>

"አሜሪካ በሰላም አስከባሪ ስም ጦሯን ወደ ኢትዮጵያ ልታዘምት ይገባል...!!!" ጀምስ ስታቨርዲስ

 
“አሜሪካ በሰላም አስከባሪ ስም ጦሯን ወደ ኢትዮጵያ ልታዘምት ይገባል…!!!”
ጀምስ ስታቨርዲስ
ዮሀንስ መኮንን

*…. “በእርግጥ ወደ ምሥራቅ አፍሪካ ጦር ማዝመት የሀገር ውስጥ ፖለቲካችንን ያበላሽብናል” የሚለው ጀምስ ስታቨርዲስ “ነገር ግን ኢትዮጵያ በስፋቷም ሆነ በጂኦግራፊያዊ አቀማመጧ በጣም አስፈላጊያችን ናት”
 
የቀድሞ የአሜሪካ ኔቪ አድሚራል፣ የኔቶ ከፍተኛ ኮማንደር በመሆን ያገለገለው ጀምስ ስታቨርዲስ (James Stavridis) ዛሬ በታተመው ብሉምበርግ ጋዜጣ ላይ “አሜሪካ ኢትዮጵያን ለማንበርከክ ካሮት እና በትር እያፈራረቀ እንዲጠቀም ለፊልትማን ልትፈቅድለት ይገባል፤ ካልሆነም ኢትዮጵያ ላይ የሰላም አስከባሪ ጦር ልታዘምት ይገባል” ሲል ጽፏል።
አሜሪካ ኢትዮጵያን በዋዛ መልቀቅ እንደሌለባት የሚመክረው  James Stavridis ለዚህ ምክንያት ያላቸውን አራት ዐበይት ጉዳዮች ያስቀምጣል።
1) የኢትዮጵያ ስፋቷ (size) እና አቅሟ (Potential)
2) ኢትዮጵያ የአፍሪካ የፖለቲካ እና የደኅንነት ማዕከል መሆኗ፤
3) ከፍተኛ ሰብአዊ ቀውስ ሊከሰት ስለሚችል፤
4) እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተጽእኖ ፈጣሪ ኢትዮጵያውያን በአሜሪካ መኖራቸው፤ (ለምሳሌ በቀደም እለት ከ70,000 በላይ ኢትዮጵያውያን በዋሽንግተን ሰልፍ መውጣታቸውን በማሳየነት ጠቅሷል)
መንግሥትን ለመጣል የሚዋጉት የትህነግ ተዋጊዎች ብቻ ሳይሆኑ በርካታ ኦሮሞዎች፣ አማራዎች እንዲሁም ሌሎች ትንሽ ቁጥር ያላቸው ብሔሮች መኖራቸውንም ይጠቅሳል።
ሰውየው አሜሪካ መውሰድ ስላለባት እርምጃ ሲመክርም ከሁሉ አስቀድሞ የተኩስ አቁም ድርድር የማያደርጉ ከሆነ አሜሪካ በሰላም አስከባሪ ስም ጦሯን ወደ ኢትዮጵያ እንድታዘምት ጠይቋል።
“በእርግጥ ወደ ምሥራቅ አፍሪካ ጦር ማዝመት የሀገር ውስጥ ፖለቲካችንን ያበላሽብናል” የሚለው ጀምስ ስታቨርዲስ “ነገር ግን ኢትዮጵያ በስፋቷም ሆነ በጂኦግራፊያዊ አቀማመጧ በጣም አስፈላጊያችን ናት” ሲል ይደመድማል።
 አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር የገባችው እሰጣገባ ጉዳዩ የሰብአዊ መብት ሳይሆን አፍሪካን ለመያዝ መግቢያ በሩን የመስበር ፍላጎት መሆኑ ግልጽ እየሆነ መጥቷል። ኢትዮጵያ ለአፍሪካውያን የኩራት እና የነጻነት ተምሳሌት መሆናቸው ብቻ ሳይሆን የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ እና የደኅንነት የስበት ማዕከል እየሆነች መምጣታ እንደ ከዚህ ቀደሙ በአፍሪካ አሻንጉሊት መንግሥታትን አስቀምጦ ለመመዝበር እንቅፋት እንደህነችባቸው መረዳት አያዳግትም።
ልብ የሚሰብረው ነገር ምዕራባውያኑ ኢትዮጵያን በማንበርከክ አፍሪካን ለመመዝበር ላይ ታች ሲሉ  የሞት ፈረስ ሆኖ እያገለገላቸው ያለው ህወሓት የተባለው ባንዳ የባንዳ ልጅ መሆኑ ነው።
“ከአጋም የተጠጋ ቁልቋል ሲያለቅስ ይኖራል” እንዲሉ ባንዳዎቹ የአሸባሪው ትህነግ አያቶቻቸው እንግሊዝን እየመሩ መቅደላ አድርሰው ኢትዮጵያን አስዘረፉ። አባቶቻቸው ጣልያንን አጅበው ለአምስት ዓመታት ኢትዮጵያን ወጉ። ዛሬ ደግሞ ልጆቻቸው ምዕራባውያንን አዝለው ሀገር ለማፍረስ ላይ ታች እያሉ ነው።
ኢትዮጵያውያን የተደቀነብንን አደጋ ለመቀልበስ በተባበረ ክንድ በአጭር ጊዜ የትህነግን ዘራፊ ቡድን መደምሰስ ቀዳሚ አጀንዳችን ሊሆን ይገባል። ይህንን ለማድረግ ያሉን ብቸኛ መተማመኛዎቻችን ደግሞ ሦስት ናቸው። ፈጣሪያችን፣ እውነታችን እና አንድነታችን!
Filed in: Amharic