>
5:14 pm - Tuesday April 20, 1897

እምዬ ሚኒልክ፣ እቴጌ ጣይቱ ብጡል እና ፊታዉራሪ ገበየሁ በጳውሎስ ኞኞ ብእር...!!!

እምዬ ሚኒልክ፣ እቴጌ ጣይቱ ብጡል እና ፊታዉራሪ ገበየሁ በጳውሎስ ኞኞ ብእር…!!!
በጋሻው ምስጋና

* አጼ ምኒልክ አርሲን ለማስገበር አገሩን ይዘዉ ነበር፡፡ የአርሲ ኦሮሞ አልገዛም እያለ በማስቸገሩ በድጋሚ ዘመቱ፡፡ የሚኒሊክ ሰራዊት በድጋሚ እንደተመለሰ ያልሰማዉ የአርሲ ኮጂ የሚባለዉ ባላባት አርሲን በሚገዛዉ ባላባት ላይ ዘምቶ ብዙ ሰዉ ጨፈጨፈ፡፡ ዘረፈ፡፡
ከእልቂቱ የተረፈች አንዲት ሴት ሚኒሊክ ወደ ሰፈሩበት ስፋራ መጥታ የሆነዉን ተናገረች፡፡ ሚኒሊክም እርዳታ ለባላባቱ ላኩ፡፡ በድጋሚ ለዘረፋ የመጣዉን የኮጂ ሰራዊት የሚኒሊክ ሰራዊት ፈጀዉ፡፡ ብዙ የአርሲ ሰዎች በሚኒሊክ ሰራዊት ተማረኩ፡፡ ተዘረፉ፡፡ ሰራዊቱም የማረከዉን ሰዉ ባሪያ አድርጎ ያዘ፡፡
እምዬ ሚኒልክ ይሄንን አዋጅ አወጁ “ . . . አሩሲን ከግራኝ ወዲህ የገዛዉና ያስገበረዉ የለም፡፡ እኛ ጥንትም የኛ ነዉ በማለት መጣንበት እንጂ እርሱ አልመጣብንም፡፡ ባለማወቁ እከላከላለሁ ብሎ አለቀ፣ ተጎዳም፡፡ ግን ባሪያ አድርገን ልንገዛዉ አይገባንም፡፡ ወንድማችን ነዉና የማረከዉን የሰዉ ምርኮኛ ሁሉ ልቀቀልኝ፡፡ በአዋጅ ከለመንሁህ በኃላ ወስልተህ የአርሲን ሰዉ ባሪያ አድርገህ የያዝህ ከተገኘህ እጣልሃለሁ፡፡ ልቀቅ ብያለሁ እና ልቀቅ፣ ላምና ከብቱ ለስንቅ ይበቃሃል፡፡”
*   *    *
ነሃሴ ፲፪…የእምዬ ሚኒልክ እቴጌ ጣይቱ ብጡል (ብርሀን ዘ ኢትዮጵያ)ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ(አባ ጎራው)የልደት ቀን:-
የቀድሞው የአሜሪካ ፕረዘዳንት ጆንኦፍ ኬኔዲ ” በምድር ላይ ጀግና ጥራ ብትሉኝ ቀድሜ ምጠራው የንጉስ ሚኒሊክን ነው ደርባባና ደፋር ናቸው።
”ባልና ሚስት ካንድ ውሃ ይቀዳል ሲባል እንጅ በአንድ ቀን መወለዳቸውንስ ሰምተንም አናውቅም”
ብለዋል!
አፄ ምኒልክ ከአባታችው ከሸዋው ንጉሥ ኃይለ
መለኮት ሣህለ ሥላሴና ከእናታቸው ወይዘሮ እጅጋየሁ ለማ አድያም ቅዳሜ ነሐሴ ፲፪ ቀን ፲፰፻፴፮ ዓ.ም. ደብረ ብርሃን አካባቢ አንጎለላ ከሚባል ሥፍራ ተወልደው፤ በአንጎለላ መቅደላ ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ክርስትና ተነሱ።
አያታቸው ንጉሥ ሣህለ ሥላሴ የልጁን መወለድ ሲሰሙ “ምን ይልህ ሸዋ” በሉት ብለው ስም አወጡ። እሳቸው “…ምኒልክ በሚል ስም የሚነግሥ ንጉሥ ኢትዮጵያን ታላቅ ያደርጋታል”
የሚል ትንቢት ስለነበር ‘ምኒልክ’ የኔ ስም ነው ብለው ነበር።
ሆኖም፣ በህልማቸው ከልጁ ጋር አብረው ቆመው ከሳቸው ጥላ የልጁ ጥላ በልጦ፤ የረገጡትን መሬት ሲያለካኩ እሳቸው ከረገጡት ልጁ የረገጠው ረዝሞ አዩ። ከዚህ በኋላ “ምኒልክ የኔ ስም አይደለም። የሱ ነው። ስሙን ምኒልክ በሉት” ብለው አዘዙ
* እቴጌ ጣይቱ ብጡል«ብርሃን ዘ ኢትዮጵያ» በሚል ቅፅል ስም የታወቁት እቴጌ ጣይቱ ከአባታቸው ደጃዝማች ብጡል ኃይለ ማርያም እና ከእናታቸው ወይዘሮ የውብ ዳር ነሐሴ ፲፪ ቀን ፲፰፻፴፪ ዓ/ም በጌምድር ውስጥ ደብረ ታቦር ከተማ ተወለዱ። በየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስርዓት መሠረት በተወለዱ በ ፹ ቀናቸው ጥቅምት ፳፯ ቀን ፲፰፻፴፫ ዓ/ም በደብረ ታቦር ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ክርስትና ተነሡ። በልጅነት ዘመናቸው በዚሁ ደብር ውስጥ ዳዊትን ሲከታተሉ ከቆዩ በኋላ በጊዜው ይሰጡ የነበሩትን ሌሎች የሃይማኖት ትምህርቶች በየታላላቁ አድባራት በመዘዋወር
ያጠናቀቁ ስለመሆናቸው ታሪክ አዋቂዎች ይናገራሉ። የተማሩባቸውም መፃሕፍት ተጽፈው ይገኙ የነበረበትን የግዕዝ ቋንቋ አጣርተው ያውቁ ነበር።
* ፊታዉራሪ ገበየሁ ገቦ(አባ ጎራዉ)በነሐሴ 12.1836 አ.ም አንጎለላ ልዩ ስሙ
*አስታ ቆላ ጌጠር* በምትባል ስፍራ ተወለዱ። ክርስትናም የተነሱት በፅርሀ አርያም አንጎለላ ኪዳነ ምህረት ነዉ። ፊታዉራሪ ገበየሁ ዉልተታቸዉምም
እድገታቸዉም ብሎም የእምዬ ምኒልክ የጦር ሚንስተር እስከመሆን የበቁት እዚሁ አንጎለላ ነዉ።
እኚህን ጀግና ስናስታዉስ ኢትዮጵያዊነት ምን ያክል እረቂቅ መሆኑን እንረዳለን ፊታዉራሪ ስለሀገራቸዉ ደማቸዉን የገበሩ ጀግና የጦር አበጋዝ እንደነበሩ ታሪክ ይነግረናል።
የንጉሰ ነገስቱ የመሀል ጦር አዛዥ ፊታውራሪ
ገበየሁ ከጣልያኖች ጋር በተደረገው በሁሉም ጦርነት የተመሰከረላቸው ጀግና ነበሩ፡፡ የአምባላጌውን ምሽግ በመስበር በጣሊያን ላይ የመጀመሪያውን የድል ደውል ያሰሙት እና ዋናው የድሉ ባለቤት እሳቸው ነበሩ፡፡በዚህም ምክንያት
በወቅቱ የፈረንሳይ ጋዜጦች “የአምባላጌው የኢትዮጵያ  ጀግና” በማለት እንዳወደሷቸው  ተፅፏል፡፡
Filed in: Amharic