>
5:13 pm - Tuesday April 18, 3684

ጸረ-አማራው ጸረ-ኦርቶዶክሱ የአብይ መንግስት ዛሬ ደግሞ በቤተክህነቷ የጥይት ክምችት አገኘሁባት አለ...!!! (ጎዳና ያእቆብ)

ጸረ-አማራው ጸረ-ኦርቶዶክሱ የአብይ መንግስት ዛሬ ደግሞ በቤተክህነቷ የጥይት ክምችት አገኘሁባት አለ…!!!
ጎዳና ያእቆብ

*…. ከዘመነ ደርግ ጀምሮ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ግምጃ ቤት ተቀምጦ ያለና በመዝገብ የሰፈረን ጥይት ያዝን ብለው ኦርቶዶክስ ተዋህዶን ለማጥቃት አብይ አህመድ መነሳቱ ምንም አይደንቀኝም።
*….  የዛሬ 13 አመት ገና ኢንሳ ውስጥ እያለ <<ስልጣን ብይን በመጀነሪያ ድምጥማጧን የማጠፋት ኦርቶዶክስ ተዋህዶን ነው። ሲቀጥል ደግሞ አማራን አጠፋና ኢትዮጵያ ሰላም ትሆናለች>> ሲል አብይ አህመድ በገሀድ ጆሮ ሰጥቶ ላዳመጠው ሁሉ ይናገር እንደነበረ አብሮት ይሰራ ከነበረ የታመነ ምንጭ ተሰምቷል።
 የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ ይህንን እውነት ብዙዎች ምስክርነት የሚሰጡበት ጉዳይ ነውና ጊዜ ለኩሉ!
 አብይ አህመድ <<ሰላም ትሆናለች>> የሚላት ኢትዮጵያ ምን አይነት ኢትዮጵያ እንደሆነች እርግጠኛ ባልሆንም ኦርቶዶክስ ተዋህዶንና አማራን እንደማታካትት ግን ግልፅ ነው።
ባይሆን እኔን የሚደንቀኝ <<በሬ ካራጁ>> እንዲሉ በአብይ ጉያ ስር ያሉ ኦርቶዶክሳዊያንና አማራ ነው።
<<እናቅዳለን፣ ያቀድነውን እንናገራለን፣ የተናገርነውን ደግሞ እንተገብራለን>> በማለት የሚታወቀው አብይ አህመድ በዚህ የህልውና አደጋ ውስጥ ነን ተብሎ ሀገር በሚታመስበት ሰዕት እንኳን ከአላማው ሳይፎርሽ ዘመን የቆጠረ ጥይት ሰብስቦ አገኘሁ ብሎ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን ማሸበር ሲጀምር ሳይ እውነትም <<ቃል በተግባር>> አሰኝቶኛል።
የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ስደት ታቅዶና ህልም የሚከወን ሳይሆን መጥፎ ገጠመኝ የሚመስለው ብዙ የዋህአለናፉጣሪ አይን ትግላችንን ይግፈፍልን እንጂ ሌላ ምን ይባላል ጎበዝ!!

ጥይት በቤተ ክህነት

ዲያቆን አባይነህ ካሳ

ተገኘ እየተባለ የሚናፈሰው ዜና መሠረት የሳተ ነው። በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመን ለቤተ ክህነት ጥበቃ ከተሰጡ ጥይቶች መካከል ሲተላለፉ የኖሩ ጥይቶችን ለሽብር ተግባር ተሰውረው እንደገቡ አድርጎ ማቅረብ ኃላፊነት የጎደለው ብቻ ሳይኾን ክብረ ነክም ነው።
በንብረት ደረጃ ተሰፍረው ተቆጥረው በመዝገብ (በቬርባል) ተይዘው ከአንዱ የንብረት ቤት ሠራተኛ ወደ ሌላው ሲተላለፉ የኖሩ ናቸው።
ስለኾነም ቤተ ክህነቱ ፡ –
፩. ዝርዝር ማብራሪያ ሊሰጥበት ይገባል
፪. ቤተ ክህነቱን የወሬ ቀለብ ያደረጉትን ስም ያጠፉ አካላትን ከከንቲባዋ ጀምሮ፣ የዐዲስ አበባ ፖሊስ፣ ኢቢሲ እና ፋና በሕግ መጠየቅ አለበት።
በፍተሻ ተገኘ የሚባለው በመዝገብ የሰፈረን ሁሉ ከኾነ ጠሚ ቢሮ ብዙ እንደሚያገኙ ልጠቁም። ለማንኛውም ነገሩ ገብቶናል። ብንተዋችሁም አትተውንም።
Filed in: Amharic