>

ተነሳ ተራመድ ...! (ዘምሳሌ)

ተነሳ ተራመድ…!

ዘምሳሌ

ተነሳ ተራመድ ክንድህን አበርታ
አሸባሪ ይጥፋ ይደምሰስ ይህ ሽፍታ
ተነሳ ተራመድ ክንድህም ይበርታ
ለቀጣዩ ትውልድ እንድትሆን መከታ
ተነስ  ታጠቅ ዝመት  ምንድነው ዝምታ
መናቆርም ይቅር  በየሁሉ ቦታ

ሆ ብለህ ተነሳ መንገላታት ይብቃ
ትጥቅህን አደራጅ ባለህበት ንቃ
እንድትኖር በሰላም ስቃዩ እንዲያበቃ
የአባቶችህ  ድንበር  መደፈሩ ይብቃ
ይህን ጨካኝ  ገዳይ  እየታጠክ  አጥቃ

ተነሳ ተራመድ ክንድህም ይበርታ
ሀገር እንድትቀጥል ትውልድ ሳይረታ
ታጋሽነት ይብቃ  ጠላትም ሳይበረታ
ዘረኝነት ይቁም  ይጥፋ ሁሉም  ሽፍታ

ተነስ ክተትና ህዝብህ አይገደል
ዘርህ እየተለየ ዘርህ አይመንገል
ባገርህ  ላትገለል በእምነትህ ላትቆስል
በዘረኞች ታረደህ  ሳይከቱህ  ከገደል
ተነስ የኢትዮጵያ ልጅ ዘረኞችን ታገል

ወያኔና ሸኔ የኢትዮጵያውን ጠላት
ተነስ  ሂድ  ካሉበት ካወጁት ጦርነት
ከሚያደርሱት ሽብር የንጹሐን ፍጅት
ባለም እንዲታወቅ ሁሉን በማሳየት
እርቃኑን እንዲወጣ የአሸባሪን ዕብሪት

ደቡብ፣ ሰሜን ምስራቅ ምእራብም  ያላችሁ
መላው የኢትዮጵያ  ልጆች ባንድነት ክንዳችሁ
ያዙት  ይህን  ባንዳ  በህብረት  ፈጥናችሁ
በርቱና አስወግዱት ከሀገር ምድራችሁ!
ኢትዮጵያ  እንድትኖር  ሁሌም ተከብራችሁ

Filed in: Amharic