይነሳ ቀርቷል። አቶ እስክንድር ሁለቱን ወጣቶች የኦሮሞ ፖሊስ ነው የገደላቸው ብለዋል።
‼ዐቃቤ ሕግ፦ ሥራዎ ምንድን ነው?
…ምስክር፦ ፖሊስ ነኝ።
‼ዐቃቤ ሕግ፦ በአካባቢው የኦሮሞ ፖሊስ አይተዋል?
… ምስክር፦ አላየሁም።
‼ዐቃቤ ሕግ፦ በ26/05/2012 ምን ተፈጠረ?
… ምስክር፦ የመንግሥት ተሽከርካሪዎች ተገልብጠዋል። ተቃጥለዋል።
‼ዐቃቤ ሕግ፦ አቶ እስክንድር መቼ መጡ?
…ምስክር፦ በ27/05/2012
‼ዐቃቤ ሕግ፦ መጥተው ምን አደረጉ?
…ምስክር፦ ወጣቶችን ይዘው ነበር የመጡት?
‼ዐቃቤ ሕግ፦ ከየት የመጡ ወጣቶች ናቸው?
…ምስክር፦ አላውቅም
‼ዐቃቤ ሕግ፦ ድንጋይ የወረወሩት የትኞቹ ወጣቶች ናቸው?
…ምስክር፦ እዚያው ሰፈር ያሉና ተሰብስበው የነበሩ ናቸው።
‼ ዐቃቤ ሕግ፦ ዋና ጥያቄያችንን ጨርሰናል።
(የጠበቆች መስቀለኛ ጥያቄ ይቀጥላል)
.
በነገራችን ላይ … ብሔርን ከብሔር ለማጋጨት ነው ተብሎ የተከሰሰው እስክንድር ነጋ ላይ ከሳሾቹ ዐቃቢያነ ሕጎቹን ጨምሮ እስከ አሁን ከፖሊስ ያየህ በቀር መስካሪዎቹ በሙሉ የኦሮሞ ነገድ ዐባላት ሆነው ተገኝተዋል። … የዐቃቢያነ ሕጎቹም በሙሉ ከአንድ ብሔር ማድረጉም መልካም አይደለም። ዐማራ ነው፣ ፀረ ኦሮሞ፣ ፀረ ቄሮ ነው የሚሉትን እስክንድር በቄሮ፣ በኦሮሞ ዐቃቢያነ ሕጎችና ምስክሮች መሟገት ደስስ አይልም።
1ኛ፦ ኦቦ ዮስያድ እጅጉ … ብሔር ኦሮሞ
2ኛ፦ ኦቦ ደመላሽ ኢጀታ… ብሔር…ኦሮሞ (ፎቶ የለኝም)
3ኛ፦ ኦቦ ሲሳይ ዱአ…  ብሔር … ?? እና  (ፎቶ የለኝም)
4ኛ፦ ኦቦ ፍቅሬ ዋቅጅራ… ብሔር ኦሮሞ (ፎቶ የለኝም) ናቸው።
… የሰላሌ ኦሮሞው ዐቃቤ ሕግ ዮስያድ እስከ ዩኒቨርስቲ ድረስ ኤርሚያስ እየተባለ ሲጠራ ከርሞ የኦህዴድ አባል ከሆነ በኋላ ግን ስሙን ወደ ዮስያድ በመቀየር ህይወቱ ሁሉ በአንድ ጊዜ መቀየሩ ነው ነው የሚነገረው። ስሙ ሀብት አመጣለት። ስሙ ሥልጣንም ከቆንጆ ሚስትም ጋር አመጣለት። ተተኮሰ ነው የሚሉት ወዳጆቹ። ዮስያድ ያልተረዳው ነገር ግን ሁሉም ሓላፊ መሆኑን ብቻ ነው። ትናንት ዳኛ ሆነው ወልቃይቶችን ዐማራ በመሆናቸው ሲያሸማቅቅ፣ መነኮሳቱን ሲያዋርድ የነበረው ዳኛ ዘርዓይ ዛሬ ቂሊንጦ ነው ያለው። አቦይ ስብሃት ዘብጥያ፣ ኦቦይ ፀሐዬ መቃብር ወርደዋል። ይሄን መረዳት መልካም ነው።
… አሁን ከዮስያድ በቀር የቀሪዎቹ የሦስቱ ፎቶግራፍ አልደረሰኝም። እንጂ ቢደርሰኝማ ኖሮ እነማን እንደሆኑ አልደብቃችሁም ነበር። የዐቃቢያነ ሕጎቹም ሆነ የመስካሪዎቹ ፎቶ ግራፍ እንደደረሰኝ ግን ሁላችሁም ታውቋቸው ለታሪክም ይቀመጥ ዘንድ አስተዋውቃችኋለሁ። የምታውቋቸው ተባበሩኝ።
… በህወሓት ጊዜ ጥቅላዩ ትግሬ፣ የጦር ኤታማዦር ሹሙ ትግሬ፣ የፖሊስ አዛዡ ትግሬ፣ የፍርድ ቤት ዳኛው፣ ዐቃቤ ሕጉ ትግሬ፣ የእስርቤት ሓላፊው ትግሬ። በጣም በጣም ይደብር ነበር። ይህ አሠራር እንዲቀየር ብዙዎች መታገል መሰዋታቸውንም አስታውሳለሁ። ታማኝ በየነ፣ አበበ ገላው፣ ፕሮፍ ብርሃኑ ነጋ፣ ሲሳይ አጌና፣ ፋሲል የኔዓለም፣ ደረጀ ኃብተወልድ፣ መሳይ መኮንን፣ ነአምን ዘለቀ፣ አንደዱአለም አራጌ ኧረ ስንቱ ተጠርቶ ስንቱ ይተዋል። ብዙዎች በሁሉ ቦታ የትግሬን የበላይነት በመቃወም በረሃ እስከመውረድ ሁሉ ደርሰው እንደነበርም ይታወሳል። አሁን ግን ሁሉም ዝም፣ ጭጭ፣ ምጭጭ። እኔ እስከአሁን የምቃወመው ይሄንን ፀያፍ ድርጊት ነው።
… ዴየስስም አይል።
Filed in: Amharic