>

ለመስማት ቀርቶ ለማሰብ የሚሰቀጥጠዉ የወያኔ ወንጀል (ሸንቁጥ አየለ)

ለመስማት ቀርቶ ለማሰብ የሚሰቀጥጠዉ የወያኔ ወንጀል
ሸንቁጥ አየለ

*….. የፋሽስት ወያኔ አንበጣ ሠራዊት በወሎ፣ በጎንደርና በአፋር ያካሄደውን መጠነ ሰፊ ዘረፋ፣ ውድመት፣ ንጽሑሀንን መፍጀት፣ ሴቶችንና ሕጻናት መድፈርን ጨምሮ በርካታ አረመኔያዊ ተግባሮችን እንደፈጸመ የተማረኩት የፋሽስት ወያኔ ወራሪው አንበጣ ሠራዊት አባላት እንዲህ ተናግረዋል!
ህዉሃት በፍጹም እንደማያሸንፍ ቢያሸንፍ እንኳን በቀጣይ የጉሬላ ዉጊያ.ህዝብ እራሱ ድምጥማጡ እንደሚጠፋ የነዚህ ሰዎች ምስክርነት  ጥሩ ማሳያ ነዉ :: ምርኮኞቹ የሚከተሉትን ቁልፍ ነጥቦች  በማያሻማ መልክ አቅርበዋል ፡-
1.አማራን እና ኣፋርን ጨፍጭፉ ተብለን ተላክን። አማራን እና ኣፋርን ጨፈጨፍን።
2. የአርሶ አደሩን ማሳ በሳት አጋዩ ተብለን ነበር። አጋዬንዉ።
3. የህዝቡን ንብረት ሀብት ወደ ትግራይ ጫኑ ተብለን ነበር ። አደረግነዉ።
4. ፋብሪካዎችን እና ሆስፒታሎችን እያወላለቅን ጫንን ::ቴሌቪዥን  እና ሬዲዮ እንኳን ሳይቀር ጫንን
5. ህዝቡን ድሃ አድርጉት ስለተባልን ወደ ትግራይ ያልጫንናቸዉን የህዝቡን ንብረት አወደምነዉ። በሳት አቃጠልነዉ
 6. ህዝቡን ደሃ አድርጉት ስለተባልን የህዝቡን ከብቶች ሳይቀር በመሳሪያ ረሸንናቸዉ
7. ህዝቡን  ፍዬል አንዴ በግ እረድ እያልን እያበሳቆልን ስንመገብ እና ስንበዘብዘዉ ነበር
 8. ሴቶችን እንደፍር ነበር። ህጻናትን ሳይቀር።
 9. ሽማግሌና አዛዉንትን በመሳሪያ እንደበድብ ነበር
9.ተደጋግሞ መመሪያ የተሰጠን ግን የአማራ እና አፋር ህዝብ ጠላት ነዉ ተብሎ ነዉ ::ስለዚህ የገባንበትን ሁሉ አወደምነዉ። አፈናቀልነዉ።ጨፈጨፍነዉ።
10. ህዝቡ እንዲሰደድ ሽብር ፍጠሩ። አንድ ከተማ ስትቆጣጠሩ ሌላዉ ከተማ ገና ሳይያዝ ተሸብሮ እንዲሰደድ በያዛችሁት ከተማ ላይ የመጨረሻዉን ጭካኔ ፈጽሙ። አሸብሩት የሚል መመሪያ ተሰጥቶን ስለነበረ ይሄንኑ አድርገናል
11. ያልደረሰ እንቡጥ ሰብል ስታገኙ ጨፍጭፉት። በማጭዽ እጨዱት ተብለን ነበርና አድርገንዋል::የደረሰዉን ሰብል ደግሞ በሳት እያጋዬን አዉድመንዋል
Filed in: Amharic