>
5:33 pm - Sunday December 6, 5114

ኦነግ ለህወሀት ጦሩን ወደ ኦሮምያ ድምበር እንዳያስጠጋ ማሳሰቢያ ሰጠ...!!! (D.W)

ኦነግ ለህወሀት ጦሩን ወደ ኦሮምያ ድምበር እንዳያስጠጋ ማሳሰቢያ ሰጠ…!!!
D.W

በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር(ኦነግ) “ህወሀት ወደ ኦሮሚያ ክልል የሚያደርገውን ጉዞ” እንዲገታ ጠየቀ፡፡ ወደ አማራ እና አፋር ክልሎች በተስፋፋው የትግራዩ ጦርነት ሕወኃት ሰሞኑን በአማራ ክልል ደሴ እና ኮምቦልቻ ከተሞችን ተቆጣጥሮ ወደ መሃል አገር እንደሚገፋ አሳውቆ ነበር፡፡
ከሰኔ 21 ቀን 2013 ዓ.ም. የኢትዮጵያ መንግስት የተናጥል የተኩስ አቁም ውሳኔ ወዲህ ወደ አማራ እና አፋር ክልሎች በተስፋፋው የትግራዩ ጦርነት ሕወኃት ሰሞኑን በአማራ ክልል ደሴ እና ኮምቦልቻ ከተሞችን ተቆጣጥሮ ወደ መሃል አገር እንደሚገሰግስ አሳውቆ ነበር፡፡ይህንኑን ተክትሎም ነው ኦነግ ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ ሕወኃት “የኦሮሞ ህዝብን ሉዋላዊነት እንዲያከብር እና የጦር ሀይላቸውን ወደ ኦሮሚያ ድንበር ውስጥ ከማስገባት እንዲቆጠቡ” ሲል ያሳሰበው።የፓርቲው ቃል አቀባይ ለዶይቼ ቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ አሁን ላይ በትግራዩ አማጺያን እና መንግስት መካከል የሚካሄደውን ጦርነት ትርጉም አልባ በማለት የሚደረጉ የክተት ጥሪዎችንም ነቅፈዋል፡፡
Filed in: Amharic