>

"እኔምለው ይሄ ደብረጽዮን የሚባል ሰው ለምንድነው የራሱን ህዝብ እንዲህ አምርሮ የጠላው ?!" (አንዷለም ቡቄቶ ገዳ

“እኔምለው ይሄ ደብረጽዮን የሚባል ሰው ለምንድነው የራሱን ህዝብ እንዲህ አምርሮ የጠላው ?!” ,,,,
  አንዷለም ቡቄቶ ገዳ

*…. በየቀኑ ለሚረግፈው የትግራይ ወጣት ነብስ ማንም የሚገደው የለም! … ይህ ምስኪን ወጣት በየቀኑ ተጨፍጭፎ ሲያበቃ ና  ሪፖርቱ ሲቀርብ…. ደብረጺዮን እጁ እየተንቀጠቀጠ ቅጥ አምባሩ የጠፋ መግለጫ ያወጣበታል!አሜሪካን ጂኦ- ፖለቲካውን ይቆምርበታል!
ሸኔ ካሁን አሁን ታዘልኩ እያለ ይቋምጥበታል !ጌች ክላስ ባለው እንግሊዝኛ ይራቀቅበታል!… ስታሊን ይኮምክበታል!…. ይሄው ነው!!!
በሚዲያ እንደማየው በከተሞች ወይም በውጭ ሀገራት በምቾት የሚኖሩ ተጋሩዎች “ህወሃት እዚህ ደረሰች! እዚያ ልትገባ ነው” እያሉ ይጨፍራሉ …በአሸናፊነት እብሪት ይወጠራሉ! የነሱን ጠባብ ብሄርተኛነት የወለደው የአሸናፊነት ስሜት ለማርካት የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር(ህወሃት) እያደረገ ያለውን ከሚሊታሪ ሳይንስ የተጣላ አካሄድ ለመመርመር ግን አይደፍሩም፡፡
የነጻነት ግንባሩ ከፕሮፓጋንዳ ያለፈ ስትራቴጅካዊ ጠቀሜታ ያሌላቸውን ቦታዎች ለመቆጣጠር ህዝቡን በገፍ እያሰለፈ በሚያደርጋቸው ጦርነቶች እንደ ቅጠል እየረገፈ ያለው ምስኪን ተጋሩ ህይወት አያሳስባቸውም፡፡
ከወር በፊት የጎንደር ፋኖዎችን አግኝቼ ስል ውቅን ተራራ ውግያ ስንጨዋወት አንደኛው ፋኖ የጠየቀኝ ጥያቄ እስከ አሁን አእምሮዬ ላይ አለ…”ወንድም አንዱአለም ..እኔ የውግያ ነገር ብትጠይቀኝ በደንብ አስረዳሃለው ..እንደው አንዳንዴ ግን የእነሱ (የትግራይ) ፖለቲካ ምንም አይገባኝም! እስቲ አስረዳኝ” አለኝ
“ምኑን ነው ግራ የሚገባህ?” አልኩት
“እንደው ይሄ ዶ/ር ደብረጽዮን የሚባል ለምንድነው እንዲህ የራሱን ህዝብ እምርሮ የጠላው ?!” ነበር ያለኝ፡፡
ይህ ፖለቲካ አይደለም…ፈጣሪ ምስክሬ ነው!
የህወሃት አመራሮች ትርጉም በሌለው ሁኔታ ህዝቡን በገፍ እየለቀቁ እንዴት እንዳስፈጁት ፋኖዎቹ ሲናገሩ እንደኔ በቦታው ሆናችሁ ብትሰሙ ቢያንስ የዛን ቀን በቀላሉ እንቅልፍ አይወስዳችሁም ነበር፡፡
ከቀናት በፊት
 ሚሌን ለመያዝ ህዋሃት ያደረገውን ሙከራ በተመለከተ በቀጥታ ውግያው ውስጥ ከነበረ አንድ ወዳጅ የተነገረኝ እጅግ አሳዛኝ ነገር ነበር….
በእግዚያብሄር አምሳል ለተፈጠረ ማንኛውም ሰው የሚያሰቅቅ ፡በቀጥታ ለማየት እስከሚዘገንን ድረስ የተጋሩ ሬሳ ተከምሮ ነበር..
ጥቂት ከተማረከው በቀር ከዘመተው በሺዎች የሚቆጠር ሰራዊት ውስጥ ለወሬ ነጋሪ የተረፈ የለም፡፡
ይሄ መረጃ ኖሮት “ግን ለምን?!” ብሎ የሚጠይቅ አንድም ተጋሩ የለም! ሊኖርም አይችልም ፡፡
አንድ ቀጭን መንገድ ይዞ ወደ አዲስአበባ በሚደረግ ጉዞ መንግስት ሊለወጥ እንደማይችል የህወሃት አመራሮች በደንብ ያውቁታል..…ወደ ሸዋ እገሰገስን ነው የሚባለውም በተጋሩ ነብስ ላይ የሚደረግ የፕሮፓጋንዳ ቁማር እንደሆነ የሚገባው ይገባዋል…
አሁን ላይ ትግራይ …..እንጥፍጣፊ ወንድ እስከሚቀራት ድረስ ህዝቦቿን ልታስጨርስ ወደምትችልበት ጫፍ የሚያደርሳት ጦርነት ውስጥ እየተዘፈቀች እንደሆነ  …በጠባብ ብሄርተኝነት አእምሮውን ለደፈኑት እና አንድ ለአምስት ለጠረነፉት ደጋፊያቸው ሊገለጽለት አይችልም…አሁን ይሄን የሚያነበውም ተጋሩ እውነታውን ከመቀበል ወይም ከመመርመር በፊት (ልክ እንደሰሜን ኮሪያ ዜጎች) ከኔ ጋር እንዴት እንደሚሟገት ብቻ ያስባል…ያሳዝናል፡፡
በየቀኑ ለሚረግፈው የትግራይ ወጣት ነብስ ማንም የሚገደው የለም፡፡…ይህ ምስኪን ወጣት በየቀኑ ተጨፍጭፎ ሲያበቃ ና  ሪፖርቱ ሲቀርብ….ደብረጺዮን እጁ እየተንቀጠቀጠ መላአምባሩ የጠፋ መግለጫ ያወጣበታል ፡አሜሪካን ጂኦ- ፖለቲካውን ይቆምርበታል፡ ሸኔ ካሁን አሁን ታዘልኩ እያለ ይቋምጥበታል ፡ጌች ክላስ ባለው እንግሊዝኛ ይራቀቅበታል… ስታሊን ይኮምክበታል….
በአጠቃላይ ግን  ለባለፉት 50 አመታት ህወሃት በኖረችበት ወቅት ተወልዶ  ወጣትነቱ በዚህ ወቅት እንዲሆን እጣክፍሉ የሆነው ትግራዋይ  ወጣት ያሳዝናል!
Filed in: Amharic