>
5:13 pm - Monday April 20, 4522

"ክህደት ሁለተኛ ባህሪያችን እንዴት ሊሆን ቻለ? ??" (ጎዳና ያእቆብ)

“ክህደት ሁለተኛ ባህሪያችን እንዴት ሊሆን ቻለ? ??”
ጎዳና ያእቆብ

 

<<ሰው ሆይ፥ መልካሙን ነግሮሃል፤ እግዚአብሔር ከአንተ ዘንድ የሚሻው ምንድር ነው? ፍርድን ታደርግ ዘንድ (to do justly)፥ምሕረትንም ትወድድ ዘንድ (to love mercy)፥ከአምላክህ ጋር በትሕትና ትሄድ ዘንድ (to walk humbly with your God) አይደለምን?>> ትንቢተ ሚክያስ ፮፥፰ የሚለው የእግዚያር ቃል ሲነበብለት ያደገው ክርስቲያን ፍርድ የሚያጓድል ምህረት የሚባል ይልፈጠረበት እና ትህትና ባለፈበት ያላለፈ መሆኑ ምን ጉድ ነው?
 ሲደመር ምሁር ተብዬው ደግሞ ስነ ምግባር ያልፈጠረበት፣ ደፋር፣ ኩሩ፣ ባለጌና፣ ሆዱን የሚወድ፣ ነገን የማያይ፣ ለልጆቼ ምን አይነት ሀገር ነው ትቼ የማልፈው ብሎ የማያስብ እርስ ወዳድ፣ እንደ አሳማ ቢያይ ምድር ቢበላ አይነ ምድር የሆነው እንዴት ነው?! እንደ ሕዝብ ችግራችን ምንድነው?
የአቶ አበበ ገላው መወጣጠርና ቅቤ ላይወጣው እንደዚህ መብትን ሳይ ሀይማኖትም፣ ትምህርትም የህይወት ተሞክሮ እና እድል እንደማይለውጠን እንደማይዋሀደንና የተሻለ ሰው እንደማያደርገን ማሳያ ነው።
ይህንን ቅራቅምቦ ክስ እንደማያሸንፈው እርግጠኛ ሆኜ መናገር ብችልም አብሮት ከበላው ከጠጣውን ሰው ጋር መክሰስ ግድ ሆኖ ቢያስፈልግ እንኳን በዚህ ደረጃ enjoy ማድረግ የአይምሮ ብሽተኛነት ነው።
 ሰው እንድ ቀን አብሮ ማዕድ ከቆረሰው ሰው መጣላት፣ መካሰስን መናፍቅ የሚያሳየው ነገር ትልቅ ችግር ውስጥ እንዳለን ነው።
 ፀብ ሁሉ ልክ አለው።
 ደግነቱ ይህ አበበ ገላው የሚሉት ሰው ተደምሮም ተቀንሶም አንድ የማይሞላና ይዞት የነጣው ክስ ቅራቅምቦ መሆኑ እንጂ የህግ እውቀቱ እንደልቡ ቢሆን እንኳን ሰውን አምላክን የሚከስ ደፋር መሆኑ መርዳት ነው።
ለነገሩ ትልቁ ስኬቴ ሰው ላይ ጮኼ መግደል መቻል ነው ከሚል ሰው ምን የተሻለ ነገር ጠብቄ እንዲህ እንደምንጨረጨር እኔም  አይገባኝም።
Filed in: Amharic