>

ከመንዝ የተላከ አፋጣኝ እርምጃ የሚሻ የድረሱልን ጥሪ ...!!! (አቻምየለህ ታምሩ)

ከመንዝ የተላከ አፋጣኝ እርምጃ የሚሻ የድረሱልን ጥሪ …!!!

አቻምየለህ ታምሩ

ሰላም ወንድሜ። ይህንን መልዕክት የምልክልህ ከሰሜን ሸዋ ከመሀል መንዝ ነው። መልዕክቱን በአደባባይ እንደምታውለው ተስፋ አለኝ። መልዕክቱ ይኼው ነው፤
ሕወሓት እና ኦነግ ሸኔ ሰሜን ሸዋ አፆኪያ ገምዛ ወረዳ ውስጥ በምትገኝ መስኖ የምትባል ቀበሌ ላይ ወረራ በመፈጸመ በንጽሑሀን ላይ ያነጣጠረ የዘር ማጥፋት ጦርነት ከፍተው በቀጥታ በከባድ መሳሪያ ሕዝብ እየፈጁ ነው። ይፋት እና ግድም፤  ማጄቴ እና ጅጉቢም ውስጥም በተመሳሳይ ንጹሐንን  በከባድ መሳሪያ በመደብደብ የዘር ፍጅት እየፈጸሙ ነው።
አነግ ሸኔ  ከዚህ በፊት በዚህ ቦታ በስፋት ይቀሳቀስ ነበር። ባለፈው አጣየን ካወደመ በኋላ እነዚህን አካባቢዎም  ልክ አዳጣዬ ለማውደም አስቦ አልተሳካለትም ነበር።  አሁን ግን የክፋት አባቱ ከሆነው ጋር ከሕወሓት ጋር በመሆን በከባድ መሳሪያ ንጹሐንን እየጨፈጨፈ ነው።
እየተጨፈጨፉ ያሉት የሸዋ ንጹሐንም በቅርበት የሕክምና ጣቢያ ወይም  ሆስፒታል ባለመኖሩ ከፍጅቱ የተረፉ የሸዋ አማራዎች በሕክምና እጦት ምክንያት ሕይወታቸው እያለፈ ነው። እነዚህ ወገኖቻችን ሕክምና የሚያገኙት ወደ መንዝ እና መሀል ሜዳ  ረጅም መንገድ በእግር ተጉዘው ስለሆነ የሚታደጋቸው የመንግሥት አካል ባለመኖሩ ሰማዕትነት ከሚቀበሉት ብቻ ሳይሆን  ቆስለው በሕይወት የተረፉትም ጭምር ከፍተኛ ጉዳትና እየደረሰባቸውና  የሕይዎት መሰዕዋትነት ጭመር እየከፈሉ ነው።
ስለሆነም የመንግሥት አካል በአስቸኳይ በቦታው በመድረስ  እስካሁን ድረስ በሕይዎት ያሉትን ንጹሐን ከሕወሓትና ከኦነግ ሸኔ ፍጅት ይታደግ ዘንድ ተማጽኖዬን አቀርባለሁ።
በሌላ መረጃ ሽብርተኛው ሕወሓት በደሴ መስመር በወራኢሉ አድርጎ ላይ ላዩን  ወደ ሸዋ ደጋማው ክፍል፤ በተለይም ወደ መንዝ፣ መሀል ሜዳ እየገባ እንደሆነ ባካባቢው ያሉ ዘመዶቻችን በስልክ ስለነገሩን የመንግሥት አካል አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ስንል እናሳስባለን። ወደ መሀል ሽዋ ለመግባት እያደረጉት ያለው እቅስቃሴ ከልተገታና በዚህ ገፍተው ከሄዱ ደብረ ብርሀንን በቆረጣ ለመያዝ ይበቃሉ። ዘመዶቻችን እንደነገሩን እየወረሩ ያሉት በመንዝ አድርገው  ወደ መሀል ሜዳ በማምራት ቀጥታ ወደ መራቤቴ ለመሻገር ነው። ወረራቸውን የሚያደርጉት ክፍት በሆነ ቦታና የወገን ጦር ባልተጠነቀቀበት አካባቢ በመንቀሳቀስ ነው።
___
Filed in: Amharic