>

አሳፋሪው መንግስት....!!! (አቤል ዘመነ)

አሳፋሪው መንግስት….!!!

አቤል ዘመነ

 

በኦሮምያ እና በሌሎች ክልሎች የጦር መሳሪያዎች ካዝና አጨናንቀዋል አማራና አፋር በቋጥኝና በዱላ ይዋደቃል… ይፈጃል ብለው ይቀላል!
ነገሮች አቅጣጫቸውን ስተዋል የአገሪቱ መንግስት በንፁሀን ዜጎች ህልውና ላይ ቆምሮዋል። ይህ ትልቅ ታሪክ ነው እጅግ በጣም ትልቅ የአፋር ህዝብ እንደ ቅጠል ሲረግፍ ንፁሀን ዜጎች መሳሪያ አተው በዱላ አቅም ህይወታቸውን ለማትረፍ ሲዋደቁ በኦሮምያ በሶማሌ በደቡብ እና በቀሪወቹ ክልሎች የጦር መሳሪያወች ተከዝነው ተቀምጠዋል። ምንም ያላጠፋው የደሴ ሰላማዊ ህዝብ ያለ በደሉ እንደ ቅጠል ሲረግፍ በተመሳሳይ እንደ አፋር በዱላ ሳይቀር ከታጠቀ ሀይል ጋር ተዋድቆዋል remember this history ሰላማዊ ንፁሀን ያለበደላቸው ሲረግፉ የአገሪቱ ህዝብ እና መንግስት ከጦር መሳሪያ አቅም እንኳን ነፍጎዋቸው አልቀዋል።
በደሴ የታየው ይህ ክስተት ወደ አለም ሚዲያወች ሳይቀር ደርሶዋል How dare the country government let innocent civilians to protect themselves with sticks,knifes and swords ሲሉ የአብይ አህመድ መንግስትን ክፋት አጋልጠዋል።
በብዙ ክልሎች ተከዝኖ ያለ የጦር መሳሪያ ለሚዋደቁት የሁለቱ ክልሎች ተነፍጎ ንፁሀን እንደ ቅጠል እንዲረግፉ ሆነዋል። ይህ ታሪክ ለአገሪቱ ጥቁር ታሪክ ይሆናል። ብዙ የጦር አመራሮች እጅጉን ከማዘን አልፈው ይህ እንዲሆን ያደረገው የብልፅግና አመራር እንደሆነ በሚገባ ገልፀውልናል በመከላከያ ሰራዊቱም ዘንድ መከፋፈል ፈጥሮዋል የተከበረ ጦር ያላት አገር ላይ በሴራ ፖለቲካ መንግስት ንፁሀኑን ሊታደግ ሲገባው እራሳቸውን በዱላ ይከላከሉ ብሎ ለሞት ጎርፍ የዳረገ መንግስት ነው ይህ የዚችን አገር የወታደር ዩኒፎርም ለለበሰ ሁሉ ውርደት ነው ያሉም አሉ። ሶስት ከፍተኛ የጦር አመራሮች በከፍተኛ ቁጣ ተዋርደናል ሲሉም ነው ያስረዱት።
የዝች አገር ጦር በቁም ተዋርዶዋል በታሪክ ያልበደሉ ንፁሀን ሰላማዊ ዜጎች ለነብሳቸው ከታጠቀ ሀይል ጋር በዱላ እስኪዋደቁ ድረስ ቆሞ ከማየት በላይ ውርደት የለም
Filed in: Amharic