>

ቀይ መስመር !!! [መስፍን ማሞ ተሰማ]

ቀይ መስመር !!!

መስፍን ማሞ ተሰማ

በኢትዮጵያ አንድነትና ሉዐላዊነት፣ ነፃነትና ታሪክ የሚያምን ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሊያልፈውም ሆነ ሊደፍረው ከቶም የማይገባ አይነኬ /taboo/ የሆነ ፍፁም ሀቅ አለ። ከሶማሌያ ወረራ እስከ ናቅፋ ተራራ በኢትዮጵያ ሠንደቅ ዓላማ ሥር ስለ ለኢትዮጵያ ህልውና የተዋደቀውን የመከላከያ ሠራዊት በቅድመ 1983 ዓ/ም የትህነግ (ወያኔ) ጉድፍ ትርክት “የደርግ ሠራዊት” በማለት ታሪክ ሲያጠለሽና ጊዜ ሰጥቶትም ሠራዊቱን በትኖ በማዋረድ የፈፀመውን ዘግናኝ ግፍ ትውልድና ኢትዮጵያ ከቶም የምትረሳው አይደለም።
እነሆ ደግሞ ከ1983 ወዲህ በ30 ዓመቱ በጥቅምት 2013 ናዚስት ትህነግ በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ላይ በቃላት ቀመር ሊገለፅ ከሚችለው በላይ የሆነ ዘግናኝ ግፍና ጭፍጨፋ በሰሜን ዕዝ ላይ ፈፀመ። እነሆም ኢትዮጵያ ከናዚስት ትህነግና ከሚመራው የሲዖል ሠራዊት ጋር የህልውና ጦርነት ውስጥ ከገባች አንድ ዓመት ሆናት። ናዚስት ትህነግ የሲዖል ሠራዊቱን በአፋር፣ በጎንደርና በወሎ አሰማርቶ ሳጥናኤላው ግፍና ዕልቂት እየፈፀመ ይገኛል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትና ሕዝባዊ ሠራዊቱ (ልዩ ሀይላት፣ ፋኖ፣ ሚሊሺያ) ኢትዮጵያን ወደ ሲዖል አወርዳታለሁ ብሎ የዛተውንና የሚዳክረውን ናዚስት ወረራ እየመከቱና ወደ ግብዐተ መሬቱ እየወሰዱት ይገኛሉ።
ከናዚስት ትህነግና ከሚመራው የሲዖል ሠራዊት ጋር የሚዋደቀውንና የኢትዮጵያ ህልውና መከታ የሆነውን የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትን እንደ አንድ ሀገራዊ ተቋም ‘ የብልፅግና ፓርቲ ወይም የአብይ ሠራዊት’ ብሎ መፈረጅ በኢትዮጵያ ህልውና ቀይ መስመር ማለፍና የወያኔን ይቅር የማይባል ስህተትና ወንጀል መድገም መሆኑ ሊታወቅ ግድ ይላል!!!! ማንም ይሁን የትም እንደ አካይስት ወያኔ የኢትዮጵያን መከላከያ ሠራዊት በግለሰብና በፓርቲ ስም አውርዶ የሚፈርጅ የናዚስት ትህነግን ታሪካዊ ወንጀል እየፈፀመ መሆኑን ነው የማምነው። ይህ የማይናወጥ አቋሜ ሀገራዊና ኢትዮጵያዊ እንጂ የብልፅግና ፓርቲ አባል ወይም የጠ/ሚር አብይ ተከታይ – መሆን አለመሆን – ጉዳይ አይደለም፣ ሊሆንም አይገባም – ብዬ በፅኑ አምናለሁ!!! የናዚስት ትህነግ የማያዳግም ሞት የኢትዮጵያን ህልውና  ማረጋገጫ ሀውልት ነው!!!
ድል ለኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት!!!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝባዊ (ልዩ ሀይላት፣ ሚሊሺያ፣ ፋኖ) ሠራዊት!!
ኢትዮጵያ ታሸንፋለች!!!
Filed in: Amharic