>

ሌላም ሀውልት አለ (ዘምሳሌ)

ሌላም ሀውልት አለ


ይድረስ ለኢትዮጵያውያን
ከአኖሌም  በላይ  ሌላም ሀውልት አለ

ኢትዮጵያን የሚያምስ ሕዝብ ሚያተራምስ
እርስበርስ ሚያናክስ ስብእና ሚያረክስ
መተሳሰብ ቀርቶ በዘር ሚያልከሰክስ
ተገንብቶ ሚናድ የማይረጋ ጥንስ
ሀገር የሚያናጋ ልማት ሕዝብ የሚያፈርስ

ሌላም ሀውልት አለ
ዘረኝነት ሚባል ከውስጥ የበቀለ
ኋላቀርነትን ሙጥኝ ብሎ ያለ
እኔ ለኔ የኔ ብሎ እየታበለ
ሀበሻን አናክሶ በፀብ ያጋደለ
ቁልቁለት የሚጓዝ ችግር የቆለለ

ከአኖሌ የባሰ አለ ዘረኝነት የህዝባችን
እውነት
እንደአክሱም የቆመ ዘልቆ ከውስጥ አንጀት
አንድ  ብቻ አደለም የጥላቻው  ሀውልት
በውስጣችን ያለው ሆኖ በእኛ መንግሥት
ሚሊዮኖች ቁጥር ተከታዮቹ ያሉት

ሁሉ እየኖረ ተሞልቶ  ጥላቻ
በዘመን ሳይዋጅ ሆኖ ለየብቻ
ባለፈ ትርክቱ  ታሪክ  መጓተቻ
ፓርቲ ቅራንቅንቦ  በሀሰት ጋብቻ
ሰርዞ ደልዞ ህግ አርጎ መጫውቻ

መቼ አኖሌ ብቻ ሌላም ካልፈረሰ
የጥላቻው  ሀውልቱ ልቡ ካልታደሰ
ዘረኝነት ፅንሱ  ውልደቱ እየባሰ
አልፎ ሂያጁ መሪም በእርሱ እየታደሰ
የእግዜር ደጃፍ ሳይቀር ሄዶ እየለወሰ

ፍፅሞ ካልዳነ ጭንቃላቱ ጠርቶ
በበቀል ከኖረ  ጥላቻ ተመልቶ
ሀገር ካልታደገ  መልካም ሀሳብ መልቶ
እንዴትስ ይፈርሳል  ምልክት ገንብቶ
ካኖሌ የሚልቅ ጥልቁን ጥላቻ ግንብ
በልቡ አስቀርቶ !!!

Filed in: Amharic