>

የሰሜን ሸዋ አማራ በጥምር ወራሪዎች ዘመቻ ተከፍቶበታል....!!! (ወንድወሰን ተክሉ)

የሰሜን ሸዋ አማራ በጥምር ወራሪዎች ዘመቻ ተከፍቶበታል….!!!
ወንድወሰን ተክሉ

በሰሜን ሸዋ አማራ ህዝብ ላይ የትህነግና ኦነግ ጥምር ወራሪ ኋይል ጦርነት ተከፍቶበታል-የብልጽግና መንግስት ለወረራው ሁኔታዎችን አመቻችቷል፦
፠ አማራን ከሰሜን ሸዋ የማጽዳት ዘመቻ
የአማራን ሕዝብ ከሰሜን ሸዋ ለማጽዳት ባለመ መልኩ መጠነ ሰፊ ወረራ በትህነግና በኦነግ ጥምር ሰራዊት ተከፍቶበታል።
የሚደንቀው ወረራው ከመጀመሩ በፊት  ብአዴን ከአለቃው ብልጽግና በተሰጠው ትእዛዝ መሰረት የአካባቢውን ታጣቂ ሚሊሺያ፣ ፋኖን እና ለመዝመት ሆ ብሎ የተነሳን ሃይል ሰብስቦ ካምፕ ውስጥ በማጎር ሕዝቡን ለማንኛውም አይነት ወረራ ዝግጁ አድርጎ መጠበቁ ሲሆን በዚህም መሰረት ዛሬ እየተካሄደ ባለው ጦርነት አንዳችም መንግስታዊ ሃይልና የመከላከያ ሰራዊት እንዳልተሰለፈ ነው መረዳት የተቻለው።
አጠቃላይ የብልጽግና መራሹን መንግስት ሁኔታና ይህንንም ጦርነት እየመራ ያለበትን እስትራቴጂ ስልትና ውሳኔን ስንመለከት ለሁለት ዓመታት ያህል ደግመን ደጋግመን ስንገልጽ የነበረውን  ሰሜን ሸዋን እና ወሎን ያካተተች የታላቂቱን ኦሮሚያ ካርታን ሁኔታ እውን እያደረገ ያለስለመሆኑ በተለይም ዛሬ ላይ ሆነን አስረግጠን የምንገልጸው ነው።
የሰሜን ሸዋ ወረራን ብልጽግና መራሹ መንግስት ለወራሪው ምቹ ካደረገባቸው ተግባሮቹ አንደኛው የአካባቢውን ታጣቂና ያልተጠቀ ግን ለህልውና ትግሉ ለመቀላቀል የተነሳን ሃይል ሰብስቦ በአንድ ቦታ ማጎሩና የሀገሪቱን የኢንተርኔት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ዘግቶ መረጃ እንዳይሰራጭ አፍኖ አማራን ከሰሜን ሸዋ የማጽዳት ዘመቻ እንዲካሄድ ማድረጉ በተጨማሪነት የስርዓቱን ሚና ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ሆኖ ነው ያየነው።
በዚህ ጉዳይ ላይ ወዳጄ ግርማ ካሳ   ስለሁኔታው የሚከተለውን መረጃ አጋርቶናል።
የሸዋ ህዝብ ሚሊሺያዎች ፋኖዎች ወያኔንና ኦነግን ገትረው እየተዋጉ ነው:: በዚያ ከባድ ጦርነት አለ::ማጀቴን ለማስለቀቅ : ከሁሉም የሸዋ መሬት ሙሉ ለሙሉ ለማስወጣት ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ነው::
ይሄ ሁሉ ችግር የሆነው ::
– 1ኛ መንግስት አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ ስላልቻለ
– 2ኛ በኦሮሞብሄረሰብ ዞን በሚባለው በዞኑና  በዞኑ ባሉ ወረዳዎች የብልፅግና ሃላፊዎች እውቅናና ያለ ምንም መከልከል በነፃነት ከሁለት አመት በላይ ኦነግ እንዲደራጅና ታጣቂዎችን እንዲያሰለጥን በመደረጉ ነው::
ሌላው ኦነግና ህወሃት ተጣሉ የሚባል የፌዝ ወሬ አለ:: ይህ ሆን ተብሎ ኦነግን  ጥሩ ሃይል አድርጎ ለማቅረብ የሚሞከር ነው:: ኦነግና ህወሃት አንድ ላይ ናቸው::
እንደውም ህወሃት በጣም ይሻላል:: ህወሃት መዝረፍ ነው:: ኦነጎች ግን መዝረፍ ብቻ አይደለም ማውደምና ማቃጠል ነው ልሜዳቸው:: ህወሃት ቢያንስ ለይስሙላም ቢሆን ለህዝብ የቆምን ነን ይላሉ:: ኦነጎች ግን ንግግርም የለም መግደልና መጨፍጨፍ ነው ስራቸው::
Filed in: Amharic