የሽንፈት ጣረሞት ላይ ያለው ወያኔ!
(ሙላለም ገ/መድህን)
* “የተመድ ኃላፊ ለምን መፈንቅለ መንግስት አይደረግም ብሎኛል…!!!” ይለናልጌታቸው ረዳ
በጦርነት ሜዳም ሆነ በፖለቲካው መድረክ ወያኔ ጥቅሙን ለማሳካት ሲሮጥ የሚጠነቀቅለት ሕሊና እና ይሉኝታ የለውም፡፡ የዛሬ ፍላጎቱን ለማሟላት ሲጣደፍ እምነት ማጉደሉ ጉዳዩ አይደለም፡፡ ሰዎች ምን ይሉኝ ብሎ አያስብም! ጠዋት የተናገረውን ከሰዓት በኋላ ለመናድ ችግር የሌለበት፣ መርህን ቆርጥሞ የበላ ቁሞ ቀር ስብስብ ነው፡፡
በዚህ ጦርነት የበለጠ ገመናው አደባባይ የወጣበት ወያኔ፤ ባዶነቱ ተጋልጦ ራቁቱን ቁሟል፡፡ የፕሮፖጋንዳም ሆነ የጦር ስልቱ እጅግ ኋላ ቀር ከመሆኑ የተነሳ በስህተት ውስጥ መኖር ልማዱ አድርጎታል፡፡
ደሴና ኮምበልቻን በመውረር የቁስ ሰቀቀኑን ለማርካት ቋምጦ በወሎ ግንባር ያለ የሌለ ኃይሉን ይዞ መግባቱ ለከፋ ኪሳራ ዳርጎታል፡፡ በተለይም ኩታበርና ቦሩ ሜዳ ላይ የገጠመው ኪሳራ በአይነቱ የተለየ ነው፡፡ በወገን በኩል በእግረኛው፣ በሜካናይዝዱና በኮማንዶው ከመቀጥቀጡም በላይ በጦር ጀት፣ በድሮን ድብደባ እየረገፈ ነው፡፡
ከዚህ የተረፈው በየጎጡ እግሬ አውጭኝ ሲል ከጀግናው የወሎ ሚሊሻ፣ ፋኖና የአርሶ አደሩ ጦር እጅ ወድቆ ትግሬነቱን እስከሚረግም ድረስ በጥይት አረር እየተለበለበ ነው፡፡
በወሎ ግንባር ወራሪው መንጋ እንደቅጠል መርገፉ ሳይሆን የሚያስገርመው ሞትን የትግል መሳሪያ ማድረጉ ነው፡፡ በዓለም የውጊያ ታሪክ ውስጥ ለመሞት በሰልፍ የሚመጣ ቢኖር የትግሬ መንጋ ብቻ ሳይሆን አይቀርም፡፡
ጂኦግራፊን ጠንቅቆ ከማወቅ ጀምሮ ሰፊ የሆነ የ ‘Fire Power’ ብልጫ ያለው የወገን ጦር ሊገድለው የመጣውን መግደል እስከሚሰለቸው ድረስ በምድር በሰማይ እሳት እያዘነነበት ነው፡፡ አሁን የሚያሰጋው የጠላት ጥይት ሳይሆን እግር መጣያ ያስጠፋው የጠላት ሬሳ ክርፋት አገሬውን ለተስቦ በሽታ እንዳይዳርገው ነው፡፡ የጠላትን በድን ሬሳ ሰብስቦ ለመቅበር በራሱ አንድ ብርጌድ የሰው ኃይል ያስፈልጋል፡፡
እውነታው ይህ በሆነበት ሁኔታ እነ ደብረጺዮን ሽንፈታቸውን በጸጋ መቀበል አቅቷቸው ‹ጦርነቱ አብቅቷል፤ እጅ ስጡ› ማለት ጀምረዋል፡፡ ማን ነው እጅ ሰጭው? ‹መግደል የሰለቸው የወገን ጦር?› ‹ምን ብሎ እጅ ይስጣችሁ?› መግደል ሰለቸኝ ብሎ?… መቼም ነውር ጌጣቸው ነው፡፡ በገዛ ወገናቸው ሞት የሚነግዱ ህሊና ቢሶች ናቸው፡፡ ሃፍረትም፣ ነውርም ሆነ ምን ይሉኝን የማያውቁ በመሆኑ ነገም በዚሁ ህሊና ቢስነታቸውን መቀጠላቸውን አያቆሙም። የወገን ጦር ሚና ወደሲዖል መወርወር ነው።
እዚህ ወሎ ላይ የነሱ መንጋ የአስከሬን ሽታ አገሬውን ለተስቦ በሽታ እንዳይዳርግብን ስጋት ገብቶናል፣ እነሱ ሌላ ቀልድ ያመጡብናል፡፡ የትግራይ እናቶች ጡታቸውን አፍርጠው እነደብረጺዮንን የሚራገሙበት ጊዜ ተቃርቧል፡፡ ልጆቻው እንደወጡ ቀርተዋልና፡፡
ከጥቅምት እስከ ጥቅምት የረገፈው ትግሬ 400 መቶ ሺህ ደርሷል፡፡ አሁን ያለጥርጥር በትግራይ የአንድ ትውልድ ክፍተት አጋጥሟል፡፡ ወንድ ብርቅ የሆነበት ክልል ተፈጥሯል፡፡ በረሃብ ከምሞት እየበላሁ ልሙት የሚለው የመንጋው “የትግል መርህ” ሩቅ የሚያስኬድ አልሆነም፣ የአማራ አርሶ አደርን ጎተራ ገልብጠው የበሉት ሳይስማማቸው በየግንባሩ እየረገፉ ነው፡፡
ኑረውም ታግለውም አላማረባቸውም፡፡ ከውሻ ሞት የከፋ ሞት እየሞቱ ነው፡፡ የወገን ጦር መግደል እስከሚሰለቸው ድረስ ጠላትን ወደትቢያ እየቀላቀለ ነው፡፡ ትንቢቱ እየተፈጸመ ነው፤ ወሎም በእርሳሱ አርከባስ እያለ እየነቀላቸው ነው፡፡ በርግጥም የጦርነቱ ፍጻሜ ወሎ ላይ ነው፡፡ የሽንፈት ጣረ ሞት ላይ ያለው ወያኔ ጨርሶ ወደመቃብር ለማውረድ ትመም ወደወሎ! የዐማራና የኢትዮጵያ ጥንተ-ጠላት የሆነውን ወያኔን በመቅበር ወሎ ላይ የማይሞት ታሪክ ስራ!!
ተያያዥነት ያለው ቁንጽል መረጃ:-
“የተመድ ኃላፊ ለምን መፈንቅለ መንግስት አይደረግም ብሎኛል።”
ጌታቸው ረዳ
ጌታቸው ረዳስ በየቀኑ፣ በየሰዓቱ ቃለ መጠይቅ ባደረገ። ሚስጥር ሲያሾልክ ነውኮ የሚውለው። በትናንትናው ቃለ መጠይቅ አንድ የተመድ የስራ ኃላፊ ለምን ወታደሮቹ ሰብሰብ ብለው ይህን ሰውዬ አያስወግዱትም ብሎ ጠየቀኝ ይላል። ተመድ ገለልተኛ ነው ተብሎ ይታሰባል። ለእነ ጌታቸው ግን ሲያማክር የሚውለው የተመድ ኃላፊ ነው። ያውም ስለ መፈንቅለ መንግስት። ራሱ ጌታቸው የመሰከረው ነው።