>

እስራኤል የጦር ወንጀል የፈጸሙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ወደ አገራቸው ለመመለስ ቃል ገባች.. !!! ( ኢትዮ ኢንተርሴፕት)

እስራኤል የጦር ወንጀል የፈጸሙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ወደ አገራቸው ለመመለስ ቃል ገባች.. !!!

ኢትዮ ኢንተርሴፕት

እስራኤል የጦር ወንጀል የፈጸሙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ወደ አገራቸውእንደምትመልስ ቃል መግባቷን ዘ ታይምስ ኦፍ እስራኤል ዘገባ አመለከተ።እስራኤል ይህን ያለችው ወደ አገሯ በስደት ከገቡት ኢትዮጵያውያን መካከል አራቱ የጦር ወንጀል የፈጸሙ በመሆናቸው ኢትዮጵያ ቅር መሰኘቷን መግለጿን ተከትሎ ነው: በጉዳዩ ዙሪያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ከእስራኤሉ አቻቸው ናፍታሊ ቤኔት ጋር በስልክ መነጋገራቸው ታውቋል።

በኢትዮጵያ የጦር ወንጀል በመፈጸም መሪ ተዋንያን የሆኑ ወንጀለኞች ወደ ጎረቤት አገራት እንዳይወጡ መንግሥት ጥብቅ ቁጥጥር እያደረገ እንደሚገኝ ይታወቃል በተለያየ አጋጣሚ ወደ ውጭና ወደ ጎረቤት አገራት የወጡ ወንጀለኞች ሲገኙም ከአገራቱ መንግሥታት ጋር በመነጋገር ኢትዮጵያ ውስጥ በሕግ እንዲጠየቁ ለማድረግ እየሰራ እንደሚገኝ ኢዜአ ዘግቧል። በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል ቀውስ ከተፈጠረ ወዲህ ማይካድራን ጨምሮ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የጦር ወንጀል የፈጸሙ ግለሰቦችና ቡድኖችን ተጠያቂ ለማድረግ መንግሥት በትኩረት እየተንቀሰቃሰ እንደሚገኝ ይታወቃል።
Filed in: Amharic