>

ወያኔ አሁን ያለዉን መንግስት ማፍረስ ቢችል እንኳን ፈጽሞ አሸናፊ ሆኖ ኢትዮጵያን ማስተዳደር አይችልም::ለምን? ( ሸንቁጥ አየለ)

ወያኔ አሁን ያለዉን መንግስት ማፍረስ ቢችል እንኳን ፈጽሞ አሸናፊ ሆኖ ኢትዮጵያን ማስተዳደር አይችልም::ለምን?
——
ሸንቁጥ አየለ

ለዚህም ብዙ ምክንያቶች አሉ::ዋና ዋናዎቹም:-
1.ወያኔ የተጣላዉ ከህዝብ ጋር ነዉ::ህዝብም ታጥቆ እና ጦርነቱን የኔ ነዉ ብሎ ተነስቷል::ስለሆነም ከህዝብ አብራክ እጅግ አሰፍሪ እና ሀያል ጦር ይወለዳል::
2.የሀገሪቱ መሪዎች ሊሸሹ ይችላሉ::ህዝቡ ግን ዉጊያዉን ይቀጥላል::በዚህም ወያኔ እንዳሰበዉ አሁን ያለዉን የመንግስት ሰራዊት ቢበትንም ጦረኛዉ ሀይል እህዝብ ጉያ ስለሆነ ወያኔን የሚወጋዉ የህዝብ ጦር የሚበተን አይደለም
3.ወያኔ አሁንም በሚያደርገዉ ፕሮፖጋንዳ ደንቆሮ:ሞኝ እና አብሪተኛ መሆኑን ደጋግሞ እያስመሰከረ ነዉ::ለማሳያነትም የሚከተሉት የወያኔ ፕሮፖጋንዳዎች በቂ ናቸዉ
ሀ.አማራን እንበቀለዋለን::አማራ ጠላታችን ነዉ::የአማራ ህዝብ እስካለ እኛ በሰላም አንኖርም
ለ.አማራን እንበቀለዋለን እንዳለዉም የያዛቸዉን የአማራ አካባቢዎችን ሙሉ ለሙሉ የማዉደም ስራዉን ቀጥሏል::ህዝቡን በማፈናቀል ለረሃብ የመዳረግ ስራዉን ያለ እረፍት አከናዉኗል
ሐ.እስክንድር ነጋ የዘር ማጥፋት ወንጀለኛ ነዉ ሲልም ወያኔ አሁንም የፖለቲካ ልዕልና ያላቸዉን ተቃዋሚዎች ለማጥፋት እንደቆረጠ በሚዲያዎች እያሰራጨ ነዉ::
መ. ኦነግን ከያዝኩ ኢትዮጵያን እንዳሰኘኝ ጠፍጥፌ እሰራታለሁ::የአማራ ህዝብ በምመሰርተዉ መንግስት ዉስጥ ቢሳተፍም ባይሳተፍም ለዉጥ የለዉም::አሁን ተሳተፉ ስንላችሁ እንቢ ብላችሁ ብኋላ እንዳታላዝኑ::
ረ. የአፋር ህዝብ እና የአማራ ህዝብ ጠላታችን ስለሆነ አጥፉት::ከብቱንም ሰዉንም ግደሉ::ሰብሉን አቃጥሉ::መልካም የሆነ ሀብትን ሁሉ ወደ ትግራይ አሽሹ::የቀረዉን ንብረቱን አዉድሙ::
ሸ. የኦሮሞን ህዝብ እና ኦህዴድን መለዬት የተሳናቸዉ የህዉሃት አመራሮች እና ፕሮፖጋንዲስቶች በኦሮሞ ህዝብ ኢትዮጵያዊነት ላይም እየተሳለቁ ነዉ:: አዳነች አበቤ ለሰራችዉ ትግራይ ከፈለገች ትገንጠል ለሚለዉ ትልቅ ስህተት ኦህዴድን መሳደብም ሆነ መዉቀስ ተገቢ ነዉ::ሆኖም ድርጅት እና ህዝብን መለዬት የማይችለዉ ህዉሃት የኦሮሞን ህዝብ በአጠቃላይ እየተሳደበ ነዉ:: “እኛ የትግራይ ሰዎች ጥንታዊ የኢትዮጵያ መስራቾች ነን::የኦሮሞ ህዝብ ኢትዮጵያዊ የሆነዉ በደብዳቤ ነዉ” ሲልም እየተሳለቀ ነዉ::ወያኔዎች ሞኝ እና እብሪተኛ ስለሆኑ ህዝብ የሚያደምጥ አይመስላቸዉም::ህዝብ ግን እያደመጠ እና እየመዘነ ነዉ::
ቀ.የአፋርን ህዝብ:የአማራን ህዝብ:የኦሮሞን ህዝብ በታላቅ ንቀት አሁንም እንደ ድሮዉ የሚያበሻቅጠዉ ወያኔ እንደ ኦነግ አይነት ፈረስ ግን አላጣም::ሆኖም ኦነግ እራሱ ወያኔን መሃል ሜዳ ላይ ጥሎ ጉድ እንደሚሰራዉ የሚያጠያይቅ አይደለም::ኦነግ በወያኔ ላይ ይሄ ነዉ የማይባል ቂም ያለዉ ድርጅት ነው::እናም በ1983 ዓም ወያኔ በኦነግ ላይ የሰራዉን ወንጀል አሁንም ምቹ ሁኔታ ሲፈጠርለት ኦነግ በወያኔ ላይ እንደሚሰራዉ ወያኔዎች በደንብ ያዉቃሉ::ስለዚህ የወያኔና የኦነግ ግንኙነት እራሱ ምቹ ሁኔታ ሲፈጠር ቀድሞ ማን ያጠፋል በሚል ስሌት ላይ የቆመ ነዉ
4.ኢትዮጵያ እንድትፈርስ ከሚፈልጉት የኦነግ እና የወያኔ ደጋፊዎች በቀር ቀሪዉ ጠቅላላ ኢትዮጵያዊ ሀገር እንዲኖረዉ ስለሚፈልግ ወያኔ እና ኦነግን ለማጥቃት አጋጣሚ በሚያገኝበት ሰዓት ሁሉ ከምድረ ገጽ እንዲጠፉ የሚሰራ ህዝብ መሆኑ ግልጽ ነዉ
5.የወያኔ የፖለቲካና የጦር ስትራቴጅስቶች የ1983 ዓም ልምዳቸዉን እና ትንታኔያቸዉን አሁንም ለመድገም መሰረት አድርገዉ ይዘዉታል::ይሄም ስትራቴጂያቸዉ ፈጽሞ የተሳሳተ የሞት ዉቅያኖስ ዉስጥ ከቷቸዋል::የ1983 ዓም እና አሁን ያለዉ ሁኔታ:የነገዶች የሀይል አሰላለፍ:የስነልቦና ጭብጥ:የማህበረሰቡ ለዉጊያ ዝግጁነት :የተቃዋሚ ሀይሎች አሰላለፍ እና የብዙ ነገሮች ዉስብስብ ድምር ዉጤት ወያኔና ኦነግ እንደሚያሰሉት ፈጽሞ አይገናኝም::ወያኔ ይሄንንም ባለመረዳቱ ጥፋቱን በራሱ እጂ የሚቆፍር ሀይል ነዉ::
Filed in: Amharic