>
5:13 pm - Monday April 19, 3486

የቀድሞው ወታደር... ሁለት ነፍስ አለው? (አሳፍ ሀይሉ)

የቀድሞው ወታደር… ሁለት ነፍስ አለው?

አሳፍ ሀይሉ

በሥልጣን ወንበር ተቆናጥጠው፣ ከሥልጣን የሚገኘውን ጥቅምና ትርፍራፊ ሙልጭ አድርገው ሲልሱ ይቆዩና፣ የሚልሱት ወንበር አጣብቂኝ ውስጥ ሲወድቅባቸው፣ በደህና ጊዜ ያላስታወሱትን መከረኛ የቀድሞ ሠራዊት “ናና ለወንበራችን ተዋጋልን” ይሉታል!
በ1983 ላይ የቀድሞ የኢትዮጵያ ሠራዊት ሲበተን ዕድሜው 30 ዓመት የነበረ ወታደር፣ አሁን ከ30 ዓመት በኋላ ስንት ዓመት ይሆነዋል? የ60 ዓመት የዕድሜ ባለፀጋ! በ83 ላይ ዕድሜው 25 ዓመት የነበረ የቀድሞ ወታደር አሁን ዕድሜው ስንት ነው? 55 ዓመት!
በምን ዕዳው ነው እሱ ያኔ አጥንቱን በከሰከሰበት ምድር መከራውን ሲበላ የኖረው ሳያንስ፣ አሁን የናንተን የዘረኝነት ወንበርና ልዩ ጥቅም ሊያስጠብቅላችሁ በስተርጅና ከቤቱ ወጥቶ የሚሞትላችሁ? ምን በወጣው? የቀድሞ ወታደር ከእናንተ አባቶች የበለጠ ሁለት ነፍስ አለው ደጋግሞ የሚሞተው?
የዕድሜ ባለፀጋው መከረኛ የቀድሞ ወታደር ናና ለወንበራችን ተዋጋ ይባላል!! ምን ዓይነት ይሉኝታ ማጣት ነው? ምንም ምንተ ዕፍረትም… ምንም ፈሪሀ እግዜርም የላቸውም! በማንኛውም ዋጋ፣ የአሁኑን ትውልድ ማግደውም፣ ከቀድሞው ትውልድ ተበድረውም፣ የተረኝነት ወንበራቸውን ለማስጠበቅ ይሟሟታሉ!
ሲሟሟቱ ደሞ መሬት ጥለው በሚረጋግጡት በባንዲራው ስም ነው! በዘር ተጠራርተው በሚግጧት በኢትዮጵያችን ስም ነው! ይሉኝታ የሚባል የላቸውም! ሰው ከህሊናው ከተለየ ሙት በድን ነው እንዳለው ነው ደራሲው! የጥቅም ሽሚያና ዘረኝነት ህሊናቸውን አበድኖታል! የተነከሩበት ደም ነውሩንና ነውር ያልሆነውን እንዳይለዩ አስክሯቸዋል!
እንጂ ደፍረው የቀድሞው ወታደር ናና በስተርጅና ለልዩ ጥቅማችን ሙትልን አይሉም ነበር! አይባልም! ነውር ነው! እናንተ ደሞ ሙቱ! እና የሰለቀጣችሁትን ኮንዶሚኒየም፣ የተንሰፈሰፋችሁለትን መንበረ ሥልጣን አድኑ!
ይኸው ነው!
Filed in: Amharic