>

ጋዜጠኛ ጌጥዬ ያለው ታሰረ - በሚኒሊክ ቲቪ ጋዜጠኛ አዲሱ ደርቤ ላይ ክስ ተመስርቷል...!!! (አሌክስ ሸገር)

ጋዜጠኛ ጌጥዬ ያለው ታሰረ –   

በሚኒሊክ ቲቪ ጋዜጠኛ አዲሱ ደርቤ ላይ ክስ ተመስርቷል…!!!

አሌክስ ሸገር

በእነ እስክንድር ችሎት የችሎቱን የየለት ሂደት የሚፅፈው ጋዜጠኛ ጌጥዬ ያለው ቀደም ሲል በአቃቤ መንግስት በተመሠረተበት በፌስ ቡክ ላይ ችሎቱን በመተቸት ክስ  ማረሚያ ቤት ቆይቶ ሠኞ አራት ሠአት ላይ ለውሳኔ ችሎት እንዲቀርብ ፍ/ቤቱ ትዕዛዝ ሠጠ
በተያያዘ ዜና አቃቤ መንግስት በሚኒሊክ ቲቪ ጋዜጠኛ አዲሱ ደርቤ ላይ ክስ መስርቱአል።
የመናገር እና የመፃፍ መብት ዳግመኛ ዛሬም በነ አብይ አህመድ መንግስት ተቀብሩአል!
ድፍን የአዲስ አበባ ህዝብን እጅግ አፀያፊና አስነዋሪ ስድብ የተሳደበው አንጋሳ ፓርላማ በገባበት ሀገር ላይ በፌስቡክ ትችት ክስ መመስረት የስርአቱን አስከፊነትና ስርአቱ ለማን እንደቆመና በአዲስ አበባ ህዝብ ነፃነት ላይ እንደቆመ እና አፈናው እየባሠ እንደመጣ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ  ነው።
በተያያዘ ዜና በነ እስክንድር ላይ በሃሰት ሲመሠክር የነበረው ስድስተኛው የአቃቤ መንግስት ምስክር ወርቁ ታደሠ ቶላ ላይ ሲቀርብ የነበረው የመስቀለኛ ጥያቄ ዛሬም ባለመጠናቀቁ ለማክሠኞ ጠዋት ተቀጥሩአል
ባያውቁን ነው እንጂ ተደጋጋሚ እስር አይደለም ሞት ሠላማዊ ትግላችንን አያስቆመንም!”

ከኢትዮጵያ ዋና ከተማ

አዲስ አበ

Filed in: Amharic