>

"ልናይ ማታ ....!!!" (ሀብታሙ አያሌው)

ልናይ ማታ ….!!!”

ሀብታሙ አያሌው

ፕሬዘዳንት ሳህለወርቅ “ጉዳዩን በውይይት በንግግር መፍታቱ ይሻላል”  ብለው ሲናገሩ ፤ የኢኮኖሚ ሚንስትር ዴኤታው እና የጠቅላዩ የቅርብ ሰው ዶ/ር ኢዮብ “የፖለቲካ ልዩነቱ በንግግር ይፈታ”  የሚል ጥቆማ በቲውተር ገፃቸው ሲያሰፍሩ፤ የሁለቱን ጥቆምታ አሰላስዬ ሳልጨርስ  በፋሲል የኔዓለም በኩል “ይሄ ነገር በድርድር በውይይታ የሚፈታበትን እድል ማየት ጠቃሚ ነው” የሚል ጽሑፍ ለንባብ ሲቀርብ ይህ ገደምዳሜ ወዴት ወዴት እያዘነበለ ነው ብዬ ጥያቄ አንስቼ ነበር።
አሁን ደግሞ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዴኤታው ሬድዋን ሁሴን “ዲፕሎማቶችን ሰብስቦ እኛ ለሰላም ለድርድር ዝግጁ ነን እናንተ ህወሓት ላይ ጫና አድርጉ”  ሲል የመንግስትን አቋም ግልፅ አደረገ፤ እሱን ተከትለው የጠቅላዩ ጽ/ቤት ኃላፊ እና የፍትህ ሚንስትሩ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ ትላንት ለ VOA “ህወሓት ከአማራ እና አፋር ክልል ይውጣና እንደራደር” የሚል ቃል ተናገሩ፤  እናማ … ገደምዳሜው በደምብ እየተጋደመ ይሆን ብዬ  ሳሰላስል ቆየሁ።  እንዲደቅቅ የተፈረደበት መድቀቁ ከተረጋገጠ በኋላ  ሁኔታው ወደ ሽምግልና  እንዲያመራ  ተወስኖ ይሆን ?  በርካታ ጥያቄዎች በህሊናዬ እየተመላለሱ ለሊቱ ተጋመሰ።
እንዲህ ያለ ነገር ሲገጥመኝ ቶሎ ወደ ህሊናዬ የሚመጣው “ልናይ ማታ”  የሚለው የሴቷ አያቴ ቃል ነው።
ልናይ ማታ   –  ክፍል ሁለት 
————– //————-
በዕለተ ሰንበት –  የተባበሩት መንግሥታት የእርዳታ ማስተባበሪያ ኃላፊ   Martin Griffiths የአፍሪካ ህብረት ልዩ መልዕክተኛ    Olusegun Obasanjo ከአራት ኪሎው ሰባተኛው ንጉሥ አብይ አህመድ ይቅናችሁ የሚል ቡራኬ ተቀብለው ከአዲስ አበባ ኤርፖርት ወደ መቀሌ ተሸኝተዋል።
ትላንት –  እኔ ባለሁበት አገር ከእኩለ ሌሊት በኋላ፣  በአገሬ በኢትዬጵያ ቅዳሜ ለሊት ለእሁድ አጥቢያ  ጎህ ሲቀድድ አንድ ጽሑፍ አስነብቤ ነበር።
ህዝብ አዳም  በቡራኬ ስለተሸኙት አደራዳሪዎች መረጃ የለውም።  አርቲስት ታሪኩ  (ዲሽተ ጊና)’ን ሲያወግዝ ዋለ።
 “ልናይ ማታ”    የሴቷ አያቴ  ቃል !
  ተራራው Vs  ተላላው
Filed in: Amharic