>

 " ምስክሮቹ ጎበዝ ናቸው ቀሽሙ ስክሪፕት ፀሀፊው ነው "  እስክንድር ነጋ

ወደ ችሎት ስንመለስ.. !!;

ሰለሞን አላምኔ

....  ” ምስክሮቹ ጎበዝ ናቸው ቀሽሙ ስክሪፕት ፀሀፊው ነው ” 

እስክንድር ነጋ

በእነ እስክንድር ነጋ መዝገብ ላይ አቃቢ ህግ ምስክሮቹን ማሰማት ከጀመረ አንድ ሳምንት አልፎቷል። ካለፈው ሳምንት የቀጠለ 6ኛ ምስክር ወርቁ ነገ ማክሰኞ (23.02.2014) ከጠዋቱ 3 ሰዓት ከቆመበት ቀጥሎ መሰማት ይጀምራል።
ያለፉት ምስክሮች በእነ እስክንድር ነጋ ላይ ሊያሰፍርድ የሚችል የምስክርነት ቃል እንዳልፈፀሙ በችሎቱ የተገኙ ገለልተኛ ሰዎች የሚዲያ ባለሙያዎች እና ሌሎች በርካታ ከጉዳዩ ጋራ ተያያዥነት የሌላቸው ሰዎች ሲናገሩ ሰምተናል ምንም እንኳን በህግ የተያዘን ጉዳይ ለከፈተኛው ፍርድ ቤት መተው ቢኖርብንም።
ነገ ረፋዱ 3 ሰዓት ላይ ችሎቱ ምስክር የማሰማት ሂደቱ የሚቀጥል ይሆናል፣ የምስክሮቹን እና የአቃቢ ህግን ሂደት እንዴት አየኸው ብየ ትላንት ቂሊንጦ ለጠየቁት መልስ እስክንድር የሰጠኝ መልስ ” ምስክሮቹ ጎበዝ ናቸው ቀሽሙ ስክሪፕት ፀሀፊው ነው ” ብሎ እንዳሳቀኝ ሁሉ ይህንን ተከታታይ ድርማ ፤ ምን አይነት ስርዓት ላይ ሀገሪቱ እንደወደቀች መመልከት በታሪክ አጋጣሚ የተሰጠን እድል ነውና እንደተለመደው ኢትዮጲያዋውያን በልደታ ፍርድ ቤት በማለዳ በመገኘት ይህንን ታሪካዊ ችሎት እንድትከታተሉ እንጋብዛችኋሏን።

በ ማለዳ ልደታ ፍርድ ቤት እንገናኝ።

Filed in: Amharic